ዘፍጥረት 5

5
ከአዳም እስከ ኖኅ
1የአዳም የትውልድ ሐረግ እንደሚከተለው ነው፦
እግዚአብሔር (ኤሎሂም) ሰውን ሲፈጥረው በራሱ አምሳል አበጀው፤ 2ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው፤ ባረካቸው፤ በተፈጠሩም ጊዜ “ሰው”#5፥2 በዕብራይስጥ አዳም ማለት ነው። ብሎ ጠራቸው።
3አዳም፣ ዕድሜው 130 ዓመት በሆነ ጊዜ፣ እርሱን ራሱን የሚመስል ወንድ ልጅ ወለደ፤ ስሙንም ሴት ብሎ ጠራው። 4ሴት ሄኖስን ከወለደ በኋላ አዳም 800 ዓመት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ወለደ፤ 5አዳም በአጠቃላይ 930 ዓመት ከኖረ በኋላ ሞተ።
6ሴት፣ ዕድሜው 105 ዓመት ሲሆን ሄኖስን ወለደ፤ 7ሴት ሄኖስን ከወለደ በኋላ 807 ዓመት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ወለደ። 8ሴት በአጠቃላይ 912 ዓመት ከኖረ በኋላ ሞተ።
9ሄኖስ፣ ዕድሜው 90 ዓመት በሆነ ጊዜ ቃይናንን ወለደ፤ 10ሄኖስ ቃይናንን ከወለደ በኋላ 815 ዓመት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ወለደ። 11ሄኖስ በአጠቃላይ 905 ዓመት ከኖረ በኋላ ሞተ።
12ቃይናን፣ ዕድሜው 70 ዓመት ሲሆን መላልኤልን ወለደ፤ 13ቃይናን መላልኤልን ከወለደ በኋላ 840 ዓመት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ወለደ። 14ቃይናን በአጠቃላይ 910 ዓመት ከኖረ በኋላ ሞተ።
15መላልኤል፣ ዕድሜው 65 ዓመት በሆነ ጊዜ ያሬድን ወለደ፤ 16መላልኤል ያሬድን ከወለደ በኋላ 830 ዓመት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ወለደ። 17መላልኤል በአጠቃላይ 895 ዓመት ከኖረ በኋላ ሞተ።
18ያሬድ፣ ዕድሜው 162 ዓመት ሲሆን ሄኖክን ወለደ፤ 19ያሬድ ሄኖክን ከወለደ በኋላ 800 ዓመት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ወለደ። 20ያሬድ በአጠቃላይ 962 ዓመት ከኖረ በኋላ ሞተ።
21ሄኖክ፣ ዕድሜው 65 ዓመት በሆነ ጊዜ ማቱሳላን ወለደ፤ 22ሄኖክ ማቱሳላን ከወለደ በኋላ አካሄዱን ከእግዚአብሔር (ኤሎሂም) ጋር በማድረግ 300 ዓመት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ወለደ። 23ሄኖክ በአጠቃላይ 365 ዓመት ኖረ፤ 24ሄኖክ አካሄዱን ከእግዚአብሔር (ኤሎሂም) ጋር አደረገ፤ እግዚአብሔር (ኤሎሂም) ስለ ወሰደውም አልተገኘም።
25ማቱሳላ፣ ዕድሜው 187 ዓመት ሲሆን ላሜሕን ወለደ፤ 26ማቱሳላ ላሜሕን ከወለደ በኋላ፣ 782 ዓመት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ወለደ፤ 27ማቱሳላ በአጠቃላይ 969 ዓመት ከኖረ በኋላ ሞተ።
28ላሜሕ፣ ዕድሜው 182 ዓመት በሆነ ጊዜ፣ ልጅ ወለደ። 29ስሙንም “እግዚአብሔር (ያህዌ) በረገማት ምድር ከልፋታችንና ከጕልበታችን ድካም ያሳርፈናል” ሲል ኖኅ#5፥29 ኖኅ የሚለው ስም መጽናናት የሚል ትርጕም ካለው የዕብራይስጥ ቃል ጋር ተመሳሳይ ድምፅ አለው። ብሎ ጠራው። 30ላሜሕ ኖኅን ከወለደ በኋላ፣ 595 ዓመት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ወለደ። 31ላሜሕ በአጠቃላይ 777 ዓመት ከኖረ በኋላ ሞተ።
32ኖኅ ዕድሜው 500 ዓመት ሲሆን ሴምን፣ ካምንና ያፌትን ወለደ።

Currently Selected:

ዘፍጥረት 5: NASV

Qaqambisa

Share

Copy

None

Ufuna ukuba iimbalasane zakho zigcinwe kuzo zonke izixhobo zakho? Bhalisela okanye ngena