YouVersion Logo
Search Icon

ወደ ገላ​ትያ ሰዎች 4

4
1ነገር ግን እላ​ለሁ፤ ወራሹ ሕፃን ሳለ ለሁሉ ጌታ ሲሆን ከአ​ገ​ል​ጋይ የሚ​ለይ አይ​ደ​ለም። 2ነገር ግን አባቱ እስከ ቀጠ​ረ​ለት ዕድሜ ድረስ በአ​ያት#ግሪኩ “በጠ​ባቂ ወይም በሞ​ግ​ዚት” ይላል። ወይም በሞ​ግ​ዚት እጅ ይጠ​በ​ቃል። 3እን​ዲሁ እኛም ሕፃ​ናት በነ​በ​ርን ጊዜ፥ ለዚህ ዓለም ስሕ​ተት ተገ​ዝ​ተን ነበር። 4ነገር ግን ቀጠ​ሮው#ግሪኩ “የዘ​መኑ ፍጻሜ” ይላል። በደ​ረሰ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጁን ላከ፤ ከሴ​ትም ተወ​ለደ፤ የኦ​ሪ​ት​ንም ሕግ ፈጸመ። 5#ሮሜ 8፥15-17። እኛ የል​ጅ​ነ​ትን ክብር እን​ድ​ና​ገኝ በኦ​ሪት የነ​በ​ሩ​ትን ይዋጅ ዘንድ። 6ልጆች እንደ መሆ​ና​ችሁ መጠን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አባ አባቴ ብላ​ችሁ የም​ት​ጠ​ሩ​ትን የል​ጁን መን​ፈስ በል​ባ​ችሁ አሳ​ደረ። 7እን​ኪ​ያስ እና​ንተ ልጆች ናችሁ እንጂ ባሮች አይ​ደ​ላ​ች​ሁም፤ ልጆች ከሆ​ና​ች​ሁም በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወራ​ሾች ናችሁ።
ወደ ጣዖ​ታት ስለ አለ​መ​መ​ለስ
8ነገር ግን ቀድሞ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ባለ​ማ​ወ​ቃ​ችሁ፥ በባ​ሕ​ር​ያ​ቸው አማ​ል​ክት ላል​ሆኑ ተገ​ዝ​ታ​ችሁ ነበር። 9ዛሬ ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ዐወ​ቃ​ች​ሁት፤ ይል​ቁ​ንም እርሱ ዐወ​ቃ​ችሁ፤ እንደ ገና ደግሞ ወደ​ዚያ ወደ ደካ​ማው፥ ወደ ድሀው ወደ​ዚህ ዓለም ጣዖት ተመ​ል​ሳ​ችሁ፥ ትገ​ዙ​ላ​ቸው ዘንድ እን​ዴት ፈጠ​ራን ትሻ​ላ​ችሁ? 10ዕለ​ት​ንና ወርን፥ ጊዜ​ንና ዓመ​ታ​ትን ትጠ​ብ​ቃ​ላ​ችሁ። 11ስለ እና​ንተ በከ​ንቱ ደክሜ እንደ ሆነ ብዬ እፈ​ራ​ች​ኋ​ለሁ። 12ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ እኔ ደግሞ እንደ እና​ንተ ሁኛ​ለሁ፤ እንደ እኔ ሁኑ ብዬ እማ​ል​ዳ​ች​ኋ​ለሁ፤ አን​ዳች አል​በ​ደ​ላ​ች​ሁ​ኝ​ምና። 13መጀ​መ​ሪያ ወን​ጌ​ልን በሰ​በ​ክ​ሁ​ላ​ችሁ ጊዜ፥ ከሥጋ ድካም የተ​ነሣ እንደ ነበር ታው​ቃ​ላ​ችሁ። 14መከራ እቀ​በል በነ​በ​ረ​በት ጊዜ አል​ሰ​ለ​ቻ​ች​ሁ​ኝም፤ እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አክ፥ እንደ ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስም ተቀ​በ​ላ​ች​ሁኝ እንጂ በሰ​ው​ነቴ አል​ና​ቃ​ች​ሁ​ኝም። 15አሁ​ንስ ደስ ማሰ​ኘ​ታ​ችሁ ወዴት አለ? ቢቻ​ላ​ች​ሁስ ዐይ​ና​ች​ሁ​ንም እንኳ ቢሆን አው​ጥ​ታ​ችሁ ትሰ​ጡኝ እንደ ነበረ፥ እኔ ምስ​ክ​ራ​ችሁ ነኝ። 