የዮሐንስ ወንጌል 5
5
ኢየሱስ አንድ ሽባ ሰው መፈወሱ
1ከዚህ በኋላ የአይሁድ በዓል ስለ ነበረ ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም ሄደ። 2በኢየሩሳሌም በበጎች በር አጠገብ፥ በዕብራይስጥ ቋንቋ ቤተ ሳይዳ የሚባል አንድ የምንጭ ኲሬ ነበረ፤ በዙሪያውም አምስት ከላይ ክዳን ያላቸው መተላለፊያዎች ነበሩ። #5፥2 ቤተሳይዳ፦ አንዳንድ የብራና ጽሑፎች ቤትዛታ፥ ሌሎች ደግሞ ቤተሄስዳ ይላሉ፤ ትርጒሙም የምሕረት ቤት ማለት ነው። 3[በጣም ብዙ በሽተኞች፥ ዕውሮች አንካሶችና ሽባዎች በመተላለፊያዎቹ ተኝተው ነበር። እነዚህ የውሃውን መንቀሳቀስ ይጠባበቁ ነበር፤ 4አልፎ አልፎ የጌታ መልአክ ወደ ኲሬው ወርዶ ውሃውን ያናውጥ ነበር፤ ከውሃው መናወጥ በኋላ በመጀመሪያ ወደ ኲሬው የሚገባ ካደረበት ከማንኛውም በሽታ ይፈወስ ነበር።] #5፥4 የጥንት ብራና ጽሑፎች ከቁ. 3 የመጨረሻ ክፍል አንሥቶ እስከ ቁ. 4 መጨረሻ ድረስ ያለውን ክፍል አይጨምሩም። 5በዚያም ሠላሳ ስምንት ዓመት ሙሉ የታመመ አንድ ሰው ነበረ። 6ኢየሱስ ይህን ሰው እዚያ ተኝቶ አየውና ከብዙ ጊዜ ጀምሮ መታመሙን ዐውቆ፥ “መዳን ትፈልጋለህን?” አለው።
7በሽተኛውም “ጌታ ሆይ! ውሃው በሚንቀሳቀስበት ጊዜ እኔን ወስዶ ወደ ኲሬው የሚያስገባኝ ሰው የለኝም፤ እኔ ልሄድ ስል ሌላው ቀድሞኝ ይወርዳል” አለው።
8ኢየሱስም “ተነሥ! አልጋህን ተሸከምና ሂድ!” አለው። 9ሰውየውም ወዲያውኑ ዳነ፤ አልጋውንም ተሸክሞ ሄደ።
ይህም የሆነው በሰንበት ቀን ነበር፤ 10ስለዚህ የአይሁድ ባለሥልጣኖች ያንን የዳነውን ሰው “ዛሬ ሰንበት ስለ ሆነ አልጋህን እንድትሸከም ሕግ አይፈቅድልህም” አሉት። #ነህ. 13፥19፤ ኤር. 17፥21።
11እርሱ ግን “ያዳነኝ ሰው አልጋህን ተሸክመህ ሂድ” ብሎኛል አላቸው።
12እነርሱም “አልጋህን ተሸክመህ ሂድ ያለህ ማን ነው?” ሲሉ ጠየቁት።
13ሰውየው ግን ሕዝብ ስለ በዛና ኢየሱስም ከዚያ ራቅ ብሎ ስለ ሄደ ያዳነው ማን እንደ ሆነ አያውቅም ነበር።
14ከዚህ በኋላ ኢየሱስ ሰውየውን በቤተ መቅደስ አገኘውና “እነሆ፥ አሁን ድነሃል፤ ከዚህ የባሰ ነገር እንዳይደርስብህ ከእንግዲህ ወዲህ ኃጢአት አትሥራ” አለው።
15ሰውየውም ሄደና ያዳነው ኢየሱስ መሆኑን ለአይሁድ ባለሥልጣኖች ነገረ። 16ይህን ነገር በሰንበት ስላደረገ የአይሁድ ባለሥልጣኖች ኢየሱስን ያሳድዱት ጀመር። 17ኢየሱስ ግን “አባቴ ሁልጊዜ ይሠራል፤ እኔም እሠራለሁ” ሲል መለሰላቸው።
18ይህም አባባል የአይሁድን ባለሥልጣኖች ኢየሱስን እንዲገድሉት በይበልጥ አነሣሣቸው፤ ይህም የሆነው እርሱ ሰንበትን በመሻሩ ብቻ ሳይሆን “እግዚአብሔር አባቴ ነው” በማለት ራሱን ከእግዚአብሔር ጋር ስለ አስተካከለ ነው።
የእግዚአብሔር ልጅ ሥልጣን
19ኢየሱስ እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “እውነት፥ እውነት እላችኋለሁ፤ አብ ሲሠራ ያየውን ከመሥራት በቀር ወልድ በራሱ ሥልጣን ምንም ሊሠራ አይችልም። አብ የሚያደርገውን ወልድም እንዲሁ ያደርጋል። 20አብ ወልድን ስለሚወድ የሚሠራውን ሁሉ ያሳየዋል፤ እናንተም እንድትደነቁ ከዚህ የበለጠ ሥራም ያሳየዋል። 21አብ የሞቱትን እንደሚያስነሣና ሕይወትን እንደሚሰጣቸው፥ ወልድም እንዲሁ ለፈለገው ሰው ሕይወትን ይሰጠዋል። 22አብ በማንም ላይ አይፈርድም፤ ነገር ግን ፍርድን ሁሉ ለወልድ ሰጥቶአል። 23ይህንንም ያደረገው ሰዎች ሁሉ አብን እንደሚያከብሩ፥ እንዲሁም ወልድን እንዲያከብሩ ነው፤ ወልድን የማያከብር፥ ወልድን የላከውን አብን አያከብርም።
