YouVersion Logo
Search Icon

መጽ​ሐፈ ሳሙ​ኤል ቀዳ​ማዊ 3

3
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሳ​ሙ​ኤል በራ​እይ እንደ ተገ​ለ​ጠ​ለት
1ብላ​ቴ​ናው ሳሙ​ኤ​ልም በዔሊ ፊት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያገ​ለ​ግል ነበር፤ በዚ​ያም ዘመን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ክቡር ነበረ፤ ራእ​ይም አይ​ገ​ለ​ጥም ነበር። 2በዚ​ያም ዘመን እን​ዲህ ሆነ፤ ዔሊም በስ​ፍ​ራው ተኝቶ ሳለ፥ ዐይ​ኖቹ መፍ​ዘዝ ጀም​ረው ነበር። ማየ​ትም አይ​ች​ልም ነበር። 3የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መብ​ራት ገና አል​ጠ​ፋም ነበር፤ ሳሙ​ኤ​ልም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቦት ባለ​በት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መቅ​ደስ ተኝቶ ነበር፤ 4እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሳሙ​ኤ​ልን፥ “ሳሙ​ኤል! ሳሙ​ኤል” ብሎ ጠራው፤ እር​ሱም፥ “እነ​ሆኝ” አለ። 5ወደ ዔሊም ሮጠ፥ “እነ​ሆኝ ስለ ጠራ​ኸኝ መጣሁ” አለው። እር​ሱም፥ “አል​ጠ​ራ​ሁ​ህም፤ ተመ​ል​ሰህ ተኛ” አለው። ሄዶም ተኛ። 6እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ደግሞ፥ “ሳሙ​ኤል! ሳሙ​ኤል” ብሎ ጠራው። ሳሙ​ኤ​ልም ተነ​ሥቶ ዳግ​መኛ ወደ ዔሊ ሄደና፥ “እነ​ሆኝ ስለ ጠራ​ኸኝ መጣሁ” አለ። እር​ሱም፥ “አል​ጠ​ራ​ሁ​ህም ተመ​ል​ሰህ ተኛ” አለው። 7ሳሙ​ኤል ግን ከዚህ በፊት ገና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አላ​ወ​ቀም ነበር፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ገና አል​ተ​ገ​ለ​ጠ​ለ​ትም ነበር። 8እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሳሙ​ኤ​ልን እንደ ገና ሦስ​ተኛ ጊዜ ጠራው። እር​ሱም ተነ​ሥቶ ወደ ዔሊ ሄደና፥ “እነ​ሆኝ ስለ ጠራ​ኸኝ መጣሁ” አለ። ዔሊም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጁን እንደ ጠራው አስ​ተ​ዋለ። 9ዔሊም ሳሙ​ኤ​ልን፥ “ልጄ፥ ሄደህ ተኛ፤ ቢጠ​ራ​ህም፦ አቤቱ፥ ባሪ​ያህ ይሰ​ማ​ልና ተና​ገር በለው፥” አለው። ሳሙ​ኤ​ልም ሄዶ በስ​ፍ​ራው ተኛ። 10እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መጥቶ ቆመ፤ እንደ ቀድ​ሞ​ውም ጠራው። ሳሙ​ኤ​ልም፥ “ባሪ​ያህ ይሰ​ማ​ልና ተና​ገር” አለ። 11እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሳሙ​ኤ​ልን አለው፥ “እነሆ የሰ​ማ​ውን ሁሉ ሁለ​ቱን ጆሮ​ዎ​ቹን ጭው የሚ​ያ​ደ​ርግ ነገ​ሬን በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ አደ​ር​ጋ​ለሁ። 12በዚ​ያም ቀን በቤቱ ላይ የተ​ና​ገ​ር​ሁ​ትን ሁሉ በዔሊ ላይ አጸ​ና​ለሁ፤ እኔም ጀምሬ እፈ​ጽ​ም​በ​ታ​ለሁ። 13ልጆቹ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ ክፉ እን​ዳ​ደ​ረጉ ዐውቆ አል​ገ​ሠ​ጻ​ቸ​ው​ምና ስለ ልጆቹ ኀጢ​አት ለዘ​ለ​ዓ​ለም ቤቱን እን​ደ​ም​በ​ቀል አስ​ታ​ው​ቄ​ዋ​ለሁ። 14ስለ​ዚ​ህም የዔሊ ቤት ኀጢ​አት በዕ​ጣ​ንና በመ​ሥ​ዋ​ዕት ለዘ​ለ​ዓ​ለም እን​ዳ​ይ​ሰ​ረ​ይ​ለት ለዔሊ ቤት ምያ​ለሁ።”
15ሳሙ​ኤ​ልም እስ​ኪ​ነጋ ተኛ፥ ማል​ዶም ተነ​ሥቶ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ደጅ ከፈተ። ሳሙ​ኤ​ልም ራእ​ዩን ለዔሊ መን​ገር ፈራ። 16ዔሊም ሳሙ​ኤ​ልን ጠርቶ፥ “ልጄ ሳሙ​ኤል ሆይ፥” አለ፤ እር​ሱም፥ “እነ​ሆኝ” አለ። 17እር​ሱም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የነ​ገ​ረህ ነገር ምን​ድን ነው? ከእኔ አት​ሸ​ሽግ፤ ከነ​ገ​ረ​ህና ከሰ​ማ​ኸው ነገር ሁሉ የሸ​ሸ​ግ​ኸኝ እንደ ሆነ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ያድ​ር​ግ​ብህ፤ እን​ዲ​ህም ይጨ​ም​ር​ብህ” አለው። 18ሳሙ​ኤ​ልም ነገ​ሩን ሁሉ ነገ​ረው፤ አን​ዳ​ችም አል​ሸ​ሸ​ገ​ውም። ዔሊም፥ “እርሱ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው፤ ደስ ያሰ​ኘ​ውን ያድ​ርግ” አለ።
19ሳሙ​ኤ​ልም አደገ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከእ​ርሱ ጋር ነበረ፤ ከቃ​ሉም አን​ዳች በም​ድር ላይ አይ​ወ​ድ​ቅም ነበር። 20እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ ከዳን እስከ ቤር​ሳ​ቤህ ድረስ ሳሙ​ኤል ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነቢይ ይሆን ዘንድ የታ​መነ እንደ ሆነ ዐወቀ። 21እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ደግሞ በሴሎ ተገ​ለጠ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሳ​ሙ​ኤል ይገ​ለ​ጥ​ለት ነበ​ርና።#ቀጣዩ በዕብ. የለም። ሳሙ​ኤ​ልም ከም​ድር ዳርቻ እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ በእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነቢይ እንደ ሆነ ታመነ። ዔሊም እጅግ አረጀ፥ ልጆቹ ግን በክ​ፋት ጸን​ተው ኖሩ፤ መን​ገ​ዳ​ቸ​ውም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉ ነበር።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in