YouVersion Logo
Search Icon

ኦሪት ዘዳ​ግም 34

34
የሙሴ መሞ​ትና መቀ​በር
1ሙሴም ከሞ​ዓብ ሜዳ በኢ​ያ​ሪኮ ፊት ለፊት ወዳ​ለው ወደ ናባው ተራራ ወደ ፈስጋ ራስ ወጣ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እስከ ዳን ድረስ ያለ​ውን የገ​ለ​ዓ​ድን ምድር አሳ​የው፤ 2የን​ፍ​ታ​ሌ​ም​ንም ምድር ሁሉ፥ የም​ና​ሴ​ንም ምድር ሁሉ፥ እስከ ምዕ​ራ​ብም ባሕር ድረስ ያለ​ውን የይ​ሁ​ዳን ምድር ሁሉ፤ 3ምድረ በዳ​ውን፥ የኢ​ያ​ሪ​ኮን ዙሪያ፥ እስከ ሴይር ዙሪያ ያለ​ው​ንም የፊ​ን​ቆ​ንን#“ፊኒ​ቆን” ዘን​ባባ ማለት ነው። ከተማ አሳ​የው፤ 4እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን፥ “ለዘ​ርህ እሰ​ጣ​ታ​ለሁ ብዬ ለአ​ብ​ር​ሃ​ምና ለይ​ስ​ሐቅ ለያ​ዕ​ቆ​ብም የማ​ል​ሁ​ላ​ቸው ምድር ይህች ናት፤ እነ​ሆም፥ በዐ​ይ​ንህ እን​ድ​ታ​ያት አደ​ረ​ግ​ሁህ፤ ነገር ግን ወደ​ዚ​ያች አት​ገ​ባም” አለው። 5የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አገ​ል​ጋይ ሙሴም እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል በዚያ በሞ​ዓብ ምድር ሞተ። 6በቤተ ፌጎ​ርም አቅ​ራ​ቢያ በና​ባው#ግሪክ ሰባ. ሊ. “በጋይ ምድር” ይላል። ምድር ቀበ​ሩት፤ እስከ ዛሬም ድረስ መቃ​ብ​ሩን ማንም የሚ​ያ​ውቅ የለም። 7ሙሴም በሞተ ጊዜ ዕድ​ሜዉ መቶ ሃያ ዓመት ነበረ፤ ዐይ​ኖ​ቹም አል​ፈ​ዘ​ዙም፤ ጕል​በ​ቱም አል​ደ​ከ​መም ነበር። 8የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በዮ​ር​ዳ​ኖስ በኢ​ያ​ሪኮ አቅ​ራ​ቢያ#“በዮ​ር​ዳ​ኖስ በኢ​ያ​ሪኮ አቅ​ራ​ቢያ” የሚ​ለው በዕብ. የለም። በሞ​ዓብ ሜዳ ሠላሳ ቀን ለሙሴ አለ​ቀ​ሱ​ለት፤ ለሙ​ሴም ያለ​ቀ​ሱ​ለት የል​ቅ​ሶው ወራት ተፈ​ጸመ።
9ሙሴም እጆ​ቹን ስለ ጫነ​በት የነዌ ልጅ ኢያሱ የጥ​በ​ብን መን​ፈስ ተሞላ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ታዘ​ዙ​ለት፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው አደ​ረጉ። 10እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ለፊት እንደ ተና​ገ​ረው#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “እን​ዳ​ወ​ቀው” ይላል። እንደ ሙሴ ያለ ነቢይ ከዚያ ወዲህ በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ አል​ተ​ነ​ሣም፤ 11በግ​ብፅ ምድር በፈ​ር​ዖ​ንና በሹ​ሞቹ ሁሉ ላይ፥ በም​ድ​ሪ​ቱም ሁሉ ላይ ምል​ክ​ት​ንና ድን​ቅን ያደ​ርግ ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ላከው ያለ፥ 12በእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ ፊት በታ​ላቅ ተአ​ምር ሁሉና በጸ​ናች እጅ፥ በተ​ዘ​ረ​ጋ​ችም ክንድ ሁሉ#“በተ​ዘ​ረ​ጋች ክንድ” የሚ​ለው በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም። እን​ዳ​ደ​ረ​ገው እንደ ሙሴ ያለ ነቢይ አል​ተ​ነ​ሣም።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in