የሉ​ቃስ ወን​ጌል 18

18
ያለ መሰ​ል​ቸት ስለ መጸ​ለይ ምሳሌ
1ዘወ​ትር እን​ዲ​ጸ​ልዩ፥ እን​ዳ​ይ​ሰ​ለ​ቹም በም​ሳሌ ነገ​ራ​ቸው። 2እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “በአ​ን​ዲት ከተማ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የማ​ይ​ፈራ፥ ሰው​ንም የማ​ያ​ፍር አንድ ዳኛ ነበር። 3በዚ​ያ​ችም ከተማ አን​ዲት መበ​ለት ነበ​ረች፤ ዕለት ዕለ​ትም#“ዕለት ዕለ​ትም” የሚ​ለው በግ​ሪኩ እና በአ​ን​ዳ​ንድ የግ​እዝ ዘርዕ የለም። ወደ እርሱ እየ​መ​ጣች ከባ​ለ​ጋ​ራዬ ፍረ​ድ​ልኝ ትለው ነበር። 4እንቢ ብሎም አዘ​ገ​ያት። ከዚ​ህም በኋላ በልቡ ዐስቦ እን​ዲህ አለ፦ ‘ምንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ባል​ፈራ፥ ሰው​ንም ባላ​ፍር 5ይህቺ ሴት እን​ዳ​ት​ዘ​በ​ዝ​በኝ፥ ዘወ​ት​ርም እየ​መ​ጣች እን​ዳ​ታ​ታ​ክ​ተኝ እፈ​ር​ድ​ላ​ታ​ለሁ’።” 6ጌታ​ች​ንም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ዐመ​ፀ​ኛው ዳኛ ያለ​ውን ስሙ። 7እን​ግ​ዲህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በመ​ዓ​ል​ትና በሌ​ሊት ወደ እርሱ ለሚ​ጮኹ ለወ​ዳ​ጆቹ አይ​ፈ​ር​ድ​ምን? ወይስ ቸል ይላ​ቸ​ዋ​ልን? 8እላ​ች​ኋ​ለሁ ፈጥኖ ይፈ​ር​ድ​ላ​ቸ​ዋል፤ ነገር ግን የሰው ልጅ በመጣ ጊዜ በም​ድር ላይ እም​ነ​ትን ያገኝ ይሆን?”
ስለ ፈሪ​ሳ​ዊ​ዉና ስለ ቀራጩ
9ራሳ​ቸ​ውን ለሚ​ያ​መ​ጻ​ድ​ቁና ባል​ን​ጀ​ራ​ቸ​ውን ለሚ​ንቁ እን​ዲህ ብሎ መሰ​ለ​ላ​ቸው። 10“ሁለት ሰዎች ሊጸ​ልዩ ወደ ቤተ መቅ​ደስ ወጡ፤ አንዱ ፈሪ​ሳዊ፥ ሁለ​ተ​ኛ​ውም ቀራጭ ነበር። 11ፈሪ​ሳ​ዊ​ውም ቆመና እን​ዲህ ብሎ ጸለየ፦ ‘አቤቱ እንደ ሌሎች ሰዎች፥ እንደ ቀማ​ኞ​ችና እንደ ዐመ​ፀ​ኞች፥ እንደ አመ​ን​ዝ​ሮ​ችም፥ ወይም እን​ደ​ዚህ ቀራጭ ያላ​ደ​ረ​ግ​ኸኝ#በግ​ሪኩ “ስላ​ል​ሆ​ንሁ” ይላል። አመ​ሰ​ግ​ን​ሃ​ለሁ። 12እኔ በየ​ሳ​ም​ንቱ ሁለት ቀን እጾ​ማ​ለሁ፤ ከማ​ገ​ኘ​ውም ሁሉ ከዐ​ሥር አንድ እሰ​ጣ​ለሁ።’ 13ቀራጩ ግን ራቅ ብሎ ቆመ፤ ዐይ​ኖ​ቹ​ንም ወደ ላይ ወደ ሰማይ ሊያ​ነሣ አል​ወ​ደ​ደም፤ ደረ​ቱ​ንም እየ​መታ፦ ‘አቤቱ፥ እኔን ኀጢ​ኣ​ተ​ኛ​ውን ይቅር በለኝ’ አለ። 14#ማቴ. 23፥12፤ ሉቃ. 14፥11። እላ​ች​ኋ​ለሁ፥ ከዚያ ይልቅ ይህ ጻድቅ ሆኖ ወደ ቤቱ ተመ​ለሰ፤ ራሱን ከፍ ከፍ የሚ​ያ​ደ​ርግ ሁሉ ይዋ​ረ​ዳ​ልና፤ ራሱ​ንም የሚ​ያ​ዋ​ርድ ይከ​ብ​ራ​ልና።”
ጌታ​ችን ሕፃ​ና​ትን ስለ መባ​ረኩ
