1
ዘፍጥረት 9:12-13
አዲሱ መደበኛ ትርጒም
እግዚአብሔርም (ኤሎሂም) እንዲህ አለ፤ “በእኔና በእናንተ መካከል፣ ከእናንተም ጋር ካሉ ሕያዋን ፍጡራን ሁሉ ጋር ከሚመጣውም ትውልድ ሁሉ ጋር፣ የማደርገው የኪዳኑ ምልክት ይህ ነው፤ ቀስተ ደመናዬን በደመና ላይ አደርጋለሁ፤ ይህም በእኔና በምድር መካከል ለገባሁት ኪዳን ምልክት ይሆናል።
Qhathanisa
Hlola ዘፍጥረት 9:12-13
2
ዘፍጥረት 9:16
ቀስቱ በደመና ላይ ተገልጦ በማይበት ጊዜ ሁሉ፣ በእኔና በምድር ላይ ባሉ ሕያዋን ፍጡራን መካከል ያለውን ዘላለማዊ ኪዳን ዐስባለሁ።”
Hlola ዘፍጥረት 9:16
3
ዘፍጥረት 9:6
“የሰውን ደም የሚያፈስስ ሁሉ፣ ደሙ በሰው እጅ ይፈስሳል፤ በእግዚአብሔር (ኤሎሂም) አምሳል፣ እግዚአብሔር (ኤሎሂም) ሰውን ሠርቶታልና።
Hlola ዘፍጥረት 9:6
4
ዘፍጥረት 9:1
እግዚአብሔር (ኤሎሂም) ኖኅንና ልጆቹን እንዲህ ሲል ባረካቸው፤ “ብዙ ተባዙ፤ ምድርንም ሙሏት፤
Hlola ዘፍጥረት 9:1
5
ዘፍጥረት 9:3
ሕያውና ተንቀሳቃሽ ፍጡር ሁሉ ምግብ ይሁናችሁ፤ ለምለሙን ዕፀዋት እንደ ሰጠኋችሁ፣ አሁን ደግሞ ሁሉን ሰጠኋችሁ።
Hlola ዘፍጥረት 9:3
6
ዘፍጥረት 9:2
አስፈሪነታችሁና አስደንጋጭነታችሁ በዱር አራዊት፣ በሰማይ አዕዋፍ፣ በደረት በሚሳቡ ተንቀሳቃሽ ፍጡሮችና በባሕር ዓሦች ሁሉ ላይ ይሁን፤ በእጃችሁ ተሰጥተዋል።
Hlola ዘፍጥረት 9:2
7
ዘፍጥረት 9:7
እናንተ ግን ብዙ ተባዙ፤ ዘራችሁ በምድር ላይ ይብዛ፤ ይንሰራፋ።”
Hlola ዘፍጥረት 9:7
Ikhaya
IBhayibheli
Amapulani
Amavidiyo