1
መዝሙር 146:5
አዲሱ መደበኛ ትርጒም
ብፁዕ ነው፤ ረዳቱ የያዕቆብ አምላክ የሆነ፣ ተስፋውንም በአምላኩ በእግዚአብሔር ላይ የጣለ ሰው፤
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
መዝሙር 146:3
በገዦች አትታመኑ፤ ማዳን በማይችሉ በሰው ልጆችም አትመኩ።
3
መዝሙር 146:7-8
ለተበደሉት የሚፈርድ፣ ለተራቡት ምግብን የሚሰጥ እርሱ ነው፤ እግዚአብሔር እስረኞችን ከእስራት ያወጣል፤ እግዚአብሔር የዕውራንን ዐይን ያበራል፤ እግዚአብሔር የተዋረዱትን ከፍ ያደርጋል፤ እግዚአብሔር ጻድቃንን ይወድዳል፤
4
መዝሙር 146:6
እርሱ ሰማይንና ምድርን፣ ባሕርንም፣ በውስጣቸውም የሚኖሩትን ሁሉ የፈጠረ፣ ታማኝነቱም ለዘላለም የሆነ ነው፤
5
መዝሙር 146:9
እግዚአብሔር ስደተኞችን ይጠብቃል፤ ድኻ አደጎችንና መበለቶችን ይደግፋል፤ የክፉዎችን መንገድ ግን ያጠፋል።
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች