ትንቢተ ዳንኤል 12
12
የመጨረሻው ዘመን
1ያ ራእዩን ያብራራልኝ የነበረው መልአክ እንደገና እንዲህ አለኝ፦ “ሕዝብህን የሚጠብቀው ታላቁ አለቃ ሚካኤል በዚያን ጊዜ ይገለጣል፤ የሰው ዘር ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ ታይቶ የማይታወቅ ታላቅ መከራ ይሆናል፤ ነገር ግን ስማቸው በእግዚአብሔር መጽሐፍ የተጻፈ የአገርህ ሕዝቦች ብቻ በዚያን ጊዜ ይድናሉ፤ #ማቴ. 24፥21፤ ማር. 13፥19፤ ራዕ. 7፥14፤ 12፥7። 2ሞተው ዐፈር የበላቸው ሁሉ ይነሣሉ፤ ከእነርሱም ከፊሎቹ ወደ ዘለዓለማዊ ሕይወት ሲገቡ ከፊሎቹ ደግሞ ወደ ዘለዓለማዊ ኀፍረትና ውርደት ይላካሉ። #ኢሳ. 26፥19፤ ማቴ. 25፥46፤ ዮሐ. 5፥29። 3በዚያን ጊዜ ጠቢባን እንደ ሰማይ ብርሃን ያንጸባርቃሉ፤ ብዙ ሰዎችን በማስተማር ከክፉ መንገድ ወደ ደግ ሥራ የመለሱ ሁሉ ለዘለዓለም እንደ ሰማይ ከዋክብት ያበራሉ።”
4እንደገናም እንዲህ አለኝ፦ “ዳንኤል ሆይ! የዓለም መጨረሻ እስከሚሆንበት ጊዜ ድረስ መጽሐፉን ዘግተህ አሽገው፤ የትንቢቱንም ቃል በምሥጢር ያዝ፤ በዚያን ጊዜ ሰዎች ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ይራወጣሉ፤ ምርምርና ዕውቀትም ይበዛል።” #ራዕ. 22፥10።
5ከዚያን በኋላ በወንዝ ዳር ሁለት ሰዎች ማዶ ለማዶ ቆመው አየሁ፤ 6ከእነርሱ አንዱ ቀጭን ሐር ለብሶ ከወንዙ በላይ በኩል የቆመውን መልአክ “ይህ ሁሉ አስደናቂ ነገር ፍጻሜ እስከሚያገኝ ምን ያኽል ጊዜ ይወስዳል?” ብሎ ጠየቀው።
7ቀጭን ሐር ለብሶ ከወንዝ በላይ በኩል የቆመው መልአክ ሁለት እጆቹን ወደ ሰማይ ዘርግቶ በዘለዓለማዊው አምላክ ስም በመማል “ሦስት ዓመት ተኩል ይወስዳል፤ በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ የሚደርሰው መከራ ሲያከትም እነዚህ ሁሉ ነገሮች ተፈጻሚነት ያገኛሉ።” #ራዕ. 10፥5፤ 12፥14።
8መልአኩ የተናገረውን ሁሉ ሰማሁ፤ ነገር ግን ሊገባኝ አልቻለም፤ ስለዚህ “ጌታዬ ሆይ! የዚህ ሁሉ የመጨረሻው ውጤት ምን ይሆን?” ብዬ ጠየቅሁት።
9እርሱም እንዲህ ሲል መለሰልኝ፦ “ዳንኤል ሆይ! የዓለም መጨረሻ እስከሚሆንበት ጊዜ ድረስ ቃሉ የትንቢቱም ቃል ምሥጢር ሆኖ ስለሚጠበቅ እንግዲህ አንተ ሂድ። 10ብዙዎች ነጥረውና ጠርተው በመውጣት ነውር የሌለባቸው ይሆናሉ፤ ክፉዎች ግን ምንም ስለማያስተውሉ በክፋት ላይ ክፋት እየጨመሩ ይሄዳሉ፤ የማስተዋል ችሎታ የሚኖራቸው ጠቢባን ብቻ ናቸው። #ራዕ. 22፥11።
11“የዘወትሩ መሥዋዕት ተቋርጦ አጸያፊ የሆነው የጥፋት ርኲሰት እንዲቆም ከተደረገበት ጊዜ ጀምሮ አንድ ሺህ ሁለት መቶ ዘጠና ቀኖች ያልፋሉ። #ዳን. 9፥27፤ 11፥31፤ ማቴ. 24፥15፤ ማር. 13፥14። 12አንድ ሺህ ሦስት መቶ ሠላሳ አምስት ቀኖች እስከሚያልፉ ድረስ እምነቱን ጠብቆ የሚኖር የተባረከ ነው።
13“አንተም ዳንኤል ሆይ! እስከ መጨረሻው በታማኝነትህ ጸንተህ ኑር፤ ከዚያ በኋላ ታርፋለህ፤ በዚህ ዐይነት ከሞትህ ተነሥተህ በመጨረሻው ቀን የክብር ዋጋህን ታገኛለህ።”
Currently Selected:
ትንቢተ ዳንኤል 12: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997