የዮ​ሐ​ንስ ወን​ጌል 5

5
ጌታ​ችን መፃ​ጕ​ዕን እንደ ፈወ​ሰው
1ከዚ​ህም በኋላ በአ​ይ​ሁድ በዓል እን​ዲህ ሆነ፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ወጣ። 2በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም በበ​ጎች በር አጠ​ገብ መጠ​መ​ቂያ ነበ​ረች፤ ስም​ዋ​ንም በዕ​ብ​ራ​ይ​ስጥ ቤተ ሳይዳ ይሉ​አ​ታል፤ አም​ስት እር​ከ​ኖ​ችም ነበ​ሩ​አት። 3በዚ​ያም ዕው​ሮ​ችና አን​ካ​ሶች፥ ሰው​ነ​ታ​ቸ​ውም የሰ​ለለ ብዙ ድው​ያን ተኝ​ተው የው​ኃ​ዉን መና​ወጥ ይጠ​ባ​በቁ ነበር። 4የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አክ ወደ መጠ​መ​ቂ​ያዉ ወርዶ ውኃ​ዉን በሚ​ያ​ና​ው​ጠው ጊዜ፥ ከው​ኃዉ መና​ወጥ በኋላ በመ​ጀ​መ​ሪያ ወርዶ የሚ​ጠ​መቅ ካለ​በት ደዌ ሁሉ ይፈ​ወስ ነበ​ርና። 5በዚ​ያም ከታ​መመ ሠላሳ ስም​ንት ዓመት የሆ​ነው አንድ ሰው ነበር። 6ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ያን ሰው በአ​ል​ጋዉ ተኝቶ ባየ ጊዜ በደዌ ብዙ ዘመን እንደ ቈየ ዐውቆ፥ “ልት​ድን ትወ​ዳ​ለ​ህን?” አለው። 7ድው​ዩም መልሶ፥ “አዎን ጌታዬ ሆይ፥ ነገር ግን ውኃዉ በተ​ና​ወጠ ጊዜ ወደ መጠ​መ​ቂ​ያዉ የሚ​ያ​ወ​ር​ደኝ ሰው የለ​ኝም፤ እኔ በም​መ​ጣ​በት ጊዜ ሌላው ቀድ​ሞኝ ይወ​ር​ዳል” አለው። 8ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “ተነ​ሥና አል​ጋ​ህን ተሸ​ክ​መህ ሂድ” አለው። 9ወዲ​ያ​ው​ኑም ያ ሰው ድኖ አል​ጋ​ውን ተሸ​ክሞ ሄደ፤ ያች ቀንም ሰን​በት ነበ​ረች።
10 # ነህ. 13፥19፤ ኤር. 17፥21። አይ​ሁ​ድም የዳ​ነ​ውን ሰው፥ “ዛሬ ሰን​በት ነው፤ አል​ጋ​ህን ልት​ሸ​ከም አይ​ገ​ባ​ህም” አሉት። 11እር​ሱም መልሶ፥ “ያዳ​ነኝ እርሱ፦ አል​ጋ​ህን ተሸ​ክ​መህ ሂድ አለኝ” አላ​ቸው። 12አይ​ሁ​ድም፥ “አል​ጋ​ህን ተሸ​ክ​መህ ሂድ ያለህ ሰው​ዬው ማነው?” ብለው ጠየ​ቁት። 13ያ የተ​ፈ​ወ​ሰው ግን ያዳ​ነው ማን እንደ ሆነ አላ​ወ​ቀም፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ በዚያ ቦታ በነ​በ​ሩት ብዙ ሰዎች መካ​ከል ተሰ​ውሮ ነበ​ርና። 14ከዚ​ህም በኋላ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ያን የዳ​ነ​ውን ሰው በቤተ መቅ​ደስ አገ​ኘ​ውና፥ “እነሆ፥ ድነ​ሃል፤ ግን ከዚህ የባሰ እን​ዳ​ያ​ገ​ኝህ ዳግ​መኛ እን​ዳ​ት​በ​ድል ተጠ​ን​ቀቅ” አለው። 15ያም ሰው ሄዶ ያዳ​ነው ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ እንደ ሆነ ለአ​ይ​ሁድ ነገ​ራ​ቸው። 16ስለ​ዚ​ህም አይ​ሁድ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን ያሳ​ድ​ዱ​ትና ሊገ​ድ​ሉ​ትም ይሹ ነበር፤ በሰ​ን​በት እን​ዲህ ያደ​ርግ ነበ​ርና። 17ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ፥ “አባቴ እስከ ዛሬ ይሠ​ራል፤ እኔም እሠ​ራ​ለሁ” አላ​ቸው። 18ስለ​ዚ​ህም አይ​ሁድ ሊገ​ድ​ሉት በጣም ይፈ​ልጉ ነበር፤ “ሰን​በ​ትን የሚ​ሽር ነው” በማ​ለት ብቻ አይ​ደ​ለም፤ ደግ​ሞም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን “አባቴ ነው ይላል፤ ራሱ​ንም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጋር ያስ​ተ​ካ​ክ​ላል” በማ​ለት ነው እንጂ።
19ከዚ​ህም በኋላ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ መልሶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እው​ነት እው​ነት እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ ወልድ ከራሱ ብቻ ምንም ሊያ​ደ​ርግ አይ​ች​ልም፤ አብ ሲያ​ደ​ርግ ያየ​ውን ነው እንጂ፤ ወል​ድም አብ የሚ​ሠ​ራ​ውን ያንኑ እን​ዲሁ ይሠ​ራል። 20አብ ልጁን ይወ​ዳ​ልና የሚ​ሠ​ራ​ው​ንም ሥራ ሁሉ ያሳ​የ​ዋል፤ እና​ን​ተም ታደ​ንቁ ዘንድ ከዚህ የሚ​በ​ልጥ ሥራን ያሳ​የ​ዋል። 21አብ ሙታ​ንን እን​ደ​ሚ​ያ​ስ​ነ​ሣ​ቸው፥ ሕይ​ወ​ት​ንም እን​ደ​ሚ​ሰ​ጣ​ቸው እን​ዲሁ ወል​ድም ለሚ​ወ​ድ​ዳ​ቸው ሕይ​ወ​ትን ይሰ​ጣል። 22አብ ከቶ በማ​ንም አይ​ፈ​ር​ድም፤ ፍር​ዱን ሁሉ ለወ​ልድ ሰጠው እንጂ። 23ሰዎች ሁሉ አብን እን​ደ​ሚ​ያ​ከ​ብሩ ወል​ድን ያከ​ብሩ ዘንድ፤ ወል​ድን የማ​ያ​ከ​ብር ግን የላ​ከ​ውን አብን አያ​ከ​ብ​ርም። 24እው​ነት እው​ነት እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ ቃሌን የሚ​ሰማ በላ​ከ​ኝም የሚ​ያ​ምን የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወ​ትን ያገ​ኛል፤ ከሞ​ትም ወደ ሕይ​ወት ተሻ​ገረ እንጂ ወደ ፍርድ አይ​ሄ​ድም።
25“እው​ነት እው​ነት እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ ሙታን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ልጅ ቃል የሚ​ሰ​ሙ​በት ሰዓት ይመ​ጣል፤ እር​ሱም አሁን ነው፤ የሚ​ሰ​ሙ​ትም ይድ​ናሉ። 26ለአብ በራሱ ሕይ​ወት እን​ዳ​ለው፥ እን​ዲ​ሁም ደግሞ ለወ​ልድ በራሱ ሕይ​ወት እን​ዲ​ኖ​ረው ሰጠው። 27የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጅ የሰው ልጅ ነውና ይፈ​ርድ ዘንድ ሥል​ጣ​ንን ሰጠው።
ስለ ትን​ሣኤ ሙታን
28“በመ​ቃ​ብር ያሉ ሁሉ ቃሉን የሚ​ሰ​ሙ​ባት ጊዜ ትመ​ጣ​ለ​ችና ስለ​ዚህ አታ​ድ​ንቁ። 29#ዳን. 12፥2። መል​ካም የሠሩ ለሕ​ይ​ወት ትን​ሣኤ፥ ክፉ የሠ​ሩም ለፍ​ርድ ትን​ሣኤ ይነ​ሣሉ። 30እኔ ከራሴ አን​ዳች አደ​ርግ ዘንድ አል​ች​ልም፤ እንደ ሰማሁ እፈ​ር​ዳ​ለሁ እንጂ፤ ፍር​ዴም እው​ነት ነው፤ የላ​ከ​ኝን ፈቃድ እንጂ የእ​ኔን ፈቃድ አል​ሻ​ምና።
