YouVersion Logo
تلاش

ዘፍጥረት 2

2
1የሰማያትና የምድር፣ በውስጣቸውም ያሉት ሁሉ አፈጣጠር በዚህ ሁኔታ ተከናወነ።
2እግዚአብሔር ይሠራ የነበረውን ሥራውን በሰባተኛው ቀን ላይ ፈጽሞ ነበር፤ ስለዚህ ይሠራ ከነበረው ሥራው ሁሉ በሰባተኛው ቀን ዐረፈ።#2፥2 ወይም አቆመ፤ በ 3 ላይም እንዲሁ፤ 3እግዚአብሔር ሰባተኛውን ቀን ባረከው፤ ቀደሰውም፤ ካከናወነው የመፍጠር ሥራው ሁሉ ያረፈው በሰባተኛው ቀን ነውና።
አዳምና ሔዋን
4 እግዚአብሔር አምላክ ሰማያትንና ምድርን በፈጠረ ጊዜ የተከናወኑት እንደዚህ ነበረ፤ እግዚአብሔር አምላክ ሰማያትንና ምድርን ሲፈጥር፣ 5የሜዳ ቡቃያ ገና በምድር#2፥5 ወይም መሬት፤ በ 6 ላይም እንዲሁ ላይ አልታየም፤ የሜዳ ተክልም ገና አልበቀለም፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር አምላክ በመሬት ላይ ገና ዝናብ አላዘነበም ነበር፤ ምድርንም የሚያለማ ሰው አልነበረም። 6ነገር ግን ውሃ#2፥6 ወይም ጭጋግ ከመሬት እየመነጨ የምድርን ገጽ ያረሰርስ ነበር። 7እግዚአብሔር አምላክ ከምድር ዐፈር ወስዶ ሰውን#2፥7 በዕብራይስጥ ሰው (አዳም) የሚለው ቃል፣ ምድር (አዳማኽ) ከሚለው ቃል ጋራ በድምፅ ይመሳሰላል፤ በፍችም ሳይዛመድ አይቀርም፤ አዳም የመጀመሪያው ሰው ስምም ነው፤ 20 ይመ። አበጀው፤ በአፍንጫውም የሕይወት እስትንፋስ እፍ አለበት፤ ሰውም ሕያው ነፍስ ሆነ።
8 እግዚአብሔር አምላክ በምሥራቅ፣ በዔድን የአትክልት ስፍራ አዘጋጀ፤ ያበጀውንም ሰው በዚያ አኖረው። 9እግዚአብሔር አምላክም ለዐይን የሚያስደስት ለመብልም መልካም የሆነውን ዛፍ ሁሉ ከምድር አበቀለ፤ በአትክልቱ ቦታ መካከልም የሕይወት ዛፍ ነበረ፤ እንዲሁም መልካምና ክፉን መለየት የሚያስችለው የዕውቀት ዛፍ ነበረ።
10የአትክልት ስፍራውን የሚያጠጣ ወንዝ ከዔድን ይፈስስ ነበር፤ ከዚያም በአራት ተከፍሎ ይወጣ ነበር። 11የመጀመሪያው፣ ወርቅ በሚገኝበት በኤውላጥ ምድር ዙሪያ ሁሉ የሚፈስሰው የፊሶን ወንዝ ነው። 12ኤውላጥ ምርጥ የሆነ ወርቅ፣ መልካም መዐዛ#2፥12 ወይም መልካም ዕንቍ ያለው ከርቤና የከበረ ድንጋይ የሚገኙበት ምድር ነው። 13ሁለተኛው፣ በኢትዮጵያ#2፥13 ደቡብ ምሥራቅ መስጴጦምያ ሊሆን ይችላል። ምድር ዙሪያ ሁሉ የሚፈስሰው የግዮን ወንዝ ነው። 14ሦስተኛው፣ ከአሦር በስተምሥራቅ የሚፈስሰው የጤግሮስ ወንዝ ሲሆን፣ አራተኛው የኤፍራጥስ ወንዝ ነው።
15 እግዚአብሔር አምላክ ሰውን ወስዶ እንዲያለማትና እየተንከባከበ እንዲጠብቃት በዔድን የአትክልት ስፍራ አስቀመጠው። 16እግዚአብሔር አምላክ ሰውን እንዲህ በማለት አዘዘው፤ “በአትክልት ስፍራው ውስጥ ከሚገኝ ከማንኛውም ዛፍ ፍሬ ትበላለህ። 17ነገር ግን መልካምና ክፉን ከሚያሳውቀው ዛፍ አትብላ፤ ምክንያቱም ከርሱ በበላህ ቀን በርግጥ ትሞታለህ።”
18ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር አምላክ፣ “ሰው ብቻውን መሆኑ መልካም አይደለምና የሚስማማውን ረዳት አበጅለታለሁ” አለ።
19 እግዚአብሔር አምላክ የዱር አራዊትንና የሰማይ ወፎችን ከምድር ሠርቶ ነበር፤ ለእያንዳንዳቸውም ምን ስም እንደሚያወጣላቸው ለማየት ወደ አዳም አመጣቸው። አዳም ሕይወት ላላቸው ፍጥረታት ሁሉ ያወጣላቸው ስም መጠሪያቸው ሆነ። 20ስለዚህ አዳም#2፥20 ወይም ሰው ለከብቶች፣ ለሰማይ ወፎች፣ ለዱር አራዊት ሁሉ ስም አወጣላቸው።
ይሁን እንጂ ለአዳም ተስማሚ ረዳት አልተገኘለትም ነበር። 21እግዚአብሔር አምላክም በአዳም ላይ ከባድ እንቅልፍ ጣለበት፤ አንቀላፍቶም ሳለ ከጐድኑ አንዲት ዐጥንት#2፥21 ወይም ከሰው የጐን ክፍል ወስዶ ወስዶ፣ ስፍራውን በሥጋ ሞላው። 22እግዚአብሔር አምላክ ከአዳም የወሰዳትን ዐጥንት#2፥22 ወይም ክፍል ሴት አድርጎ ሠራት፤ ወደ አዳምም አመጣት።
23አዳምም እንዲህ አለ፤
“እነሆ፤ ይህች ዐጥንት ከዐጥንቴ፣
ሥጋም ከሥጋዬ ናት።
ከወንድ ተገኝታለችና ‘ሴት’#2፥23 ሰው የሚል ትርጕም ያለው የዕብራይስጥ ቃል ሴት የሚል ትርጕም ካለው የዕብራይስጥ ቃል ጋራ ተመሳሳይ ድምፅ አለው። ትባል።”
24ስለዚህ ሰው ከአባቱና ከእናቱ ተለይቶ ከሚስቱ ጋራ ይጣመራል፤ ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ።
25አዳምና ሚስቱ፣ ሁለቱም ዕራቍታቸውን ነበሩ፤ ይሁን እንጂ አይተፋፈሩም ነበር።

موجودہ انتخاب:

ዘፍጥረት 2: NASV

سرخی

شئیر

کاپی

None

کیا آپ جاہتے ہیں کہ آپ کی سرکیاں آپ کی devices پر محفوظ ہوں؟ Sign up or sign in