መዝሙረ ዳዊት 9
9
ለመዘምራን አለቃ በሙት ላቤን የዳዊት መዝሙር።
1አቤቱ፥ በፍጹም ልቤ አመሰግንሃለሁ፥
ታምራትህንም ሁሉ እናገራለሁ።
2በአንተ ደስ ይለኛል፥ ሐሤትንም አደርጋለሁ፤
ልዑል ሆይ፥ ለስምህ እዘምራለሁ።
3ጠላቶቼ ወደ ኋላቸው በተመለሱ ጊዜ፥
ይታመሙ፥#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ይሰናከላሉ” ይላል። ከፊትህም ይጥፉ።#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ይጠፋሉ” ይላል።
4ፍርዴንና በቀሌን አድርገህልኛልና፤
የጽድቅ ፈራጅ ሆይ፥ በዙፋንህ ላይ ተቀመጥህ።
5አሕዛብን ገሠጽህ፥ ዝንጉዎችም ጠፉ፥#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ዝንጉዎችንም አጠፋህ” ይላል።
ስማቸውንም ለዘለዓለም ደመሰስህ።
6ጠላቶች በጦር ለዘለዓለም ጠፉ፥#ግሪክ ሰባ. ሊ. “የጠላት ሰይፎች ጠፉ” ይላል።
ከተሞቻቸውንም አፈረስህ፥
ዝክራቸውንም በአንድነት ታጠፋለህ።
7እግዚአብሔር ግን ለዘለዓለም ይኖራል፥
ዙፋኑንም ለመፍረድ አዘጋጀ፤
8እርሱም ዓለምን በጽድቅ ይዳኛታል።
አሕዛብንም በቅንነት ይዳኛቸዋል።
9እግዚአብሔርም ለድሆች መጠጊያ ሆናቸው፥
እርሱም በመከራቸው ጊዜ ረዳታቸው ነው።
10ስምህን የሚወዱ#ግሪክ ሰባ. ሊ. “የሚያውቁ” ይላል። ሁሉ በአንተ ይታመናሉ፥
አቤቱ፥ የሚሹህን አትተዋቸውምና።
11በጽዮን ለሚኖር ለእግዚአብሔር ዘምሩ፥
ለአሕዛብም ሥራውን ንገሩ፤
12ደማቸውን የሚመራመር እርሱ አስቦአልና፥
የድሆችንም ጩኸት አልረሳምና።
13አቤቱ፥ ይቅር በለኝ፥ ጠላቶቼም የሚያመጡብኝን መከራ እይ፥
ከሞት ደጆች ከፍ ከፍ የሚያደርገኝ፤#ግሪክ ሰባ. ሊ. “የምታደርገኝ” ይላል።
14ምስጋናውን ሁሉ እናገር ዘንድ፤
በጽዮን ልጅ በደጆችዋ፥
በማዳንህ ደስ ይለናል።#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ደስ ይለኛል” ይላል።
15አሕዛብ በሠሩት በደላቸው ጠፉ፥#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ባቀዱት ጥፋት ተያዙ” ይላል።
በዚያችም በሸሸጓት ወጥመድ እግራቸው ተጠመደ።
16እግዚአብሔር ፍርድን ማድረግ ያውቃል፤
ኀጢአተኛው በእጆቹ ሥራ ተጠመደ።
17ኀጢአተኞች ወደ ሲኦል ይመለሱ፥
እግዚአብሔርን የሚረሱ አሕዛብም ሁሉ።
18ድሃ ለዘለዓለም የሚረሳ አይደለምና፥
ችግረኞችም ተስፋቸውን ለዘለዓለም አያጡም።
19አቤቱ፥ ተነሥ፥ ሰውም አይበርታ፥
አሕዛብም በፊትህ ይፈረድባቸው።
20አቤቱ፥ የሕግ መምህርን#ዕብ. “ፍርሀትን ጫንባቸው” ይላል። በላያቸው ላይ ሹም፤
አሕዛብም ሰዎች እንደ ሆኑ ይወቁ።
21 # መዝ. 9 ቍ. 21 በዕብ. መዝ. 10 ቍ. 1 ነው። አቤቱ፥ ለምን ርቀህ ቆምህ?
በመከራም ጊዜ ለምን ቸል ትላለህ?
22በኀጢአተኛ ትዕቢት ድሃ ይናደዳል፤
ባሰቡት ተንኮላቸው ይጠመዳሉ።
23ኀጢአተኛ በነፍሱ ፈቃድ ይወደሳል፥
ዐመፀኛም ይባረካል።
24ኀጢአተኛ እግዚአብሔርን አበሳጨው፥
እንደ ቍጣውም ብዛት አይመራመረውም፤
በእርሱ ፊት እግዚአብሔር የለም።
25መንገዱ ሁሉ የረከሰ ነው፥
ፍርድህም በፊቱ የፈረሰ ነው፥
ጠላቶቹንም ሁሉ ይገዛቸዋል።
26በልቡ ይላል፥ “ለልጅ ልጅ አልታወክም
ክፉም አያገኘኝም።”
27አፉ መርገምንና ሽንገላን የተመላ ነው፤
ከምላሱ በታች ድካምና መከራ ነው።
28ከባለጸጎች ጋር ይሸምቃል፥ ያድድናልም
ንጹሑን በስውር ይገድል ዘንድ፥
ዐይኖቹም ወደ ድሃው ይመለከታሉ።
29እንደ አንበሳ በጕድጓድ#ግሪክ ሰባ. ሊ. “በችፍግ ዱር” ይላል። በስውር ይሸምቃል፤
ድሃውን ለመንጠቅ ያደባል፤
ድሃውን ይነጥቀዋል፥ ይስበዋልም።
30በወጥመዱም ያዋርደዋል፥
ይጐብጣል፥ ድሃውንም በገዛው ጊዜ ይወድቃል።
31በልቡም ይላል፥ “እግዚአብሔር ረስቶኛል፤
ፈጽሞም እንዳያይ ፊቱን መለሰ።”
32አቤቱ፥ አምላክ ሆይ፥ ተነሥ፥ እጅህም ከፍ ከፍ ትበል፤
ድሆችንም አትርሳ።
33ኀጢአተኛ ስለ ምን እግዚአብሔርን አስቈጣው?
በልቡ፥ “አይመራመረኝም” ይላልና።
34አንተ ድካምንና ቍጣን እንድትመለከት ታያለህን?
በእጅህ አሳልፈህ እንድትሰጠው፥
እንግዲህ ድሃ በአንተ ላይ ተጣለን?
ለድሃ አደግም ረዳቱ አንተ ነህ?
35የኀጢአተኛንና የክፉን ክንድ ስበር፥
ስለ እርሱም ኀጢአቱ ትመረመራለች፥ አትገኝምም።
36እግዚአብሔር ለዘለዓለም ይነግሣል፤
አሕዛብ ከምድር ይጠፋሉ።
37እግዚአብሔር የድሆችን ምኞት ሰማ፥
ጆሮውም የልባቸውን ዐሳብ አደመጠች፥
38ፍርዱ ለድሃ አደግና ለችግረኛ ይደረግ ዘንድ፥
ሰዎች በምድር ላይ አፋቸውን ከፍ ከፍ ማድረግን እንዳይደግሙ።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 9: አማ2000
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in