YouVersion Logo
Search Icon

መጽ​ሐፈ ሳሙ​ኤል ቀዳ​ማዊ 12

12
የሳ​ሙ​ኤል የመ​ሰ​ና​በቻ ንግ​ግር
1ሳሙ​ኤ​ልም ለእ​ስ​ራ​ኤል ሕዝብ ሁሉ አለ፥ “የነ​ገ​ራ​ች​ሁ​ኝን ሁሉ ሰምቼ ንጉሥ አን​ግ​ሼ​ላ​ች​ኋ​ለሁ። 2አሁ​ንም እነሆ፥ ንጉሡ በፊ​ታ​ችሁ ይሄ​ዳል፤ እኔም አር​ጅ​ቻ​ለሁ፤ እን​ግ​ዲ​ህም አር​ፋ​ለሁ፤ እነ​ሆም፥ ልጆቼ ከእ​ና​ንተ ጋር ናቸው፤ እኔም ከሕ​ፃ​ን​ነቴ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ በፊ​ታ​ችሁ ሄድሁ። 3እነ​ሆኝ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርና እርሱ በቀ​ባው ፊት መስ​ክ​ሩ​ብኝ፤ የማ​ንን በሬ ወሰ​ድሁ? የማ​ን​ንስ አህያ ወሰ​ድሁ? ማን​ንስ ሸነ​ገ​ልሁ? በማ​ንስ ላይ ግፍ አደ​ረ​ግሁ? ነጠላ ጫማ እን​ኳን ቢሆን ከማን እጅ መማ​ለጃ ተቀ​በ​ልሁ? መስ​ክ​ሩ​ብኝ፤ እኔ እመ​ል​ስ​ላ​ች​ኋ​ለሁ።” 4እነ​ር​ሱም ሳሙ​ኤ​ልን፥ “ግፍም አላ​ደ​ረ​ግ​ህ​ብ​ንም፤ የቀ​ማ​ኸን የለም፤ አላ​ሠ​ቃ​የ​ኸ​ንም፤ ከእ​ኛም ከማ​ንም እጅ ምንም አል​ወ​ሰ​ድ​ህም” አሉት። 5ሳሙ​ኤ​ልም፥ “በእጄ ምንም እን​ዳ​ላ​ገ​ኛ​ችሁ ዛሬ በዚ​ህች ቀን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምስ​ክር ነው፤ እርሱ የቀ​ባ​ውም ምስ​ክር ነው” አላ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም፥ “አዎ ምስ​ክር ነው” አሉ።
6ሳሙ​ኤ​ልም ሕዝ​ቡን አለ፥ “ሙሴ​ንና አሮ​ንን ያላቀ፥ አባ​ቶ​ቻ​ች​ሁ​ንም ከግ​ብጽ ምድር ያወጣ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምስ​ክር ነው። 7አሁ​ንም ቁሙ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት እፋ​ረ​ዳ​ች​ኋ​ለሁ፤ ለእ​ና​ን​ተና ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ ያደ​ረ​ገ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጽድቅ ሁሉ እነ​ግ​ራ​ች​ኋ​ለሁ። 8ያዕ​ቆ​ብና ልጆቹ ወደ ግብጽ በገቡ ጊዜ ግብ​ጻ​ው​ያን አስ​ጨ​ነ​ቁ​አ​ቸው፤ አባ​ቶ​ቻ​ች​ሁም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኹ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴ​ንና አሮ​ንን ላከ፤ አባ​ቶ​ቻ​ች​ሁ​ንም ከግ​ብጽ አው​ጥ​ተው በዚህ ቦታ አኖ​ሩ​አ​ቸው። 9አም​ላ​ካ​ቸ​ው​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ረሱ፤ ለአ​ሶር ሠራ​ዊ​ትም አለቃ ለሲ​ሣራ እጅ፥ ለፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም እጅ፥ ለሞ​ዓ​ብም ንጉሥ እጅ አሳ​ልፎ ሰጣ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም ወጉ​አ​ቸው፤ 10እነ​ር​ሱም፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትተን በዓ​ሊ​ም​ንና ምስ​ሎ​ቹን በማ​ም​ለ​ካ​ችን በድ​ለ​ናል፤ አሁ​ንም ከጠ​ላ​ቶ​ቻ​ችን እጅ አድ​ነን፤ እና​መ​ል​ክ​ሃ​ለ​ንም” ብለው ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኹ ። 11እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ይሩ​በ​ኣ​ልን፥ ባር​ቅ​ንም፥ ዮፍ​ታ​ሔ​ንም፥ ሳሙ​ኤ​ል​ንም ላከ፤ በዙ​ሪ​ያ​ች​ሁም ካሉት ከጠ​ላ​ቶ​ቻ​ችሁ እጅ አዳ​ኑ​አ​ችሁ፤ ተዘ​ል​ላ​ች​ሁም ተቀ​መ​ጣ​ችሁ። 12የአ​ሞ​ንም ልጆች ንጉሥ ናዖስ እንደ መጣ​ባ​ችሁ ባያ​ችሁ ጊዜ፥ አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ንጉ​ሣ​ችሁ ሳለ፦ እን​ዲህ አይ​ሁን፤ ነገር ግን ንጉሥ አን​ግ​ሥ​ልን አላ​ች​ሁኝ። 