YouVersion Logo
Search Icon

መጽ​ሐፈ ሳሙ​ኤል ቀዳ​ማዊ 2

2
የሳ​ሙ​ኤል እናት የሐና ጸሎት
1ሐናም ጸለ​የች፤ እን​ዲ​ህም አለች፦
“ልቤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸና፤
ቀን​ዴም#ምሥ​ጢሩ “ኀይል” ነው። በአ​ም​ላኬ በመ​ድ​ኀ​ኒቴ ከፍ ከፍ አለ፤
አፌ በጠ​ላ​ቶቼ ላይ ተከ​ፈተ፤
በማ​ዳ​ን​ህም ደስ ብሎ​ኛል።
2እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቅዱስ የለ​ምና፥
እንደ አም​ላ​ካ​ች​ንም ጻድቅ የለ​ምና፤
አቤቱ፥ ከአ​ን​ተም በቀር ቅዱስ የለም።
3አት​መኩ፤ የኵ​ራት ነገ​ሮ​ች​ንም አት​ና​ገሩ፤
ፅኑዕ ነገ​ርም ከአ​ፋ​ችሁ አይ​ውጣ፤
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ ዐዋቂ ነውና፥
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ዙፋ​ኑን ያዘ​ጋ​ጃል።#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “ሥራ​ውን የሚ​መ​ዝን ነውና” ይላል።
4የኀ​ያ​ላ​ንን ቀስት ሰብ​ሮ​አል፤
ደካ​ሞ​ች​ንም ኀይ​ልን አስ​ታ​ጥ​ቋ​ቸ​ዋል።
5እን​ጀራ ጠግ​በው የነ​በሩ ተራቡ፤
ተር​በ​ውም የነ​በሩ ጠገቡ፤
መካ​ኒቱ ሰባት ወል​ዳ​ለ​ችና፥
ብዙም የወ​ለ​ደ​ችው መው​ለድ አል​ቻ​ለ​ችም።
6እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይገ​ድ​ላል፤ ያድ​ና​ልም፤
ወደ ሲኦል ያወ​ር​ዳል፤ ያወ​ጣ​ልም።
7እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ድሀ ያደ​ር​ጋል፤ ባለ​ጠ​ጋም ያደ​ር​ጋል፤
ያዋ​ር​ዳል፤ ደግ​ሞም ከፍ ከፍ ያደ​ር​ጋል።
8ችግ​ረ​ኛ​ውን ከመ​ሬት ያነ​ሣ​ዋል፤
ምስ​ኪ​ኑ​ንም ከጕ​ድፍ ያነ​ሣ​ዋል፤
ከሕ​ዝቡ መኳ​ን​ንት ጋር ያስ​ቀ​ም​ጠው ዘንድ፥
የክ​ብ​ር​ንም ዙፋን ያወ​ር​ሰው ዘንድ።
9ለሚ​ጸ​ልይ ጸሎ​ቱን ይሰ​ጠ​ዋል፤
የጻ​ድ​ቃ​ንን ዘመን ይባ​ር​ካል፤
የሰው ኀይል ጽኑዕ አይ​ደ​ለ​ምና።
10እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጠላ​ቶ​ቹን ያደ​ክ​ማ​ቸ​ዋል፤
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ብቻ ቅዱስ ነው፤
ጥበ​በኛ በጥ​በቡ አይ​መካ፤
ኀይ​ለ​ኛም በኀ​ይሉ አይ​መካ፤
ሀብ​ታ​ምም በሀ​ብቱ አይ​መካ፤
የሚ​መካ ግን በዚህ ይመካ፤
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በማ​ወ​ቅና በማ​ስ​ተ​ዋል፤
በም​ድ​ርም መካ​ከል ፍር​ድ​ንና እው​ነ​ትን በማ​ድ​ረግ፥
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ ሰማይ ወጣ፤ አን​ጐ​ደ​ጐ​ደም።
ጻድቅ እርሱ እስከ ምድር ዳርቻ ይፈ​ር​ዳል፤
ለን​ጉ​ሦ​ቻ​ች​ንም ኀይ​ልን ይሰ​ጣል፤
የመ​ሲ​ሑ​ንም ቀንድ ከፍ ከፍ ያደ​ር​ጋል።”#ምዕ. 2 ቍ. 8፥ 9 እና 10 በዕብ. እና በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. ልዩ​ነት አለው።
11በዚ​ያም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ተዉት።#ግሪክ ሰባ. ሊ. “በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ትታው ሄደች” ይላል። እነ​ር​ሱም ወደ አር​ማ​ቴም ወደ ቤታ​ቸው ገቡ፤ ልጁም በካ​ህኑ በዔሊ ፊት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያገ​ለ​ግል ነበር።
የካ​ህኑ የዔሊ ልጆች ክፉ ሥራ