15ይባ​ር​ካ​ቸ​ውም ዘንድ ሕፃ​ና​ትን ወደ እርሱ አመ​ጡ​አ​ቸው፤ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም አይ​ተው ገሠ​ጹ​አ​ቸው። 16ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ጠራ​ቸው፤#በግ​ሪኩ “ሕፃ​ና​ትን ጠርቶ አለ” ይላል። እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “ሕፃ​ና​ትን ወደ እኔ ይመጡ ዘንድ ተዉ​አ​ቸው፥ አት​ከ​ል​ክ​ሉ​አ​ቸ​ውም፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥት እንደ እነ​ዚህ ላሉት ናትና። 17እው​ነት እላ​ች​ኋ​ለሁ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መን​ግ​ሥት እንደ ሕፃ​ናት ያል​ተ​ቀ​በ​ላት አይ​ገ​ባ​ባ​ትም።”
ስለ ሕይ​ወት ጥያቄ
18አንድ አለ​ቃም፥ “ቸር መም​ህር፥ ምን ሥራ ሠርቼ የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወ​ትን እወ​ር​ሳ​ለሁ?” አለው። 19ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እን​ዲህ አለው፥ “ለምን ቸር ትለ​ኛ​ለህ? ከአ​ንዱ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቀር ቸር የለም። 20#ዘፀ. 20፥12-16፤ ዘዳ. 5፥16-20። ትእ​ዛ​ዛ​ቱን አንተ ራስህ ታው​ቃ​ለህ፤ ‘አት​ግ​ደል፤ አታ​መ​ን​ዝር፤ አት​ስ​ረቅ፤ በሐ​ሰት አት​መ​ስ​ክር፤ አባ​ት​ህ​ንና እና​ት​ህ​ንም አክ​ብር።’ 21እር​ሱም፦ ‘ይህ​ንስ ሁሉ ከል​ጅ​ነቴ ጀምሬ እስከ ዛሬ ጠብ​ቄ​አ​ለሁ’።” አለው። 22ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ይህን ሰምቶ እን​ዲህ አለው፥ “አን​ዲት ቀር​ታ​ሃ​ለች፤ ሂድና ያለ​ህን ሁሉ ሸጠህ ለነ​ዳ​ያን ስጥ፤ በሰ​ማ​ይም መዝ​ገብ ታገ​ኛ​ለህ፤ መጥ​ተ​ህም ተከ​ተ​ለኝ።” 23እርሱ ግን ይህን ሰምቶ በጣም አዘነ፤ እርሱ እጅግ ባለ​ጸጋ ነበ​ርና። 24ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እጅግ ሲያ​ዝን አይቶ እን​ዲህ አለ፥ “ገን​ዘብ ላላ​ቸው ሰዎች ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥት መግ​ባት እን​ዴት ጭንቅ ነው! 25ባለ​ጸጋ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥት ከሚ​ገባ ይልቅ ግመል በመ​ርፌ ቀዳዳ ሊያ​ልፍ ይቀ​ላል።” 26የሰ​ሙ​ትም፥ “እን​ግ​ዲህ ማን ሊድን ይች​ላል?” አሉ። 27እርሱ ግን “በሰው ዘንድ የማ​ይ​ቻ​ለው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ይቻ​ላል” አላ​ቸው።
የጴ​ጥ​ሮስ ጥያቄ
