ማቴዎስ 26:69-70

ማቴዎስ 26:69-70 NASV

ከዚህ በኋላ ጴጥሮስ በሊቀ ካህናቱ ግቢ ውስጥ ተቀምጦ ሳለ አንዲት የቤት ሠራተኛ ወደ እርሱ ቀርባ፣ “አንተም ከገሊላው ኢየሱስ ጋራ ነበርህ” አለችው። እርሱ ግን፣ “ምን እንደምትናገሪ እኔ አላውቅም” በማለት በሁላቸውም ፊት ካደ።