ኦሪት ዘፍጥረት 16
16
እስማኤል ልደት
1የአብራም ሚስት ሦራ ግን ለአብራም ልጅ አልወለደችለትም ነበር፥ ስምዋ አጋር የተባለ ግብፃዊት ባርያም ነበረቻት። 2ሦራም አብራምን፦ እነሆ፥ እንዳልወልድ እግዚአብሔር ዘጋኝ፥ ምናልባት ከእርሷ በልጅ እታነጽ እንደሆነ ወደ እርሷ ግባ አለችው።#16፥2 እንደ ሜሶጴጣሚያን ሕግ መሠረት መካን ሴት ከሴት አገልጋዮች መካከል አንዷን መርጣ ከባሏ እንድትወልድ ታደርግ ነበር። በዚህ ሁኔታ የተገኘውን ልጅ እንደ እራሷ አድርጋ ትቀበላለች። 3አብራምም የሦራን ቃል ሰማ። አብራምም በከነዓን ምድር ዐሥር ዓመት ከተቀመጠ በኋላ፥ የአብራም ሚስት ሦራ ግብፃዊት ባርያዋን አጋርን ወስዳ ለባልዋ ለአብራም ሚስት ትሆነው ዘንድ ሰጠችው። 4እርሱም ወደ አጋር ገባ፥ አረገዘችም፥ እንዳረገዘችም ባየች ጊዜ እመቤትዋን በዓይንዋ አቃለለች። 5ሦራም አብራምን፦ መገፋቴ በአንተ ላይ ይሁን፥ እኔ ባርያዬን በጉያህ ሰጠሁህ፥ እንዳረገዘችም ባየች ጊዜ እኔን በዓይንዋ አቃለለችኝ፥ እግዚአብሔር በእኔና በአንተ መካከል ይፍረድ አለችው። 6አብራምም ሣራን፦ እነሆ ባርያሽ በእጅሽ ናት፥ እንደ ወደድሽ አድርጊባት አላት። ሦራም ባሠቀየቻት ጊዜ አጋር ከፊትዋ ኮበለለች።
7የእግዚአብሔር መልአክም በውኃ ምንጭ አጠገብ በበረሀ አገኛት፥ ምንጩም ወደ ሱር በምትወስደው መንገድ አጠገብ ነው። 8እርሱም፦ “የሦራ ባርያ አጋር ሆይ፥ ከወዴት መጣሽ? ወዴትስ ትሄጃለሽ?” አላት። እርሷም፦ “እኔ ከእመቤቴ ከሦራ የኮበለልሁ ነኝ” አለች። 9የእግዚአብሔር መልአክም፦ “ወደ እመቤትሽ ተመለሺ፥ ከእጅዋም በታች ሆነሽ ተገዥ” አላት። 10የእግዚአብሔር መልአክም፦ ዘርሽን እጅግ አበዛለሁ፥ ከብዛቱም የተነሣ አይቆጠርም አላት። 11የእግዚአብሔር መልአክም አላት፦ እነሆ አንቺ ፀንሰሻል፥ ወንድ ልጅንም ትወልጃለሽ፥ ስሙንም እስማኤል ብለሽ ትጠሪዋለሽ፥ እግዚአብሔር መቸገርሽን ሰምቶአልና። 12እርሱም የሜዳ አህያን የሚመስል ሰው ይሆናል፥ እጁ በሁሉ ላይ ይሆናል፥ የሁሉም እጅ ደግሞ በእርሱ ላይ ይሆናል፥ እርሱም በወንድሞቹ ሁሉ ፊት ይኖራል። 13እርሷም ይናገራት የነበረውን የእግዚአብሔርን ስም ኤልሮኢ ብላ ጠራች፥ የሚያየኝን በውኑ እዚህ ደግሞ አየሁትን? ብላለችና። 14ስለዚህም የዚያ ጉድጓድ ስም ብኤርለሃይሮኢ ተብሎ ተጠራ፥ እርሱም በቃዴስና በባሬድ መካከል ነው።
15 #
ገላ. 4፥22። አጋርም ለአብራም ወንድ ልጅን ወለደችለት፥ አብራምም አጋር የወለደችለትን የልጁን ስም እስማኤል ብሎ ጠራው። 16አጋር እስማኤልን ለአብራም በወለደችለት ጊዜ አብራም የሰማንያ ስድስት ዓመት ሰው ነበረ።
موجودہ انتخاب:
ኦሪት ዘፍጥረት 16: መቅካእኤ
سرخی
شئیر
کاپی
کیا آپ جاہتے ہیں کہ آپ کی سرکیاں آپ کی devices پر محفوظ ہوں؟ Sign up or sign in