13አሁ​ንም የመ​ረ​ጣ​ች​ሁ​ትን ንጉሥ እዩ፤ እነ​ሆም፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ንጉሥ ሰጣ​ችሁ። 14እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ብት​ፈሩ፥ ብታ​መ​ል​ኩ​ትም፥ ቃሉ​ንም ብት​ሰሙ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ትእ​ዛዝ ላይ ባታ​ምፁ፥ እና​ን​ተና በእ​ና​ንተ ላይ የነ​ገ​ሠው ንጉሥ አም​ላ​ካ​ች​ሁን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ብት​ከ​ተሉ፥ መል​ካም ይሆ​ን​ላ​ች​ኋል። 15ነገር ግን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ባት​ሰሙ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ትእ​ዛዝ ላይ ብታ​ምፁ፥ በእ​ና​ን​ተና በን​ጉ​ሣ​ችሁ ላይ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ ትመ​ጣ​ለች። 16አሁ​ንም ቁሙ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በዐ​ይ​ና​ችሁ ፊት የሚ​ያ​ደ​ር​ገ​ውን ይህን ታላቅ ነገር ተመ​ል​ከቱ። 17የስ​ንዴ መከር ዛሬ አይ​ደ​ለ​ምን? ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጮ​ኻ​ለሁ፤ እር​ሱም ነጐ​ድ​ጓ​ድ​ንና ዝና​ብን ይል​ካል፤ እና​ን​ተም ንጉሥ በመ​ለ​መ​ና​ችሁ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያደ​ረ​ጋ​ች​ሁት ክፋት ታላቅ እንደ ሆነ ታው​ቃ​ላ​ችሁ፤ ታያ​ላ​ች​ሁም።” 18ሳሙ​ኤ​ልም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኸ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በዚያ ቀን ነጐ​ድ​ጓ​ድ​ንና ዝና​ብን ላከ፤ ያን​ጊ​ዜም ሕዝቡ ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንና ሳሙ​ኤ​ልን እጅግ ፈሩ​አ​ቸው።
19ሕዝ​ቡም ሁሉ ሳሙ​ኤ​ልን፥ “ንጉሥ በመ​ለ​መ​ና​ችን በኀ​ጢ​አ​ታ​ችን ሁሉ ላይ ይህን ክፋት ጨም​ረ​ና​ልና እን​ዳ​ን​ሞት ስለ ባሪ​ያ​ዎ​ችህ ወደ አም​ላ​ክህ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸል​ይ​ልን” አሉት። 20ሳሙ​ኤ​ልም ሕዝ​ቡን ሁሉ አላ​ቸው፥ “አት​ፍሩ፤ በእ​ው​ነት ይህን ክፋት ሁሉ አደ​ረ​ጋ​ችሁ፤ ነገር ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በፍ​ጹም ልባ​ችሁ አም​ል​ኩት እንጂ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ከመ​ከ​ተል ፈቀቅ አት​በሉ። 21ምንም አይ​ደ​ሉ​ምና የማ​ይ​ረ​ቡ​ት​ንና የማ​ያ​ድ​ኑ​አ​ች​ሁን ለመ​ከ​ተል ከእ​ርሱ ፈቀቅ አት​በሉ። 22እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለእ​ርሱ ሕዝብ ያደ​ር​ጋ​ችሁ ዘንድ ተቀ​ብ​ሎ​አ​ች​ኋ​ልና፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ ታላቅ ስሙ ሕዝ​ቡን አይ​ተ​ውም። 23ደግሞ መል​ካ​ሙ​ንና ቅኑን መን​ገድ አሳ​ያ​ች​ኋ​ለሁ እንጂ ስለ እና​ንተ መጸ​ለ​ይ​ንና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ማገ​ል​ገ​ልን በመ​ተው እር​ሱን እበ​ድል ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይህን አያ​ድ​ር​ግ​ብኝ። 24ብቻ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፍሩ፤ ያደ​ረ​ገ​ላ​ች​ሁ​ንም ታላቅ ነገር አይ​ታ​ች​ኋ​ልና በፍ​ጹም ልባ​ችሁ በእ​ው​ነት አም​ል​ኩት፤ 25ነገር ግን ክፉ ብት​ሠሩ እና​ን​ተም፥ ንጉ​ሣ​ች​ሁም ትጠ​ፋ​ላ​ችሁ።”

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in