የማቴዎስ ወንጌል 26:69-70

የማቴዎስ ወንጌል 26:69-70 አማ05

ጴጥሮስ ከቤት ውጪ በሊቀ ካህናቱ ግቢ ውስጥ ተቀምጦ ነበር፤ በዚያን ጊዜ አንዲት ገረድ ወደ እርሱ ቀርባ “አንተም ከገሊላዊው ኢየሱስ ጋር ነበርክ!” አለችው። እርሱ ግን “የምትዪውን አላውቅም!” ሲል በሁሉም ፊት ካደ።