መዝሙር 57
57
መዝሙር 57
57፥7-11 ተጓ ምብ – መዝ 108፥1-5
ለመዘምራን አለቃ፤ “አታጥፋ” በሚለው ቅኝት የሚዘመር፤ ከሳኦል ፊት ሸሽቶ በዋሻ በነበረበት ጊዜ፤ የዳዊት ሚክታም።#57 ርእስ የሥነ ጽሑፉን ቅርጽ የሚያሳይ ወይም በሙዚቃ ውስጥ የሚጠቀሙበት ቃል ሳይሆን አይቀርም።
1ማረኝ፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ ማረኝ፤
ነፍሴ አንተን መጠጊያ አድርጋለችና፤
በክንፎችህ ሥር እጠለላለሁ።
2ለእኔ ያሰበውን ወደሚፈጽምልኝ አምላክ፣
ወደ ልዑል እግዚአብሔር እጮኻለሁ።
3ከሰማይ ልኮ ያድነኛል፤
የረገጡኝን ያዋርዳቸዋል፤ ሴላ
እግዚአብሔር ምሕረቱንና ታማኝነቱን ይልካል።
4ነፍሴ በአንበሶች ተከብባለች፤
በሚዘነጣጥሉ አራዊት መካከል ወድቄአለሁ፤
እነዚህም፣ ጥርሳቸው ጦርና ፍላጻ፣
ምላሳቸውም የተሳለ ሰይፍ የሆኑ ሰዎች ናቸው።
5እግዚአብሔር ሆይ፤ ከሰማያት በላይ ከፍ ከፍ በል፤
ክብርህም በምድር ሁሉ ላይ ትንሰራፋ።
6ለእግሬ ወጥመድን ዘረጉ፤
ነፍሴንም አጐበጧት፤
በመተላለፊያዬ ላይ ጕድጓድ ቈፈሩ፤
ነገር ግን ራሳቸው ገቡበት። ሴላ
7እግዚአብሔር ሆይ፤ ልቤ ጽኑ ነው፤
ልቤ ጽኑ ነው፤
እቀኛለሁ፤ እዘምራለሁ።
8ነፍሴ ሆይ፤ ንቂ!
በገናና መሰንቆም ተነሡ!
እኔም ማልጄ እነሣለሁ።
9ጌታ ሆይ፤ በሕዝቦች መካከል አመሰግንሃለሁ፤
በሰዎችም መካከል እዘምርልሃለሁ፤
10ምሕረትህ እስከ ሰማያት ከፍ ብላለችና፤
ታማኝነትህም እስከ ሰማያት ትደርሳለች።
11እግዚአብሔር ሆይ፤ ከሰማያት በላይ ከፍ ከፍ በል፤
ክብርህም በምድር ሁሉ ላይ ትንሰራፋ።
Currently Selected:
መዝሙር 57: NASV
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
መጽሐፍ ቅዱስ፣ አዲሱ መደበኛ ትርጕም™
የቅጂ መብት © 2001, 2024 በBiblica, Inc.
በፈቃድ የሚወሰድ። በዓለም ዐቀፍ ባለቤትነቱ።
The Holy Bible, New Amharic Standard Version™
Copyright © 2001, 2024 by Biblica, Inc.
Used with permission. All rights reserved worldwide.