ኢሳይያስ 20
20
በግብጽና በኢትዮጵያ ላይ የተነገረ ትንቢት
1ዋናው የጦር አዛዥ#20፥1 ዋናው የጦር አዛዥ የሚለውን ዕብራይስጡ ተርታን ይለዋል። በአሦር ንጉሥ በሳርጎን ተልኮ፣ የአዛጦንን ከተማ ወርሮ በያዘበት ዓመት፣ 2በዚያ ጊዜ እግዚአብሔር የአሞጽን ልጅ ኢሳይያስን፣ “ማቁን ከሰውነትህ፣ ጫማህን ከእግርህ አውልቅ” ሲል ተናገረው። እርሱም እንዲሁ አደረገ፤ ዕርቃኑንና ባዶ እግሩን ተመላለሰ።
3ከዚያም እግዚአብሔር እንዲህ አለ፤ “ባሪያዬ ኢሳይያስ ሦስት ዓመት በግብጽና በኢትዮጵያ ለምልክትና ለማስጠንቀቂያ ዕርቃኑንና ባዶ እግሩን እንደ ሄደ፣ 4እንዲሁ የአሦር ንጉሥ ወጣትና ሽማግሌ የሆኑትን የተማረኩ ግብጻውያንንና የተሰደዱ ኢትዮጵያውያንን#20፥4 የላይኛውን የአባይ ወንዝ አካባቢን ያመላክታል። ዕርቃናቸውንና ባዶ እግራቸውን ይወስዳቸዋል፤ መቀመጫቸውን ገልቦ በመስደድም ግብጽን ያዋርዳል። 5በኢትዮጵያ ተስፋ ያደረጉ፣ በግብጽ የተመኩ ይፈራሉ፤ ይዋረዳሉም። 6በዚያ ቀን በዚህ ባሕር ዳርቻ የሚኖረው ሕዝብ፣ ‘የተመካንባቸው፣ ከአሦር ንጉሥ ለማምለጥና ነጻ ለመውጣት የተሸሸግንባቸው ምን እንደ ደረሰባቸው ተመልከቱ! እንግዲህ እኛስ እንዴት እናመልጣለን?’ ይላል።”
Currently Selected:
ኢሳይያስ 20: NASV
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
መጽሐፍ ቅዱስ፣ አዲሱ መደበኛ ትርጕም™
የቅጂ መብት © 2001, 2024 በBiblica, Inc.
በፈቃድ የሚወሰድ። በዓለም ዐቀፍ ባለቤትነቱ።
The Holy Bible, New Amharic Standard Version™
Copyright © 2001, 2024 by Biblica, Inc.
Used with permission. All rights reserved worldwide.