1
ትንቢተ ኢሳይያስ 60:1
የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)
ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ብርሃንሽ መጥቶአልና፥ የእግዚአብሔርም ብርሃን በአንቺ ላይ ወጥቶአልና አብሪ፤ አብሪ።
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
ትንቢተ ኢሳይያስ 60:3
ነገሥታት በብርሃንሽ፥ አሕዛብም በፀዳልሽ ይሄዳሉ።
3
ትንቢተ ኢሳይያስ 60:2
እነሆ፥ ጨለማ ምድርን፥ ድቅድቅ ጨለማም አሕዛብን ይሸፍናል፤ ነገር ግን በአንቺ ላይ እግዚአብሔር ይገለጣል፤ ክብሩም በአንቺ ላይ ይታያል፤
4
ትንቢተ ኢሳይያስ 60:22
ታናሹ ሺህ፥ የሁሉም ታናሽ ታላቅ ሕዝብ ይሆናል፤ እኔ እግዚአብሔር በዘመናቸው ሁሉ እሰበስባቸዋለሁ።
5
ትንቢተ ኢሳይያስ 60:19
ፀሐይ በቀን የሚያበራልሽ አይደለም፤ በሌሊትም ጨረቃ የሚወጣልሽ አይደለም፤ ለአንቺስ እግዚአብሔር የዘለዓለም ብርሃንሽ፥ አምላክሽም ክብርሽ ይሆናል።
6
ትንቢተ ኢሳይያስ 60:20
እግዚአብሔር የዘለዓለም ብርሃንሽ ይሆናልና፥ የልቅሶሽም ወራት ያልፋልና፤ ፀሐይሽ ከዚህ በኋላ አትጠልቅም፤ ጨረቃሽም አይቋረጥም።
7
ትንቢተ ኢሳይያስ 60:5
በዚያ ጊዜ አይተሽ ትፈሪያለሽ፤ የአሕዛብና የሀገሮች ብልጽግና ወደ አንቺ ይመለሳልና፥ ልብሽ ይደነግጣል።
8
ትንቢተ ኢሳይያስ 60:4
ዐይኖችሽን አንሥተሽ በዙሪያሽ ተመልከቺ፤ ልጆችሽም እንደ ተሰበሰቡ እነሆ፥ እዪ፤ ወንዶች ልጆችሽ ከሩቅ ይመጣሉ፤ ሴቶች ልጆችሽንም በጫንቃ ላይ ይሸከሙአቸዋል።
9
ትንቢተ ኢሳይያስ 60:21
ሕዝብሽ ሁሉ ጻድቃን ይሆናሉ፤ ምድርንም ለዘለዓለም ይወርሳሉ፤ እርሱንም ለማመስገን የእጆቹን ሥራ ይጠብቃሉ።
10
ትንቢተ ኢሳይያስ 60:18
እንግዲህ በምድርሽ ውስጥ ግፍ፥ በዳርቻሽም ውስጥ ጕስቍልናና ቅጥቃጤ አይሰማም፤ ቅጥሮችሽ ድኅነት ይባላሉ፤ በሮችሽም በጥርብ ድንጋይ ይሠራሉ።
11
ትንቢተ ኢሳይያስ 60:11
በሮችሽም ሁልጊዜ ይከፈታሉ፤ ሰዎች የአሕዛብን ብልጽግና፥ የተማረኩትንም ነገሥታቶቻቸውን ወደ አንቺ ያመጡ ዘንድ ሌሊትና ቀን አይዘጉም።
12
ትንቢተ ኢሳይያስ 60:6
የግመሎች መንጋ ወደ አንቺ ይመጣሉ፤ የምድያምና የኤፋ ግመሎች ይሸፍኑሻል፤ ሁሉ ከሳባ ወርቅንና ዕጣንን ይዘው ይመጣሉ፤ የእግዚአብሔርንም ማዳን ያበሥራሉ።
13
ትንቢተ ኢሳይያስ 60:10
በቍጣዬ ቀሥፌ በይቅርታዬ አቅርቤሻለሁና መጻተኞች ቅጥርሽን ይሠራሉ፤ ነገሥታቶቻቸውም በፊትሽ ይቆማሉ።
14
ትንቢተ ኢሳይያስ 60:15
የተተውሽና የተጠላሽ ሆነሻልና የሚረዳሽ አጣሽ፤ ነገር ግን የዘለዓለም ደስታን ለልጅ ልጅ እሰጥሻለሁ።
15
ትንቢተ ኢሳይያስ 60:16
የአሕዛብንም ወተት ትጠጫለሽ፤ የነገሥታትንም ብልጽግና ትበያለሽ፤ እኔም እግዚአብሔር የእስራኤል ቅዱስ፥ መድኀኒትሽና ታዳጊሽ እንደ ሆንሁ ታውቂያለሽ።
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች