ዘፍጥረት 36
36
የዔሳው ዝርያዎች
36፥10-14 ተጓ ምብ – 1ዜና 1፥35-37
36፥20-28 ተጓ ምብ – 1ዜና 1፥38-42
1ኤዶም የተባለው የዔሳው ትውልድ ይህ ነው፦
2ዔሳው ከከነዓን ሴቶች አገባ፤ እነርሱም፦ የኬጢያዊው የዔሎን ልጅ ዓዳን፣ የኤዊያዊው የፅብዖን ልጅ ዓና የወለዳት አህሊባማ፣ 3እንዲሁም የነባዮት እኅት የሆነችው የእስማኤል ልጅ ቤሴሞት ነበሩ።
4ዓዳ ለዔሳው ኤልፋዝን ወለደችለት፤ ቤሴሞት ደግሞ ራጉኤልን ወለደችለት። 5እንደዚሁም አህሊባማ የዑስን፣ የዕላምንና ቆሬን ወለደችለት፤ እነዚህ ዔሳው በከነዓን አገር የወለዳቸው ልጆች ናቸው።
6ዔሳው ሚስቶቹን፣ ወንዶችና ሴቶች ልጆቹን፣ ቤተ ሰቦቹን በሙሉ እንደዚሁም የቀንድ ከብቶቹንና ሌሎቹንም እንስሳት ሁሉ በከነዓን ምድር ያፈራውን ሀብት እንዳለ ይዞ ከወንድሙ ከያዕቆብ ራቅ ወዳለ ቦታ ሄደ። 7ብዙ ሀብት ስለ ነበራቸው አብረው መኖር አልቻሉም፤ የነበሩበትም ስፍራ ከከብቶቻቸው ብዛት የተነሣ ሊበቃቸው አልቻለም። 8ስለዚህ ኤዶም የተባለው ዔሳው መኖሪያውን በተራራማው አገር በሴይር አደረገ።
9በሴይር ተራራማ አገር የሚኖሩ የኤዶማውያን አባት፣ የዔሳው ዝርያዎች እነዚህ ናቸው፤
10የዔሳው ልጆች ስም፦
የዔሳው ሚስት የዓዳ ልጅ ኤልፋዝና የዔሳው ሚስት የቤሴሞት ልጅ ራጉኤል፤
11የኤልፋዝ ልጆች፦
ቴማን፣ ኦማር፣ ስፎ፣ ጎቶምና ቄኔዝ፤ 12የዔሳው ልጅ ኤልፋዝ ትምናዕ የምትባል ቁባት ነበረችው፤ እርሷም አማሌቅን ወለደችለት፤ የዔሳው ሚስት የዓዳ የልጅ ልጆች እነዚህ ናቸው።
13የራጉኤል ልጆች፦
ናሖት፣ ዛራ፣ ሣማና ሚዛህ፤ እነዚህ ደግሞ የዔሳው ሚስት የቤሴሞት የልጅ ልጆች ናቸው።
14የፅብዖን የልጅ ልጅ፣ የዓና ልጅ የዔሳው ሚስት አህሊባማ ለዔሳው የወለደቻቸው ልጆች፦
የዑስ፣ የዕላማና ቆሬ።
15ከዔሳው ዝርያዎች እነዚህ የነገድ አለቆች ነበሩ፤
የዔሳው የበኵር ልጅ የኤልፋዝ ልጆች፦
አለቃ ቴማን፣ አለቃ ኦማር፣ አለቃ ስፎ፣ አለቃ ቄኔዝ፣ 16አለቃ ቆሬ፣#36፥16 ከማሶሬቲኩ ጽሑፍ ጋር ተመሳሳይ ሲሆን በኦሪተ ሳምራውያን ግን (በተጨማሪ ዘፍ 36፥11 እና 1ዜና 1፥36 ይመ) ውስጥ “ቆሬ” የሚለው ቃል የለም። አለቃ ጎቶምና አለቃ አማሌቅ፤ እነዚህ በኤዶም ምድር ከኤልፋዝ የተገኙ የነገድ አለቆች፣ የዓዳ የልጅ ልጆች ነበሩ።
17የዔሳው ልጅ ራጉኤል ልጆች፦
አለቃ ናሖት፣ አለቃ ዛራ፣ አለቃ ሣማና አለቃ ሚዛህ፤ እነዚህ በኤዶም ምድር ከራጉኤል የተገኙ የነገድ አለቆች፣ የዔሳው ሚስት የቤሴሞት የልጅ ልጅ ነበሩ።
18የዔሳው ሚስት የአህሊባም ልጆች፦
አለቃ የዑስ፣ አለቃ የዕላማና፣ አለቃ ቆሬ፤ እነዚህ ከዓና ልጅ፣ ከዔሳው ሚስት ከአህሊባማ የተገኙ የነገድ አለቆች ነበሩ።
19እነዚህም ኤዶም የተባለው የዔሳው ልጆችና የነገድ አለቆቻቸው ነበሩ።
20በዚያች ምድር ይኖሩ የነበሩ የሖሪው የሴይር ልጆች እነዚህ ነበሩ፦
ሎጣን፣ ሦባል፣ ፅብዖን፣ ዓና፣ 21ዲሶን፣ ኤጽርና ዲሳን፤ እነዚህ በኤዶም የነበረው የሴይር ልጆች፣ የሖሪውያን የነገድ አለቆች ነበሩ።
22የሎጣን ልጆች፦
ሖሪና ሔማም#36፥22 ሔማም የሚለው የዕብራይስጥ ቃል ሖማም ለሚለው ቃል አማራጭ ትርጕም ነው (1ዜና 1፥39 ይመ)።፤ የሎጣንም እኅት ቲምናዕ ትባል ነበር።
