1
ኦሪት ዘፍጥረት 42:21
መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
እርስ በርሳቸውም፥ “ይኸው በወንድማችን ላይ ባደረስነው በደል ምክንያት ቅጣታችንን እየተቀበልን ነው። እርሱ እንደዚያ ተጨንቆ ስለ ሕይወቱ ሲማጠነን፥ እኛ አልሰማነውም ነበር፤ ይህ መከራ የደረሰብንም በዚሁ ምክንያት ነው” ተባባሉ።
موازنہ
تلاش ኦሪት ዘፍጥረት 42:21
2
ኦሪት ዘፍጥረት 42:6
በዚህ ጊዜ ዮሴፍ የምድሪቱ ገዥ ነበር፤ ለአገሩ ሰዎች ሁሉ እህል የሚሸጥላቸው እርሱ ነበር። የዮሴፍ ወንድሞችም እንደ ደረሱ፥ ከፊቱ ቀርበው ወደ ምድር ለጥ ብለው እጅ ነሡት።
تلاش ኦሪት ዘፍጥረት 42:6
3
ኦሪት ዘፍጥረት 42:7
ዮሴፍም ወንድሞቹን ገና ሲያያቸው ወዲያውኑ ዐወቃቸው፤ ነገር ግን እንደማያውቃቸው ሆኖ፥ “ከየት የመጣችሁ ናችሁ?” ብሎ በቁጣ ቃል ተናገራቸው። እነርሱም፥ “እህል፤ ለመሸመት ከከነዓን ምድር የመጣን ነን” ብለው መለሱለት።
تلاش ኦሪት ዘፍጥረት 42:7
صفحہ اول
بائبل
مطالعاتی منصوبہ
Videos