1
መጽሐፈ ምሳሌ 22:6
የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)
ልጅን በሚሄድበት መንገድ ምራው፥ በሸመገለም ጊዜ ከእርሱ ፈቀቅ አይልም።
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
መጽሐፈ ምሳሌ 22:4
እግዚአብሔርን መፍራት፥ ጥበብን ባለጠግነትንና ክብርን፥ ሕይወትንም ትወልዳለች።
3
መጽሐፈ ምሳሌ 22:1
መልካም ስም ከብዙ ባለ ጠግነት ይሻላል፥ መልካም ሞገስም ከብርና ከወርቅ ይበልጣል።
4
መጽሐፈ ምሳሌ 22:24
ከቍጡ ሰው ጋር ባልንጀራ አትሁን፥ ከነዝናዛም ጓደኛ ጋር አትኑር።
5
መጽሐፈ ምሳሌ 22:9
ለድሃ የሚራራ እርሱ ይበላል እንጀራውን ለድሃ ሰጥቶአልና። ለሰጠው ሀብታምም የሚከፍል አይደለምና። መማለጃን የሰጠ ሰው ድል መንሣትንና ሞገስን ያገኛል፥ ነገር ግን የተቀበለውን ነፍስ ያጠፋል።
6
መጽሐፈ ምሳሌ 22:3
ዐዋቂ ሰው ክፉ ሰው በኀይል ሲቀጣ አይቶ ይገሠጻል፥ አላዋቂዎች ግን ሲያልፉ ይጐዳሉ።
7
መጽሐፈ ምሳሌ 22:7
ድሆች ባለጠጎችን ይገዛሉ፥ አገልጋዮችም ለጌቶቻቸው ያበድራሉ።
8
መጽሐፈ ምሳሌ 22:2
ባለ ጠጋና ድሃ በአንድነት ተገናኙ፤ ሁለቱንም እግዚአብሔር ፈጠራቸው።
9
መጽሐፈ ምሳሌ 22:22-23
ድሃን በግድ አትበለው፥ ድሃ ነውና ችግረኛውንም በበር አትግፋው፤ እግዚአብሔር ፍርዱን ይፈርድለታልና። አንተም ነፍስህን በሰላም ታድናለህ።
Home
Bible
Plans
Videos