መዝሙረ ዳዊት 8
8
ለመዘምራን አለቃ በዋሽንት የዳዊት መዝሙር።
1አቤቱ ጌታችን፥ ስምህ በምድር ሁሉ እጅግ ተመሰገነ፥
ምስጋናህ በሰማዮች ላይ ከፍ ከፍ ብሎአልና።
2ከሕፃናትና ከሚጠቡ ልጆች አፍ ምስጋናን አዘጋጀህ፥
ስለ ጠላት፥#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ስለ ጠላትህ” ይላል።
ጠላትንና ግፈኛን ታጠፋው ዘንድ።
3የጣቶችህን ሥራ ሰማዮችን፥
አንተ የሠራሃቸውን፥ ጨረቃንና ከዋክብትን እናያለንና።
4ታስበው ዘንድ ሰው ምንድን ነው?
ትጐበኘውም ዘንድ የሰው ልጅ ምንድን ነው?
5ከመላእክት ጥቂት#ግሪክ ሰባ ሊ. “እጅግ ጥቂት” ይላል። አሳነስኸው፤
በክብርና በምስጋና ዘውድ ከለልኸው።
6በእጆችህም ሥራ ሁሉ ላይ ሾምኸው፤
ሁሉን ከእግሮቹ በታች አስገዛህለት፥
7በጎችንም በሬዎችንም ሁሉ፥
ደግሞም የምድረ በዳውን እንስሶች፥
8የሰማይንም ወፎች፥ የባሕርንም ዓሦች፥
በባሕር መንገድ የሚሄደውንም ሁሉ።
9አቤቱ፥ ጌታችን፥ ስምህ በምድር ሁሉ እጅግ ተመሰገነ።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 8: አማ2000
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in