16እው​ነ​ቱን ስለ ነገ​ር​ኋ​ችሁ ባላ​ጋራ ሆን​ኋ​ች​ሁን? 17እነ​ዚ​ያማ ይቀ​ኑ​ባ​ች​ኋል፤ ነገር ግን በእ​ነ​ርሱ ላይ እን​ድ​ት​ቀኑ ሊዘ​ጉ​አ​ችሁ ይወ​ዳሉ እንጂ ለመ​ል​ካም አይ​ደ​ለም። 18መቅ​ና​ትስ ዘወ​ትር ለመ​ል​ካም ሥራ ልት​ቀኑ ይገ​ባል፤ ነገር ግን እኔ ከእ​ና​ንተ ዘንድ ባለ​ሁ​በት ጊዜ ብቻ አይ​ደ​ለም። 19ልጆች፥ እንደ ገና የም​ጨ​ነ​ቅ​ላ​ችሁ ክር​ስ​ቶስ በል​ባ​ችሁ እስ​ኪ​ሣ​ል​ባ​ችሁ ድረስ ነው። 20ቃሌን ለውጬ አሁን በእ​ና​ንተ ዘንድ ልገኝ እሻ​ለሁ፤ ስለ እና​ንተ የም​ና​ገ​ረ​ውን አጣ​ለ​ሁና። 21በኦ​ሪት ሕግ እን​ኑር ትላ​ላ​ች​ሁን? ኦሪ​ትን አት​ሰ​ሙ​አ​ት​ምን? 22#ዘፍ. 16፥15፤ 21፥2። አብ​ር​ሃም ሁለት ልጆ​ችን አን​ዱን ከባ​ሪ​ያ​ዪቱ፥ አን​ዱ​ንም ከእ​መ​ቤ​ቲቱ እንደ ወለደ ተጽ​ፎ​አ​ልና። 23ነገር ግን ከባ​ሪ​ያ​ዪቱ የተ​ወ​ለ​ደው ልደቱ ልዩ ነው፤ በሰው ልማድ ተወ​ለደ፤ ከእ​መ​ቤ​ቲቱ የተ​ወ​ለ​ደው ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሰ​ጠው ተስፋ ተወ​ለደ። 24ይህም የሁ​ለቱ ሥር​ዐት ምሳሌ ነው፤ አን​ዲቱ ከደ​ብረ ሲና ለባ​ር​ነት ትወ​ል​ዳ​ለች፤ እር​ስ​ዋም አጋር ናት። 25አጋ​ርም በዐ​ረብ ሀገር ያለች ደብረ ሲና ናት፤ ከዛ​ሬ​ዪቱ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ጋር ትነ​ጻ​ጸ​ራ​ለች፤ ከል​ጆ​ችዋ ጋርም ትገ​ዛ​ለች። 26የላ​ይ​ኛ​ዪቱ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ግን በነ​ፃ​ነት የም​ት​ኖር ናት፤ እር​ስ​ዋም እና​ታ​ችን ናት። 27#ኢሳ. 54፥1። “የማ​ት​ወ​ልድ መካን ደስ ይላ​ታል፤ ምጥ የማ​ታ​ው​ቀ​ውም ደስ ብሎ​አት እልል ትላ​ለች፤ ባል ካላት ይልቅ የፈ​ቲቱ ልጆች ብዙ​ዎች ናቸ​ውና”#ግሪኩ “አንቺ የማ​ት​ወ​ልጂ መካን! ደስ ይበ​ልሽ፤ አንቺ አም​ጠሽ የማ​ታ​ውቂ እልል በዪና ጩኺ ...” ይላል የብ​ሉይ ኪዳን ግሪ​ክም እን​ደ​ዚሁ ነው። ተብሎ ተጽ​ፎ​አል። 28ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ እኛስ እንደ ይስ​ሐቅ የተ​ስፋ ልጆች ነን። 29#ዘፍ. 21፥9። ነገር ግን በሥጋ ልማድ የተ​ወ​ለ​ደው በመ​ን​ፈ​ሳዊ ግብር የተ​ወ​ለ​ደ​ውን በዚያ ጊዜ እን​ዳ​ሳ​ደ​ደው ዛሬም እን​ዲሁ ነው። 30#ዘፍ. 21፥10። ነገር ግን መጽ​ሐፍ ምን ይላል? “የባ​ሪ​ያ​ዪቱ ልጅ ከእ​መ​ቤ​ቲቱ ልጅ ጋር አይ​ወ​ር​ስ​ምና ባሪ​ያ​ዪ​ቱን ከል​ጅዋ ጋር አስ​ወ​ጥ​ተህ ስደ​ዳት” 31ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ አሁ​ንም እኛ የእ​መ​ቤ​ቲቱ ነን እንጂ የባ​ሪ​ያ​ዪቱ ልጆች አይ​ደ​ለ​ንም፤ ክር​ስ​ቶስ ነጻ አው​ጥ​ቶ​ና​ልና።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in