መዝሙር 113
113
መዝሙር 113
1ሃሌ ሉያ።#113፥1 እግዚአብሔር ይመስገን ማለት ሲሆን፣ በሌሎች መዝሙራትም ይገኛል።
የእግዚአብሔር አገልጋዮች ሆይ፤ አመስግኑት፤
የእግዚአብሔርን ስም አወድሱ።
2ከአሁን እስከ ዘላለም፣
የእግዚአብሔር ስም የተመሰገነ ይሁን።
3ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ ድረስ፣
የእግዚአብሔር ስም የተመሰገነ ይሁን።
4 እግዚአብሔር ከሕዝቦች ሁሉ በላይ ከፍ ያለ ነው፤
ክብሩም ከሰማያት በላይ ነው።
5እንደ አምላካችን እንደ እግዚአብሔር፣
በላይ በዙፋኑ የተቀመጠ ማን ነው?
6በሰማይና በምድር ያሉትንስ ለማየት፣
ራሱን ወደ ታች ዝቅ የሚያደርግ ማን ነው?
7ድኻውን ከዐፈር ያነሣል፤
ችግረኛውን ከዐመድ ከፍ ከፍ ያደርጋል፤
8ከመኳንንትም እኩል ስፍራ ይሰጠዋል፤
ከሕዝቡም ሹማምት ጋራ ያስቀምጠዋል።
9መካኒቱን ሴት በቤት ያኖራታል፤
ደስተኛም የልጆች እናት ያደርጋታል።
ሃሌ ሉያ።
መጽሐፍ ቅዱስ፣ አዲሱ መደበኛ ትርጕም™
የቅጂ መብት © 2001, 2024 በBiblica, Inc.
በፈቃድ የሚወሰድ። በዓለም ዐቀፍ ባለቤትነቱ።
The Holy Bible, New Amharic Standard Version™
Copyright © 2001, 2024 by Biblica, Inc.
Used with permission. All rights reserved worldwide.