YouVersion Logo
Search Icon

መዝ​ሙረ ዳዊት 9

9
ለመ​ዘ​ም​ራን አለቃ በሙት ላቤን የዳ​ዊት መዝ​ሙር።
1አቤቱ፥ በፍ​ጹም ልቤ አመ​ሰ​ግ​ን​ሃ​ለሁ፥
ታም​ራ​ት​ህ​ንም ሁሉ እና​ገ​ራ​ለሁ።
2በአ​ንተ ደስ ይለ​ኛል፥ ሐሤ​ት​ንም አደ​ር​ጋ​ለሁ፤
ልዑል ሆይ፥ ለስ​ምህ እዘ​ም​ራ​ለሁ።
3ጠላ​ቶቼ ወደ ኋላ​ቸው በተ​መ​ለሱ ጊዜ፥
ይታ​መሙ፥#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ይሰ​ና​ከ​ላሉ” ይላል። ከፊ​ት​ህም ይጥፉ።#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ይጠ​ፋሉ” ይላል።
4ፍር​ዴ​ንና በቀ​ሌን አድ​ር​ገ​ህ​ል​ኛ​ልና፤
የጽ​ድቅ ፈራጅ ሆይ፥ በዙ​ፋ​ንህ ላይ ተቀ​መ​ጥህ።
5አሕ​ዛ​ብን ገሠ​ጽህ፥ ዝን​ጉ​ዎ​ችም ጠፉ፥#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ዝን​ጉ​ዎ​ች​ንም አጠ​ፋህ” ይላል።
ስማ​ቸ​ው​ንም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ደመ​ሰ​ስህ።
6ጠላ​ቶች በጦር ለዘ​ለ​ዓ​ለም ጠፉ፥#ግሪክ ሰባ. ሊ. “የጠ​ላት ሰይ​ፎች ጠፉ” ይላል።
ከተ​ሞ​ቻ​ቸ​ው​ንም አፈ​ረ​ስህ፥
ዝክ​ራ​ቸ​ው​ንም በአ​ን​ድ​ነት ታጠ​ፋ​ለህ።
7እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይኖ​ራል፥
ዙፋ​ኑ​ንም ለመ​ፍ​ረድ አዘ​ጋጀ፤
8እር​ሱም ዓለ​ምን በጽ​ድቅ ይዳ​ኛ​ታል።
አሕ​ዛ​ብ​ንም በቅ​ን​ነት ይዳ​ኛ​ቸ​ዋል።
9እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለድ​ሆች መጠ​ጊያ ሆና​ቸው፥
እር​ሱም በመ​ከ​ራ​ቸው ጊዜ ረዳ​ታ​ቸው ነው።
10ስም​ህን የሚ​ወዱ#ግሪክ ሰባ. ሊ. “የሚ​ያ​ውቁ” ይላል። ሁሉ በአ​ንተ ይታ​መ​ናሉ፥
አቤቱ፥ የሚ​ሹ​ህን አት​ተ​ዋ​ቸ​ው​ምና።
11በጽ​ዮን ለሚ​ኖር ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘምሩ፥
ለአ​ሕ​ዛ​ብም ሥራ​ውን ንገሩ፤
12ደማ​ቸ​ውን የሚ​መ​ራ​መር እርሱ አስ​ቦ​አ​ልና፥
የድ​ሆ​ች​ንም ጩኸት አል​ረ​ሳ​ምና።
13አቤቱ፥ ይቅር በለኝ፥ ጠላ​ቶቼም የሚ​ያ​መ​ጡ​ብ​ኝን መከራ እይ፥
ከሞት ደጆች ከፍ ከፍ የሚ​ያ​ደ​ር​ገኝ፤#ግሪክ ሰባ. ሊ. “የም​ታ​ደ​ር​ገኝ” ይላል።
14ምስ​ጋ​ና​ውን ሁሉ እና​ገር ዘንድ፤
በጽ​ዮን ልጅ በደ​ጆ​ችዋ፥
በማ​ዳ​ንህ ደስ ይለ​ናል።#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ደስ ይለ​ኛል” ይላል።
15አሕ​ዛብ በሠ​ሩት በደ​ላ​ቸው ጠፉ፥#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ባቀ​ዱት ጥፋት ተያዙ” ይላል።
በዚ​ያ​ችም በሸ​ሸ​ጓት ወጥ​መድ እግ​ራ​ቸው ተጠ​መደ።
16እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፍር​ድን ማድ​ረግ ያው​ቃል፤
ኀጢ​አ​ተ​ኛው በእ​ጆቹ ሥራ ተጠ​መደ።
17ኀጢ​አ​ተ​ኞች ወደ ሲኦል ይመ​ለሱ፥
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ረሱ አሕ​ዛ​ብም ሁሉ።
18ድሃ ለዘ​ለ​ዓ​ለም የሚ​ረሳ አይ​ደ​ለ​ምና፥
ችግ​ረ​ኞ​ችም ተስ​ፋ​ቸ​ውን ለዘ​ለ​ዓ​ለም አያ​ጡም።
19አቤቱ፥ ተነሥ፥ ሰውም አይ​በ​ርታ፥
አሕ​ዛ​ብም በፊ​ትህ ይፈ​ረ​ድ​ባ​ቸው።
20አቤቱ፥ የሕግ መም​ህ​ርን#ዕብ. “ፍር​ሀ​ትን ጫን​ባ​ቸው” ይላል። በላ​ያ​ቸው ላይ ሹም፤
አሕ​ዛ​ብም ሰዎች እንደ ሆኑ ይወቁ።
21 # መዝ. 9 ቍ. 21 በዕብ. መዝ. 10 ቍ. 1 ነው። አቤቱ፥ ለምን ርቀህ ቆምህ?
