1
ዘፍጥረት 41:16
አዲሱ መደበኛ ትርጒም
ዮሴፍም ፈርዖንን፣ “እኔ የመተርጐም ችሎታ የለኝም፤ ነገር ግን እግዚአብሔር (ኤሎሂም) ለፈርዖን የሚሻውን ትርጕም ይሰጠዋል” አለው።
Paghambingin
I-explore ዘፍጥረት 41:16
2
ዘፍጥረት 41:38
ፈርዖንም፣ “የእግዚአብሔር (ኤሎሂም) መንፈስ ያለበት እንደዚህ ያለ ሰው ማንን ልናገኝ እንችላለን?” ብሎ ጠየቃቸው።
I-explore ዘፍጥረት 41:38
3
ዘፍጥረት 41:39-40
ፈርዖን ዮሴፍን እንዲህ አለው፤ “እግዚአብሔር (ኤሎሂም) ይህን ሁሉ ስለ ገለጠልህ፣ እንደ አንተ ያለ አስተዋይና ብልኅ ሰው የለም። አንተ በቤተ መንግሥቴ የበላይ ትሆናለህ፤ ሕዝቤም ሁሉ ለሥልጣንህ ይገዛል፤ እኔ ከአንተ የምበልጠው በዙፋኔ ብቻ ይሆናል።”
I-explore ዘፍጥረት 41:39-40
4
ዘፍጥረት 41:52
እንደዚሁም፣ “መከራ በተቀበልሁበት ምድር እግዚአብሔር (ኤሎሂም) ፍሬያማ አደረገኝ” ሲል ሁለተኛ ልጁን ኤፍሬም አለው።
I-explore ዘፍጥረት 41:52
5
ዘፍጥረት 41:51
ዮሴፍም፣ “እግዚአብሔር (ኤሎሂም) መከራዬን ሁሉ፣ የአባቴንም ቤት እንድረሳ አድርጎኛል” በማለት የመጀመሪያ ልጁን ስም ምናሴ አለው።
I-explore ዘፍጥረት 41:51
Home
Biblia
Mga Gabay
Mga Palabas