23የሦባል ልጆች፦
ዓልዋን፣ ማኔሐት፣ ዔባል፣ ስፎና አውናም፤
24የፅብዖን ልጆች፦
አያና ዓና፤ ይህ ዓና የአባቱን የፅብዖንን አህዮች ሲጠብቅ፣ የፍል ውሃ ምንጮችን#36፥24 ከቩልጌት ጋር ተመሳሳይ ሲሆን ሱርስቱ ግን የተገኘ ውሃ ይለዋል፤ በዕብራይስጥ የዚህ ቃል ትርጕም አይታወቅም። በምድረ በዳ ያገኘ ሰው ነው።
25የዓና ልጆች፦
ዲሶንና የዓና ሴት ልጅ አህሊባማ፤
26የዲሶን#36፥26 በዕብራይስጥ ዲሳን፣ የዲሶን አማራጭ ትርጕም ነው። ልጆች፦
ሔምዳን፣ ኤስባን፣ ይትራንና ክራን፤
27የኤጽር ልጆች፦
ቢልሐን፣ ዛዕዋንና ዓቃን፤
28የዲሳን ልጆች፦
ዑፅና አራን።
29የሖሪውያን የነገድ አለቆች እነዚህ ነበሩ፦
ሎጣን፣ ሦባል፣ ፅብዖን፣ ዓና፣ 30ዲሶን፣ ኤጽርና ዲሳን፤ እነዚህ በሴይር ምድር እንደየነገዳቸው የሖሪውያን የነገድ አለቆች ነበሩ።
የኤዶም ነገሥታት
36፥31-43 ተጓ ምብ – 1ዜና 1፥43-54
31ንጉሥ በእስራኤል ከመንገሡ በፊት፣#36፥31 ወይም እስራኤላዊ መንግሥት በእነርሱ ላይ ከመንገሡ በፊት በኤዶም የነገሡ ነገሥታት እነዚህ ነበሩ፦
32የቢዖር ልጅ ባላቅ በኤዶም ነበር፤ የከተማውም ስም ዲንሃባ ይባል ነበር።
33ባላቅ ሲሞት፣ የባሶራው የዛራ ልጅ ኢዮባብ በምትኩ ነገሠ።
34ኢዮባብ ሲሞት፣ የቴማኒው ሑሳም በምትኩ ነገሠ።
35ሑሳም ሲሞት፣ የምድያምን ሰዎች በሞዓብ ምድር ድል ያደረጋቸው የባዳድ ልጅ ሃዳድ በምትኩ ነገሠ፤ የከተማውም ስም ዓዊት ይባል ነበር።
36ሃዳድ ሲሞት፣ የመሥሬቃው ሠምላ በምትኩ ነገሠ።
37ሠምላ ሲሞት፣ በወንዙ#36፥37 የኤፍራጥስ ወንዝ ሊሆን ይችላል። አጠገብ ያለው የርሆቦቱ ሳኦል በምትኩ ነገሠ።
38ሳኦል ሲሞት፣ የዓክቦር ልጅ በኣልሐናን በምትኩ ነገሠ።
39የዓክቦር ልጅ በኣልሐናን ሲሞት፣ ሃዳር በምትኩ ነገሠ፤ የከተማውም ስም ፋዑ ይባል ነበር፤ የሚስቱም ስም መሄጣብኤል ሲሆን፣ እርሷም የሜዛሃብ ልጅ መጥሬድ የወለደቻት ነበረች።
40ከዔሳው የተገኙት የነገድ አለቆች ስም፣ እንደየነገዳቸውና እንደየአገራቸው ይህ ነው፦
ቲምናዕ፣ ዓልዋ፣ የቴት፣
41አህሊባማ፣ ኤላ፣ ፊኖን፣
42ቄኔዝ፣ ቴማን፣ ሚብሳር፣
43መግዲኤልና ዒራም።
እነዚህ፣ በያዙት ምድር እንደየይዞታቸው ከኤዶም የተገኙ የነገድ አለቆች ነበሩ።
ይህም ዔሳው፣ የኤዶማውያን አባት ነው።
Kasalukuyang Napili:
ዘፍጥረት 36: NASV
Haylayt
Ibahagi
Kopyahin
Gusto mo bang ma-save ang iyong mga hinaylayt sa lahat ng iyong device? Mag-sign up o mag-sign in
መጽሐፍ ቅዱስ፣ አዲሱ መደበኛ ትርጕም™
የቅጅ መብት © 2001 በ Biblica, Inc.
ፈቃድ የተገኘባቸው ናቸው። መብቱ በመላው ዓለም በሕግ የተጠበቀ።
Holy Bible, New Amharic Standard Version™ (Addisu Medebegna Tirgum™)
Copyright © 2001 by Biblica, Inc.
Used with permission. All rights reserved worldwide.