በመ​ከ​ራም ጊዜ ለምን ቸል ትላ​ለህ?
22በኀ​ጢ​አ​ተኛ ትዕ​ቢት ድሃ ይና​ደ​ዳል፤
ባሰ​ቡት ተን​ኮ​ላ​ቸው ይጠ​መ​ዳሉ።
23ኀጢ​አ​ተኛ በነ​ፍሱ ፈቃድ ይወ​ደ​ሳል፥
ዐመ​ፀ​ኛም ይባ​ረ​ካል።
24ኀጢ​አ​ተኛ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አበ​ሳ​ጨው፥
እንደ ቍጣ​ውም ብዛት አይ​መ​ራ​መ​ረ​ውም፤
በእ​ርሱ ፊት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የለም።
25መን​ገዱ ሁሉ የረ​ከሰ ነው፥
ፍር​ድ​ህም በፊቱ የፈ​ረሰ ነው፥
ጠላ​ቶ​ቹ​ንም ሁሉ ይገ​ዛ​ቸ​ዋል።
26በልቡ ይላል፥ “ለልጅ ልጅ አል​ታ​ወ​ክም
ክፉም አያ​ገ​ኘ​ኝም።”
27አፉ መር​ገ​ም​ንና ሽን​ገ​ላን የተ​መላ ነው፤
ከም​ላሱ በታች ድካ​ምና መከራ ነው።
28ከባ​ለ​ጸ​ጎች ጋር ይሸ​ም​ቃል፥ ያድ​ድ​ና​ልም
ንጹ​ሑን በስ​ውር ይገ​ድል ዘንድ፥
ዐይ​ኖ​ቹም ወደ ድሃው ይመ​ለ​ከ​ታሉ።
29እንደ አን​በሳ በጕ​ድ​ጓድ#ግሪክ ሰባ. ሊ. “በች​ፍግ ዱር” ይላል። በስ​ውር ይሸ​ም​ቃል፤
ድሃ​ውን ለመ​ን​ጠቅ ያደ​ባል፤
ድሃ​ውን ይነ​ጥ​ቀ​ዋል፥ ይስ​በ​ዋ​ልም።
30በወ​ጥ​መ​ዱም ያዋ​ር​ደ​ዋል፥
ይጐ​ብ​ጣል፥ ድሃ​ው​ንም በገ​ዛው ጊዜ ይወ​ድ​ቃል።
31በል​ቡም ይላል፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ረስ​ቶ​ኛል፤
ፈጽ​ሞም እን​ዳ​ያይ ፊቱን መለሰ።”
32አቤቱ፥ አም​ላክ ሆይ፥ ተነሥ፥ እጅ​ህም ከፍ ከፍ ትበል፤
ድሆ​ች​ንም አት​ርሳ።
33ኀጢ​አ​ተኛ ስለ ምን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አስ​ቈ​ጣው?
በልቡ፥ “አይ​መ​ራ​መ​ረ​ኝም” ይላ​ልና።
34አንተ ድካ​ም​ንና ቍጣን እን​ድ​ት​መ​ለ​ከት ታያ​ለ​ህን?
በእ​ጅህ አሳ​ል​ፈህ እን​ድ​ት​ሰ​ጠው፥
እን​ግ​ዲህ ድሃ በአ​ንተ ላይ ተጣ​ለን?
ለድሃ አደ​ግም ረዳቱ አንተ ነህ?
35የኀ​ጢ​አ​ተ​ኛ​ንና የክ​ፉን ክንድ ስበር፥
ስለ እር​ሱም ኀጢ​አቱ ትመ​ረ​መ​ራ​ለች፥ አት​ገ​ኝ​ምም።
36እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይነ​ግ​ሣል፤
አሕ​ዛብ ከም​ድር ይጠ​ፋሉ።
37እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የድ​ሆ​ችን ምኞት ሰማ፥
ጆሮ​ውም የል​ባ​ቸ​ውን ዐሳብ አደ​መ​ጠች፥
38ፍርዱ ለድሃ አደ​ግና ለች​ግ​ረኛ ይደ​ረግ ዘንድ፥
ሰዎች በም​ድር ላይ አፋ​ቸ​ውን ከፍ ከፍ ማድ​ረ​ግን እን​ዳ​ይ​ደ​ግሙ።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in