ስለ ምስ​ክ​ር​ነት
31“እኔ ለራሴ ብመ​ሰ​ክር ምስ​ክ​ር​ነቴ እው​ነት አይ​ደ​ለም። 32ነገር ግን ለእኔ የሚ​መ​ሰ​ክር ሌላ ነው፤ ስለ እኔ የመ​ሰ​ከ​ረው ምስ​ክ​ር​ነ​ቱም እው​ነት እን​ደ​ሆነ አው​ቃ​ለሁ። 33#ዮሐ. 1፥19-27፤ 3፥27-30። እና​ንተ ወደ ዮሐ​ንስ ልካ​ችሁ አል​ነ​በ​ረ​ምን? እር​ሱም ምስ​ክ​ር​ነ​ቱን በእ​ው​ነት ነገ​ራ​ችሁ። 34እኔ ግን የሰ​ውን ምስ​ክ​ር​ነት የምሻ አይ​ደ​ለ​ሁም፤ ነገር ግን እና​ንተ ትድኑ ዘንድ ይህን እላ​ለሁ። 35እርሱ የሚ​ነ​ድና የሚ​ያ​በራ መብ​ራት ነበረ፤ እና​ን​ተም አን​ዲት ሰዓት በብ​ር​ሃኑ ደስ ሊላ​ችሁ ወደ​ዳ​ችሁ። 36እኔ ግን ከዮ​ሐ​ንስ ምስ​ክ​ር​ነት የሚ​በ​ልጥ ምስ​ክር አለኝ፤ ልሠ​ራ​ውና ልፈ​ጽ​መው አባቴ የሰ​ጠኝ ሥራ፥ አብ እንደ ላከኝ ያ የም​ሠ​ራው ሥራ ምስ​ክሬ ነውና። 37#ማቴ. 3፥17፤ ማር. 1፥11፤ ሉቃ. 3፥22። የላ​ከኝ አብም ስለ እኔ መስ​ክ​ሮ​አል፤ ከሆ​ነም ጀምሮ ቃሉን አል​ሰ​ማ​ች​ሁም፤ መል​ኩ​ንም አላ​ያ​ች​ሁም። 38ቃሉም የላ​ች​ሁም፤ በእ​ና​ንተ ዘን​ድም አይ​ኖ​ርም፤ እርሱ የላ​ከ​ውን አላ​መ​ና​ች​ሁ​ምና። 39መጻ​ሕ​ፍ​ትን መር​ምሩ፤ በእ​ነ​ርሱ የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወ​ትን የም​ታ​ገኙ ይመ​ስ​ላ​ች​ኋ​ልና፤ እነ​ር​ሱም የእኔ ምስ​ክ​ሮች ናቸው። 40ሕይ​ወ​ትን ታገኙ ዘንድ ወደ እኔ ልት​መጡ አት​ወ​ዱም። 41እኔ ከሰው ክብ​ርን ልቀ​በል አል​ሻም። 42ነገር ግን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፍቅር በእ​ና​ንተ እን​ደ​ሌ​ለ​ባ​ችሁ ዐወ​ቅሁ። 43እኔ በአ​ባቴ ስም መጣሁ፥ አል​ተ​ቀ​በ​ላ​ች​ሁ​ኝ​ምም፤ ሌላው ግን በራሱ ስም ቢመጣ እር​ሱን ትቀ​በ​ሉ​ታ​ላ​ችሁ። 44ከባ​ል​ን​ጀ​ራ​ችሁ ክብ​ርን የም​ት​መ​ርጡ፥ ከአ​ንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ክብ​ርን የማ​ትሹ እና​ንተ እን​ዴት ልታ​ምኑ ትች​ላ​ላ​ችሁ? 45እኔ በአብ ዘንድ የም​ከ​ስ​ሳ​ችሁ አይ​ም​ሰ​ላ​ችሁ፤ የሚ​ከ​ስ​ሳ​ች​ሁስ አለ፤ እር​ሱም እና​ንተ ተስፋ የም​ታ​ደ​ር​ጉት ሙሴ ነው። 46ሙሴ​ንስ አም​ና​ች​ሁት ቢሆን እኔ​ንም ባመ​ና​ች​ሁኝ ነበር፤ እርሱ ስለ እኔ ጽፎ​አ​ልና። 47ሙሴ የጻ​ፈ​ውን ካላ​መ​ና​ችሁ ግን የእ​ኔን ቃል እን​ዴት ታም​ና​ላ​ችሁ?”

سرخی

شئیر

کاپی

None

کیا آپ جاہتے ہیں کہ آپ کی سرکیاں آپ کی devices پر محفوظ ہوں؟ Sign up or sign in

YouVersion آپ کے تجربے کو ذاتی بنانے کے لیے کوکیز کا استعمال کرتا ہے۔ ہماری ویب سائٹ کا استعمال کرتے ہوئے، آپ ہماری کوکیز کے استعمال کو قبول کرتے ہیں جیسا کہ ہماری رازداری کی پالیسیمیں بیان کیا گیا ہے۔