Logo ng YouVersion
Hanapin ang Icon

ዘፀአት 1

1
እስራኤላውያን በጭቈና ሥር
1ቤተ ሰቦቻቸውን ይዘው ከያዕቆብ ጋር ወደ ግብፅ የሄዱት የእስራኤል ልጆች ስሞች እነዚህ ናቸው፦
2ሮቤል፣ ስምዖን፣ ሌዊ፣ ይሁዳ፣
3ይሳኮር፣ ዛብሎን፣ ብንያም፣
4ዳን፣ ንፍታሌም፣
ጋድና አሴር።
5የያዕቆብ ዘር ጠቅላላ ብዛት ሰባ#1፥5 የማሶሬቱ ቅጅ (ዘፍ 46፥27 ይመ)፣ የሙት ባሕር ጥቅልል እንዲሁም የሰብዓ ሊቃናት ትርጕም (ሐሥ 7፥14 እና የዘፍ 46፥27 ማብ ይመ)፣ ሰባ አምስት ይላሉ። ሲሆን፣ ዮሴፍ ግን ቀደም ብሎ በግብፅ ነበረ።
6ከጊዜ በኋላ ዮሴፍና ወንድሞቹ ያም ትውልድ በሙሉ ሞቱ፤ 7ይሁን እንጂ እስራኤላውያን እየተዋለዱ በዙ፤ ቍጥራቸው እጅግ ከመጨመሩም የተነሣ የግብፅን ምድር ሞሏት።
8በግብፅም፣ ስለ ዮሴፍ የማያውቅ አዲስ ንጉሥ ነገሠ። 9እርሱም ሕዝቡን እንዲህ አላቸው፤ “እነሆ፤ እስራኤላውያን በቍጥር በልጠውናል፤ ከእኛም ይልቅ እየበረቱ ነው፤ 10ቍጥራቸው እንዳይጨምር፣ ጦርነት ቢነሣ ከጠላቶቻችን ጋር አብረው እንዳይወጉንና ከምድሪቱም ኰብልለው እንዳይሄዱ ዘዴ እንፈልግ።”
11ስለዚህ እያስጨነቁ የግዳጅ ሥራ የሚያሠሯቸውን አሠሪ አለቆች ሾሙባቸው። እስራኤላውያንም ፊቶምና ራምሴ የተባሉ ንብረት ማከማቻ ከተሞችን ለፈርዖን ሠሩለት። 12ነገር ግን ባስጨነቋቸው መጠን የእስራኤላውያን ቍጥር በዛ፤ በምድሪቱም እየተስፋፉ ሄዱ፤ ከዚህም የተነሣ ግብፃውያኑ እስራኤላውያንን እጅግ ፈሯቸው፤ 13ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታም ያሠሯቸው ጀመር። 14ጭቃ በማስቦካት፣ ጡብ በማሠራትና በእርሻም ሁሉ እያስጨነቁ ከባድ ሥራ እንዲሠሩ በማድረግ ሕይወታቸውን አስመረሩ፤ ግብፃውያኑ በሚያሠሯቸው ከባድ ሥራ ሁሉ ፈጽሞ አይራሩላቸውም ነበር።
15የግብፅም ንጉሥ ሲፓራና ፉሐ የተባሉትን ዕብራውያን ሴቶች አዋላጆች እንዲህ አላቸው፤ 16“የዕብራውያንን ሴቶች በማማጫው ድንጋይ ላይ በምታዋልዱበት ጊዜ የሚወለደው ሕፃን ወንድ ከሆነ ግደሉት፤ ሴት ከሆነች ግን በሕይወት ትኑር።” 17አዋላጆቹ ግን እግዚአብሔርን (ኤሎሂም) ስለ ፈሩ የግብፅ ንጉሥ ያዘዛቸውን አልፈጸሙም፤ ወንዶቹንም ልጆች በሕይወት እንዲኖሩ ተዉአቸው። 18ንጉሡም አዋላጆቹን ጠርቶ፣ “ለምንድን ነው ወንዶቹን ልጆች በሕይወት እንዲኖሩ የተዋችኋቸው?” አላቸው።
19እነርሱም፣ “የዕብራውያን ሴቶች እንደ ግብፃውያን ሴቶች አይደሉም፤ ብርቱዎች ስለሆኑ አዋላጆች ከመድረሳቸው በፊት ይወልዳሉ” ሲሉ ለፈርዖን መለሱለት።
20ከዚህም የተነሣ እግዚአብሔር (ኤሎሂም) ለአዋላጆቹ መልካም ሆነላቸው፤ ሕዝቡም በቍጥር እየበዛና እያየለ ሄደ። 21አዋላጆቹም እግዚአብሔርን (ኤሎሂም) በመፍራታቸው ቤተ ሰብ ሰጣቸው።
22ፈርዖንም፣ “የሚወለደውን ወንድ ልጅ#1፥22 የማሶሬቱ ቅጅ፣ ኦሪተ ሳምራውያን፣ የሰብዓ ሊቃናት ትርጕም እንዲሁም ታርጕም ከዕብራውያን የሚወለደውን ይላሉ። ሁሉ አባይ ወንዝ ውስጥ ጣሉት፤ ሴት ልጅ ሁሉ ግን በሕይወት ትኑር” ሲል ሕዝቡን አዘዘ።

Kasalukuyang Napili:

ዘፀአት 1: NASV

Haylayt

Ibahagi

Kopyahin

None

Gusto mo bang ma-save ang iyong mga hinaylayt sa lahat ng iyong device? Mag-sign up o mag-sign in