12የካ​ህ​ኑም የዔሊ ልጆች ክፉ​ዎች ነበሩ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም አያ​ው​ቁም ነበር። 13መሥ​ዋ​ዕት በሚ​ሠዉ በሕ​ዝቡ ሁሉ ዘንድ የነ​በረ የካ​ህ​ኑ​ንም ሕግ አያ​ው​ቁም ነበረ፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ መሥ​ዋ​ዕት በሠዉ ጊዜ የካ​ህኑ ብላ​ቴና ይመጣ ነበር፤ በእ​ጁም ሦስት ጣት ያለው ሜንጦ ነበር፤ 14ወደ ድስ​ቱም ወይም ወደ ምን​ቸቱ ወይም ወደ አፍ​ላሉ ወይም ወደ ቶፋው#“ወደ ቶፋው” የሚ​ለው በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም። ይሰ​ድ​ደው ነበር። ሜን​ጦ​ውም ያወ​ጣ​ውን ሁሉ ካህኑ ለእ​ርሱ ይወ​ስ​ደው ነበር፤ በሴ​ሎም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሊሠዉ በሚ​ወጡ በእ​ስ​ራ​ኤ​ላ​ው​ያን ሁሉ ላይ እን​ዲህ ያደ​ርጉ ነበር። 15ደግ​ሞም ስቡ ሳይ​ጤስ የካ​ህኑ ልጅ መጥቶ የሚ​ሠ​ዋ​ውን ሰው፥ “ጥሬ​ውን እንጂ የተ​ቀ​ቀ​ለ​ውን ሥጋ ከአ​ንተ አይ​ወ​ስ​ድ​ምና እጠ​ብ​ስ​ለት ዘንድ ለካ​ህኑ ሥጋ ስጠኝ” ይለው ነበር። 16የሚ​ሠ​ዋ​ውም ሰው፥ “አስ​ቀ​ድሞ እንደ ሕጉ ስቡ ይጢስ፤ ኋላም ሰው​ነ​ት​ህን ደስ የሚ​ያ​ሰ​ኛ​ትን ትወ​ስ​ዳ​ለህ” ቢለው፥ እርሱ፥ “አይ​ሆ​ንም፥ ነገር ግን አሁን ስጠኝ፤ ካል​ሆ​ነም በግድ አወ​ስ​ደ​ዋ​ለሁ” ይለው ነበር። 17የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቍር​ባን ይንቁ ነበ​ርና የዔሊ ልጆች ኀጢ​አት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እጅግ ታላቅ ነበ​ረች።
ብላ​ቴ​ናው ሳሙ​ኤል በሴሎ
18ሳሙ​ኤል ግን ገና ብላ​ቴና ሳለ የበ​ፍታ ኤፉድ ታጥቆ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያገ​ለ​ግል ነበር። 19እና​ቱም ታናሽ መደ​ረ​ቢያ ሠራ​ች​ለት፤ በየዓ​መ​ቱም መሥ​ዋ​ዕት ለመ​ሠ​ዋት ከባ​ልዋ ጋር ስት​ወጣ ትወ​ስ​ድ​ለት ነበር። 20ዔሊም ሕል​ቃ​ና​ንና ሚስ​ቱን ባረ​ካ​ቸው፥ “ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ አገ​ባ​ኸው ስጦታ ፈንታ ከዚ​ህች ሴት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘር ይስ​ጥህ” አለው፤ እነ​ር​ሱም ወደ ቤታ​ቸው ገቡ። 21እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሐናን ጐበኘ፤ ዳግ​መ​ኛም ፀነ​ሰች፥#“ፀነ​ሰች” የሚ​ለው በዕብ. ብቻ። ሦስት ወን​ዶ​ችና ሁለት ሴቶች ልጆ​ችን ወለ​ደች። ብላ​ቴ​ናው ሳሙ​ኤ​ልም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት አደገ።
ካህኑ ዔሊ የል​ጆ​ቹን ክፉ ሥራ እንደ ሰማ
22ዔሊም እጅግ አረጀ፤ ልጆ​ቹም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ያደ​ረ​ጓ​ቸ​ውን፥ በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ ከሚ​ያ​ገ​ለ​ግ​ሉት ሴቶ​ችም ጋር እን​ደ​ሚ​ተኙ ሰማ።#“በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ ከሚ​ያ​ገ​ለ​ግሉ ሴቶች ጋር እን​ደ​ሚ​ተ​ኙም ሰማ” የሚ​ለው በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም። 23እር​ሱም አላ​ቸው፥ “ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕዝብ ሁሉ አፍ የም​ሰ​ማ​ውን ይህን ነገር ለምን ታደ​ር​ጋ​ላ​ችሁ? 24ልጆቼ ሆይ፥ ይህ አይ​ሆ​ንም፤ እኔ የም​ሰ​ማው ይህ ነገር መል​ካም አይ​ደ​ለ​ምና እን​ዲህ አታ​ድ​ርጉ። ሕዝ​ቡ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ከማ​ገ​ል​ገል አት​ከ​ል​ክ​ሉ​አ​ቸው። 