1
1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 12:7
መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
ለእያንዳንዱ የመንፈስን መገለጥ የሚሰጠው ለጥቅም ነው።
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 12:27
እናንተም የክርስቶስ አካል ናችሁ፤ እያንዳንዳችሁም የአካሉ ክፍሎች ናችሁ።
3
1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 12:26
አንድም አካል ቢሠቃይ የአካል ክፍሎች ሁሉ ከእርሱ ጋር ይሠቃያሉ፤ አንድ አካልም ቢከበር የአካል ክፍሎች ሁሉ ከእርሱ ጋር ደስ ይላቸዋል።
4
1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 12:8-10
ለአንዱ ጥበብን መናገር በመንፈስ ይሰጠዋል፤ ለሌላውም ያው መንፈስ እውቀትን መናገር ይሰጠዋል፤ በዚያው መንፈስ ለአንዱ እምነት ይሰጠዋል፤ ለሌላው የመፈወስ ስጦታን በዚያው አንድ መንፈስ ይሰጠዋል፤ ለሌላው ተአምራትን የማድረግ ኃይል ይሰጠዋል፤ ለሌላው ትንቢትን መናገር፥ ለአንዱ መናፍስትን መለየት፥ ለሌላው በልዩ ዓይነት ልሳን መናገር፥ ለሌላውም በልሳኖች የተነገረውን መተርጎም ይሰጠዋል፤
5
1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 12:11
ይህን ሁሉ ግን አንዱና ያው መንፈስ ያደርጋል፤ እንደፈቃዱም ለእያንዳንዱ ሰው ለብቻው እያካፈለ ያደርጋል።
6
1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 12:25
ይህም በአካል ክፍሎች መካከል መለያየት ሳይኖር እርስ በርሳቸው እንዲተሳሰቡ ነው።
7
1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 12:4-6
ልዩ ልዩ ስጦታዎች አሉ፤ መንፈስ ግን አንድ ነው፤ ጌታም አንድ ሲሆን፤ ልዩ ልዩ አገልግሎቶችም አሉ፤ አሠራሮችም ልዩ ልዩ አሉ፤ ሁሉን በሁሉ የሚያደርግ ግን አንዱ እግዚአብሔር ነው።
8
1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 12:28
እግዚአብሔርም አንዳንዶቹን አስቀድሞ ሐዋርያትን፥ ሁለተኛም ነቢያትን፥ ሦስተኛም አስተማሪዎችን፥ ቀጥሎም ተአምራት የሚያደርጉትን፥ ቀጥሎም የመፈወስ ስጦታ ያላቸውን፥ ሰዎችን የመርዳት ስጦታ ያላቸውን፥ አስተዳዳሪዎችንና በተለያዩ ልሳኖች የሚናገሩትን ሰዎች በቤተ ክርስቲያን ሰይሟል።
9
1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 12:14
አካል ብዙ የአካል ክፍሎች እንጂ አንድ የአካል ክፍል አይደለምና።
10
1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 12:22
ነገር ግን ደካሞች የሚመስሉ የአካል ክፍሎች ይልቁን የሚያስፈልጉ ናቸው፤
11
1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 12:17-19
አካል ሁሉ ዐይን ቢሆን መስማት ወዴት በተገኘ? ሁሉም መስማት ቢሆን ማሽተት ወዴት በተገኘ? አሁን ግን እግዚአብሔር እንደ ወደደ የአካል ክፍሎችን እያንዳንዳቸው በአካል አድርጎአል። ሁሉም አንድ የአካል ክፍል ቢሆንስ አካል ወዴት በሆነ?
Home
Bible
Plans
Videos