YouVersion Logo
Search Icon

መጽ​ሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ 3

3
እስ​ራ​ኤል የዮ​ር​ዳ​ኖ​ስን ወንዝ እንደ ተሻ​ገሩ
1ኢያ​ሱም ማልዶ ተነሣ፤ እር​ሱና እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ#“እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ” የሚ​ለው በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም። ከሰ​ጢም ተጕ​ዘው ወደ ዮር​ዳ​ኖስ መጡ፤ ሳይ​ሻ​ገ​ሩም በዚያ አደሩ። 2ከሦ​ስት ቀንም በኋላ ጸሓ​ፊ​ዎች በሰ​ፈሩ መካ​ከል ገቡ። 3ለሕ​ዝ​ቡም እን​ዲህ ብለው ዐወጁ፥ “የአ​ም​ላ​ካ​ች​ሁን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የቃል ኪዳ​ኑን ታቦት ሌዋ​ው​ያ​ንና ካህ​ናት ተሸ​ክ​መ​ውት ባያ​ችሁ ጊዜ፥ ከሰ​ፈ​ራ​ችሁ ተነ​ሥ​ታ​ችሁ ተከ​ተ​ሉት። 4በእ​ና​ን​ተና በታ​ቦቱ መካ​ከል ያለው ርቀት በስ​ፍር ሁለት ሺህ ክንድ ያህል ይሁን፤ በዚህ መን​ገድ በፊት አል​ሄ​ዳ​ች​ሁ​በ​ት​ምና የም​ት​ሄ​ዱ​በ​ትን መን​ገድ እን​ድ​ታ​ውቁ ወደ ታቦቱ አት​ቅ​ረቡ።”
5ኢያ​ሱም ሕዝ​ቡን፥ “ነገ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ ድንቅ ነገር ያደ​ር​ጋ​ልና ራሳ​ች​ሁን አንጹ” አለ። 6ኢያ​ሱም ካህ​ና​ቱን፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የቃል ኪዳ​ኑን ታቦት ተሸ​ክ​ማ​ችሁ በሕ​ዝቡ ፊት ሂዱ” ብሎ ተና​ገ​ራ​ቸው፤ ካህ​ና​ቱም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የቃል ኪዳ​ኑን ታቦት ተሸ​ክ​መው በሕ​ዝቡ ፊት ሄዱ።
7እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ኢያ​ሱን፥ “ከሙሴ ጋር እንደ ሆንሁ እን​ዲሁ ከአ​ንተ ጋር መሆ​ኔን ያውቁ ዘንድ በዚህ ቀን በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሁሉ ፊት ከፍ ከፍ አደ​ር​ግህ ዘንድ እጀ​ም​ራ​ለሁ። 8አሁ​ንም አንተ የቃል ኪዳ​ኑን ታቦት የሚ​ሸ​ከ​ሙ​ትን ካህ​ናት በዮ​ር​ዳ​ኖስ ውኃ ዳር ስት​ደ​ርሱ በዮ​ር​ዳ​ኖስ ውስጥ ቁሙ ብለህ እዘዝ” አለው።
9ኢያ​ሱም ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች፥ “ወደ​ዚህ ቀር​ባ​ችሁ የአ​ም​ላ​ካ​ች​ንን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ” አለ። 10ኢያ​ሱም አለ፥ “ሕያው አም​ላክ በመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ እንደ ሆነ፥ እር​ሱም ከፊ​ታ​ችሁ ከነ​ዓ​ና​ዊ​ውን፥ ኬጤ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም፥ ኤዌ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም፥ ፌር​ዜ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም፥ ጌር​ጌ​ሴ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም፥ አሞ​ሬ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም፥ ኢያ​ቡ​ሴ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም ፈጽሞ እን​ዲ​ያ​ጠ​ፋ​ቸው በዚህ ታው​ቃ​ላ​ችሁ። 11እነሆ፥ የም​ድር ሁሉ ጌታ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የቃል ኪዳኑ ታቦት በፊ​ታ​ችሁ ዮር​ዳ​ኖ​ስን ትሻ​ገ​ራ​ለች። 12አሁ​ንም ከእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ዶች ዐሥራ ሁለት ሰዎ​ችን ምረጡ፤ ከየ​ነ​ገዱ አንድ አንድ ሰው ይሁን። 13እን​ዲ​ህም ይሆ​ናል፤ የም​ድ​ርን ሁሉ ጌታ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦት የተ​ሸ​ከሙ ካህ​ናት እግር ጫማ በዮ​ር​ዳ​ኖስ ውኃ ውስጥ ሲቆም፥ የዮ​ር​ዳ​ኖስ ውኃ ይደ​ር​ቃል፤ ከላይ የሚ​ወ​ር​ደ​ውም ውኃ ይቆ​ማል።”
14እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ሕዝቡ ዮር​ዳ​ኖ​ስን ሊሻ​ገሩ ከየ​ድ​ን​ኳ​ና​ቸው በወጡ ጊዜ፥ የቃል ኪዳ​ኑን ታቦት የተ​ሸ​ከሙ ካህ​ናት በሕ​ዝቡ ፊት ይሄዱ ነበር። 15እንደ ክረ​ም​ትና እንደ መከር ወራት ሁሉ ዮር​ዳ​ኖስ እስከ ወሰኑ ሞልቶ ነበ​ርና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የቃል ኪዳን ታቦት ተሸ​ካ​ሚ​ዎቹ ወደ ዮር​ዳ​ኖስ በገቡ ጊዜ፥ ታቦ​ቱን የተ​ሸ​ከ​ሙት የካ​ህ​ናቱ እግ​ሮች በው​ኃዉ ዳር ሲጠ​ልቁ፥ 16ከላይ የሚ​ወ​ር​ደው ውኃ ቆመ፤ እስከ ቀር​ያ​ት​ያ​ርም አው​ራጃ እጅግ ርቆ እንደ ግድ​ግዳ ቆመ፤ ወደ ዓረባ ባሕር ወደ ጨው ባሕር የሚ​ወ​ር​ደው ውኃም ፈጽሞ ደረቀ፤ ሕዝ​ቡም በኢ​ያ​ሪኮ ፊት ለፊት ቆሙ። 17የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም የቃል ኪዳ​ኑን ታቦት የተ​ሸ​ከሙ ካህ​ናት በዮ​ር​ዳ​ኖስ መካ​ከል በደ​ረቅ መሬት ጸን​ተው ቆመው ነበር፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ ዮር​ዳ​ኖ​ስን ፈጽ​መው እስ​ኪ​ሻ​ገሩ ድረስ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሁሉ በደ​ረቅ መሬት ተሻ​ገሩ።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in