25ሰውስ ሰውን ቢበ​ድል ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይጸ​ል​ዩ​ለ​ታል፤ ሰው ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቢበ​ድል ስለ እርሱ ወደ ማን ይጸ​ል​ዩ​ለ​ታል?” እነ​ርሱ ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሊያ​ጠ​ፋ​ቸው ወድ​ዶ​አ​ልና የአ​ባ​ታ​ቸ​ውን ቃል አል​ሰ​ሙም። 26ብላ​ቴ​ናው ሳሙ​ኤ​ልም አደገ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሰ​ውም ፊት ሞገስ እያ​ገኘ ሄደ።
በካ​ህኑ ቤተ ሰብ ላይ የተ​ነ​ገረ ትን​ቢት
27የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰው ወደ ዔሊ መጥቶ እን​ዲህ አለው፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ በግ​ብፅ በፈ​ር​ዖን ቤት ባሪ​ያ​ዎች ሳሉ ለአ​ባ​ትህ ቤት ተገ​ለ​ጥሁ፤ 28ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ነገድ ሁሉ ካህን ይሆ​ነኝ ዘንድ፥ በመ​ሠ​ዊ​ያ​ዬም ላይ ይሠዋ ዘንድ፥ ዕጣ​ን​ንም ያጥን ዘንድ፥ ኤፉ​ድ​ንም በፊቴ ይለ​ብስ ዘንድ፥ የአ​ባ​ት​ህን ቤት ለእኔ መረ​ጥ​ሁት፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ልጆች የእ​ሳት ቍር​ባን ሁሉ ስለ ምግብ ለአ​ባ​ትህ ቤት ሰጠሁ። 29በመ​ሥ​ዋ​ዕቴ ላይና በዕ​ጣኔ ላይ ስለ ምን በክፉ ዐይን ተመ​ለ​ከ​ትህ? የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች በፊቴ ከሚ​ያ​ቀ​ር​ቡት መሥ​ዋ​ዕት ሁሉ በቀ​ዳ​ም​ያቱ ስለ አከ​በ​ር​ሁህ ከእኔ ይልቅ ልጆ​ች​ህን ለምን መረ​ጥህ? 30ስለ​ዚ​ህም የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ በእ​ው​ነት ቤትህ፥ የአ​ባ​ት​ህም ቤት፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለም በፊቴ እን​ዲ​ኖር ተና​ግ​ሬ​አ​ለሁ፤ አሁን ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ያከ​በ​ሩ​ኝን አከ​ብ​ራ​ለ​ሁና፥ የና​ቁ​ኝም ይና​ቃ​ሉና ይህ አይ​ሆ​ን​ል​ኝም። 31እነሆ፥#ዕብ. “ለቤ​ትህ ሽማ​ግሌ እን​ዳ​ይ​ገኝ” የሚል ይጨ​ም​ራል። ዘር​ህ​ንም፥ የአ​ባ​ት​ህ​ንም ቤት ዘር የማ​ጠ​ፋ​በት ዘመን ይመ​ጣል፤ 32#ዕብ. “በእ​ስ​ራ​ኤል በረ​ከት በማ​ደ​ሪ​ያዬ ጠላ​ት​ህን ታያ​ለህ” የሚል ይጨ​ም​ራል።በቤ​ት​ህም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሽማ​ግሌ አይ​ገ​ኝም። 33በዐ​ይ​ኖቹ የሚ​ፈ​ጽም በነ​ፍ​ሱም የሚ​ተጋ ሰውን ከመ​ሠ​ዊ​ያዬ አላ​ጠ​ፋም።#ዕብ. “ከመ​ሠ​ዊ​ያዬ ያል​ተ​ቈ​ረጠ ልጅህ ቢገኝ ዐይ​ን​ህን ያፈ​ዝ​ዘ​ዋል ፤ ነፍ​ስ​ህ​ንም ያሳ​ዝ​ናል” ይላል። ከቤ​ትህ የሚ​ቀ​ሩት ሰዎች ሁሉ ግን በጐ​ል​ማ​ሶች#ዕብ. “በጐ​ል​ማ​ሳ​ነት ይሞ​ታሉ” ይላል። ሰይፍ ይሞ​ታሉ። 34ይህ በሁ​ለቱ ልጆ​ችህ በአ​ፍ​ኒ​ንና በፊ​ን​ሐስ ላይ የሚ​መጣ ለአ​ንተ ምል​ክት ነው፤ ሁለቱ በአ​ንድ ቀን በጦር ይሞ​ታሉ። 35የታ​መነ ካህን ለእኔ አስ​ነ​ሣ​ለሁ፤ በል​ቤም፥ በነ​ፍ​ሴም እን​ዳለ እን​ዲሁ ያደ​ር​ጋል፤ እኔም የታ​መነ ቤት እሠ​ራ​ለ​ታ​ለሁ፤ ዘመ​ኑን ሁሉ እኔ በቀ​ባ​ሁት ሰው ፊት ይሄ​ዳል። 36ከቤ​ት​ህም የቀ​ረው ሁሉ ይመ​ጣል፤ ከካ​ህ​ና​ትም ወደ አን​ዲቱ ዕጣ፥ እን​ጀራ ወደ​ም​በ​ላ​በት እባ​ክህ ላከኝ ብሎ ለአ​ንድ ብር መሐ​ልቅ ለቍ​ራሽ እን​ጀራ በፊቱ ይሰ​ግ​ዳል።”

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in