24“እውነት፥ እውነት እላችኋለሁ፤ ቃሌን የሚሰማና በላከኝም የሚያምን የዘለዓለም ሕይወት አለው፤ እርሱ ከሞት ወደ ሕይወት የተሻገረ ስለ ሆነ አይፈረድበትም። 25እውነት፥ እውነት እላችኋለሁ፤ የሞቱ ሰዎች የእግዚአብሔርን ልጅ ድምፅ የሚሰሙበት ጊዜ ይመጣል፤ ጊዜውም አሁን ነው፤ የሚሰሙትም ሁሉ በሕይወት ይኖራሉ። 26አብ ራሱ የሕይወት ምንጭ እንዲሆን አድርጎታል። 27የሰው ልጅ በመሆኑም ፍርድ እንዲፈርድ ሥልጣን ሰጥቶታል። 28በዚህ ነገር አትደነቁ፤ በመቃብር ውስጥ ያሉት ሁሉ የእርሱን ድምፅ የሚሰሙበት ሰዓት ይመጣል። 29መልካም የሠሩ ከሞት ተነሥተው በሕይወት ይኖራሉ፤ ክፉ የሠሩ ግን ከሞት ተነሥተው ይፈረድባቸዋል። #ዳን. 12፥2።
ስለ ኢየሱስ የተሰጠ ምስክርነት
30“እኔ በራሴ ሥልጣን ምንም ማድረግ አልችልም፤ ነገር ግን ከአብ የሰማሁትን እፈርዳለሁ፤ የላከኝን ፈቃድ እንጂ የራሴን ፈቃድ ስለማላደርግ ፍርዴ ትክክል ነው።
31“እኔ ስለ ራሴ ብመሰክር ምስክርነቴ እውነት አይደለም። 32ነገር ግን ስለ እኔ የሚመሰክር ሌላ አለ፤ እርሱም ስለ እኔ የሚመሰክረው ምስክርነት እውነት መሆኑን ዐውቃለሁ። 33እናንተ ወደ ዮሐንስ መልእክተኞች ልካችሁ ነበር፤ እርሱም ስለ እውነት መስክሮአል። #ዮሐ. 1፥19-27፤ 3፥27-30። 34ይህንንም ማለቴ እንድትድኑ ነው እንጂ እኔ የሰው ምስክርነት ስላስፈለገኝ አይደለም። 35ዮሐንስ እንደሚነድና እንደሚበራ መብራት ነበረ፤ እናንተም ለጥቂት ጊዜ በእርሱ ብርሃን ለመደሰት ፈለጋችሁ። 36እኔ ግን ከዮሐንስ ምስክርነት የበለጠ ምስክር አለኝ፤ ምስክሬም አባቴ እንድሠራው የሰጠኝ ሥራ ነው፤ ይህም የምሠራው ሥራ፥ አብ እንደ ላከኝ ስለ እኔ ይመሰክራል። 37የላከኝም አብ፥ ራሱ ስለ እኔ መስክሮአል፤ እናንተ ግን ድምፁን ከቶ አልሰማችሁም፤ መልኩንም ከቶ አላያችሁም። #ማቴ. 3፥17፤ ማር. 1፥11፤ ሉቃ. 3፥22። 38እርሱ የላከውን ስለማታምኑ የእርሱ ቃል በእናንተ ዘንድ አይኖርም። 39እናንተ በቅዱሳት መጻሕፍት የዘለዓለምን ሕይወት የምታገኙ ስለሚመስላችሁ እነርሱን ትመረምራላችሁ፤ እነርሱም ስለ እኔ የሚመሰክሩ ናቸው። 40ይሁን እንጂ እናንተ ሕይወትን ለማግኘት ወደ እኔ መምጣት አትፈልጉም።
41“እኔ ክብርን ከሰው አልፈልግም። 42እናንተ ከልባችሁ እግዚአብሔርን የማታፈቅሩ መሆናችሁን ዐውቃለሁ። 43እኔ በአባቴ ስም መጣሁ፤ እናንተ ግን አልተቀበላችሁኝም፤ ሌላ በራሱ ስም ቢመጣ ግን ትቀበሉታላችሁ። 44እናንተ እርስ በርሳችሁ ክብርን የምትፈልጉ ከአንዱ ከእግዚአብሔር የሚገኘውን ክብር ግን የማትፈልጉ፥ እንዴት ልታምኑ ትችላላችሁ? 45እኔ በአባቴ ፊት የምከሳችሁ አይምሰላችሁ፤ የሚከሳችሁ፥ ተስፋ የምታደርጉበት ሙሴ ነው። 46ሙሴን ብታምኑ ኖሮ እርሱ ስለ እኔ ጽፎአልና እኔንም ባመናችሁ ነበር። 47እርሱ የጻፈውን ካላመናችሁ ግን የእኔን ቃል እንዴት ታምናላችሁ?”
موجودہ انتخاب:
የዮሐንስ ወንጌል 5: አማ05
سرخی
شئیر
کاپی
کیا آپ جاہتے ہیں کہ آپ کی سرکیاں آپ کی devices پر محفوظ ہوں؟ Sign up or sign in
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997

: