1
ትንቢተ ኢሳይያስ 26:3
መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
በአንተ ለምትደገፍ ነፍስ በአንተ ላይ ታምናለችና በሰላም ትጠብቃታለህ።
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
ትንቢተ ኢሳይያስ 26:4
ጌታ እግዚአብሔር የዘለዓለም ዐለት ነውና ለዘለዓለም በጌታ ታመኑ።
3
ትንቢተ ኢሳይያስ 26:9
ፍርድህን በምድር ላይ በፈረድክ ጊዜ በዓለም የሚኖሩ ጽድቅን ይማራሉና ነፍሴ በሌሊት ትናፍቅሃለች፥ መንፈሴም በውስጤ ወደ አንተ ትገሠግሣለች።
4
ትንቢተ ኢሳይያስ 26:12
አቤቱ ጌታ፥ ሥራችንን ሁሉ ሠርተህልናልና ሰላምን ትሰጠናለህ።
5
ትንቢተ ኢሳይያስ 26:8
አቤቱ ጌታ፥ በፍርድህ መንገድ ተስፋ አድርገንሃል፥ ስምህም መታሰቢያህም የነፍሳችን ምኞት ነው።
6
ትንቢተ ኢሳይያስ 26:7
የጻድቃን መንገድ ቅን ናት፤ አንተ ቅን የሆንክ የጻድቃንን መንገድ ታቀናለህ።
7
ትንቢተ ኢሳይያስ 26:5
በከፍታ የሚኖሩትን ሰዎች ዝቅ ያደርጋል፤ ከፍ ያለችውን ከተማ ያዋርዳል፥ እስከ መሬትም ድረስ ያወርዳታል፥ እስከ ትቢያም ድረስ ይጥላታል።
8
ትንቢተ ኢሳይያስ 26:2
በእምነቱ የጸና ጻድቅ ሕዝብ ይገባ ዘንድ በሮችን ክፈቱ።
Home
Bible
Plans
Videos