መዝሙር 42

42
ሁለተኛ መጽሐፍ
ከመዝሙር 42–72
መዝሙር 42#42 በብዙ የዕብራይስጥ ቅጆች መዝሙር 42 እና 43 አንድ መዝሙር ነው።
ለመዘምራን አለቃ፤ የቆሬ ልጆች ማስኪል።#42፥0 በሙዚቃ ውስጥ የሚጠቀሙበት ቃል ሳይሆን አይቀርም።
1ዋላ የምንጭ ውሃ እንደምትናፍቅ፣
አምላክ ሆይ፤ ነፍሴም እንዲሁ አንተን ትናፍቃለች።
2ነፍሴ አምላክን፣ ሕያው አምላክን ተጠማች፤
መቼ ደርሼ ነው የአምላክን ፊት የማየው?
3ሰዎች ቀኑን ሙሉ፣
“አምላክህ የት አለ?” ባሉኝ ቍጥር፣
እንባዬ ቀንና ሌሊት፣
ምግብ ሆነኝ።
4ነፍሴ በውስጤ እየፈሰሰች፣
እነዚህን ነገሮች አስታወስሁኝ፤
ታላቅ ሕዝብ ወደ እግዚአብሔር ቤት እየመራሁ፣
በእልልታና በምስጋና መዝሙር፣
በአእላፍ ሕዝብ መካከል፣
እንዴት ከሕዝቡ ጋራ እሄድ እንደ ነበር ትዝ አለኝ።
5ነፍሴ ሆይ፤ ለምን ትተክዢያለሽ?
ለምንስ በውስጤ ትታወኪያለሽ?
ተስፋሽን በአምላክ ላይ አድርጊ፤
አዳኜና አምላኬን ገና አመሰግነዋለሁና።
6ነፍሴ በውስጤ ተክዛለች፤
ስለዚህ በዮርዳኖስ ምድር፣
በአርሞንዔም ከፍታ፣ በሚዛር ተራራ ዐስብሃለሁ።
7በፏፏቴህ ማስገምገም፣
አንዱ ጥልቅ ሌላውን ጥልቅ ይጣራል፤
ማዕበልህና ሞገድህ ሁሉ፣
ሙሉ በሙሉ አጥለቀለቀኝ።
8 እግዚአብሔር ምሕረቱን በቀን ያዝዛል፤
ዝማሬውም በሌሊት በእኔ ዘንድ አለ፤
ይህም ለሕይወቴ አምላክ የማቀርበው ጸሎት ነው።
9እግዚአብሔር ዐለቴን፣
“ለምን ረሳኸኝ?
ጠላትስ እያስጨነቀኝ፣
ለምን በሐዘን እመላለሳለሁ?” እለዋለሁ።
10ጠላቶቼ ቀኑን ሙሉ፣
“አምላክህ የት አለ?” እያሉ፣
በነገር ጠዘጠዙኝ፣
ዐጥንቴም ደቀቀ።
11ነፍሴ ሆይ፤ ለምን ትተክዢያለሽ?
ለምንስ በውስጤ ትታወኪያለሽ?
ተስፋሽን በአምላክ ላይ አድርጊ፣
አዳኜና አምላኬን
ገና አመሰግነዋለሁና።

Currently Selected:

መዝሙር 42: NASV

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