28ጴጥ​ሮ​ስም፥ “እነሆ፥ እኛ ሁሉን ትተን ተከ​ት​ለ​ን​ሃል፤ እን​ግ​ዲህ ምን እና​ገ​ኛ​ለን?”#“እን​ግ​ዲህ ምን እና​ን​ገ​ኛ​ለን” የሚ​ለ​ውን ግሪኩ እና አን​ዳ​ንድ የግ​እዝ ዘርዕ አይ​ጽ​ፍም። አለው። 29እር​ሱም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እው​ነት እላ​ች​ኋ​ለሁ፥ ቤቱ​ንና ዘመ​ዶ​ቹን፥ ወን​ድ​ሞ​ቹ​ንና ሚስ​ቱን፥ ልጆ​ቹ​ንም ስለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥት የሚ​ተው፥ 30በዚህ ዓለም መቶ እጥፍ#በግ​ሪኩ እና በአ​ን​ዳ​ንድ የግ​እዝ ዘርዕ “ብዙ ዕጥፍ” ይላል። ዋጋ፥ በሚ​መ​ጣ​ውም ዓለም የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወ​ትን የማ​ይ​ቀ​በል ማንም የለም።”
ስለ ሕማ​ሙና ስለ ሞቱ
31ዐሥራ ሁለ​ቱ​ንም ወሰ​ዳ​ቸው፤ እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “እነሆ፥ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም እን​ወ​ጣ​ለን፤ በነ​ቢ​ያ​ትም የተ​ጻ​ፈው ሁሉ በሰው ልጅ ላይ ይፈ​ጸ​ማል። 32ለአ​ሕ​ዛብ አሳ​ል​ፈው ይሰ​ጡ​ታል፤ ይዘ​ብ​ቱ​በ​ታ​ልም፤ ይሰ​ድ​ቡ​ታ​ልም፤ ይተ​ፉ​በ​ታ​ልም። 33ይገ​ር​ፉ​ታል፤ ይገ​ድ​ሉ​ታ​ልም፤ በሦ​ስ​ተ​ኛ​ዪ​ቱም ቀን ይነ​ሣል።” 34እነ​ርሱ ግን፤ ከተ​ና​ገ​ራ​ቸው ያስ​ተ​ዋ​ሉት የለም፤ ይህ ነገር ከእ​ነ​ርሱ የተ​ሰ​ወረ ነበ​ርና፤ የተ​ና​ገ​ረ​ው​ንም አያ​ው​ቁም ነበ​ርና።
በኢ​ያ​ሪኮ ስለ ነበ​ረው ዕውር
35ከዚ​ህም በኋላ ኢያ​ሪኮ በደ​ረሱ ጊዜ አንድ ዕውር በጎ​ዳና ተቀ​ምጦ ይለ​ምን ነበር። 36የሚ​ያ​ል​ፈ​ው​ንም ሰው ድምፅ ሰምቶ፥ “ይህ የም​ሰ​ማው ምን​ድን ነው?” አለ። 37እነ​ር​ሱም፥ “የና​ዝ​ሬቱ ኢየ​ሱስ ያል​ፋል” ብለው ነገ​ሩት። 38ድም​ፁ​ንም ከፍ አድ​ርጎ፥ “የዳ​ዊት ልጅ ኢየ​ሱስ ሆይ፥ ማረኝ” አለ። 39የሚ​መ​ሩ​ትም ዝም እን​ዲል ገሠ​ጹት፤ እርሱ ግን በጣም ጮኾ፥ “የዳ​ዊት ልጅ ሆይ፥ ማረኝ” አለ። 40ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ቆመና ወደ እርሱ እን​ዲ​ያ​መ​ጡት አዘዘ። 41ወደ እር​ሱም በደ​ረሰ ጊዜ፥ “ምን ላደ​ር​ግ​ልህ ትወ​ዳ​ለህ?” ብሎ ጠየ​ቀው፤ እር​ሱም፥ “ጌታ ሆይ፥ ዐይ​ኖች እን​ዲ​ያዩ ነው” አለው። 42ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “እይ፤ እም​ነ​ትህ አዳ​ነ​ችህ” አለው። 43በዚ​ያን ጊዜም አየ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም አመ​ሰ​ገነ፤ ተከ​ተ​ለ​ውም፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ አይ​ተው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ሰ​ገ​ኑት።

اکنون انتخاب شده:

የሉ​ቃስ ወን​ጌል 18: አማ2000

های‌لایت

به اشتراک گذاشتن

کپی

None

می خواهید نکات برجسته خود را در همه دستگاه های خود ذخیره کنید؟ برای ورودثبت نام کنید یا اگر ثبت نام کرده اید وارد شوید