የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ትንቢተ ሕዝቅኤል 10

10
የእግዚአብሔር ክብር ከቤተ መቅደሱ መራቁ
1ከኪሩቤል ራሶች በላይ ያለውን ጠፈር ተመለከትኩ፤ በኪሩቤል ላይ ከሰንፔር ዕንቊ የተሠራ ዙፋን የሚመስል ነገር አየሁ። #ሕዝ. 1፥26፤ ራዕ. 4፥2። 2እግዚአብሔርም ቀጭን ሐር የለበሰውን ሰው “ከሕያዋን ፍጥረቶች በታች ባሉት መንኰራኲሮች መካከል አልፈህ ሂድ፤ ከከሰልም ፍም በእጅህ አፍሰህ ውሰድና በከተማይቱ ላይ በትነው!” አለው። #ራዕ. 8፥5።
እኔም እያየሁት ገባ፤ 3ወደ ውስጥ በሚገባበትም ጊዜ ኪሩቤል ከቤተ መቅደሱ በስተ ደቡብ በኩል ቆመው ነበር፤ በውስጥ በኩል ያለውንም አደባባይ ደመና ሞላው፤ 4የእግዚአብሔር ክብር ከኪሩብ ተነሥቶ ወደ ቤተ መቅደሱ መድረክ ሄደ፤ ደመና ቤቱን ሞላው፤ አደባባዩም በእግዚአብሔር ክብር ነጸብራቅ ተሞላ። 5ኪሩቤል በክንፎቻቸው የሚያሰሙት ድምፅ በውጪ በኩል ባለው አደባባይ እንኳ ይሰማ ነበር፤ ድምፁም ሁሉን የሚችል አምላክ ድምፅ ይመስል ነበር።
6እግዚአብሔር ያንን በፍታ የለበሰውን ሰው ከኪሩቤል ሥር ከነበሩት መንኰራኲሮች መካከል እሳት እንዲወስድ ባዘዘው ጊዜ ወዲያውኑ ወደ ውስጥ ገብቶ ከመንኰራኲሮቹ በአንደኛው አጠገብ ቆመ፤ 7ከኪሩቤልም አንዱ በመካከላቸው ባለው እሳት ውስጥ እጁን ሰድዶ ጥቂት ፍሞች አነሣና በፍታ በለበሰው ሰው እጅ ላይ አኖረው፤ ሰውየውም ፍሙን ይዞ ሄደ።
8እኔም እያንዳንዱ ኪሩብ የሰው እጅ የሚመስል እጅ በየክንፎቹ ሥር ያለው መሆኑን ተመለከትኩ፤ 9ስመለከት እያንዳንዱ መንኰራኲር በያንዳንዱ ኪሩብ አጠገብ ሆኖ አራት መንኰራኲሮችን አየሁ፤ የመንኰራኲሮቹም መልክ የሚያንጸባርቅ ዕንቊ ይመስል ነበር። #ሕዝ. 1፥15-21። 10የአራቱ መንኰራኲሮች መልክ ተመሳሳይ ነበር፤ እነርሱም በመንኰራኲር ውስጥ የሚተላለፉ መንኰራኲሮች ይመስሉ ነበር። 11ወደ ፊታቸው በሚንቀሳቀሱበት ጊዜ ወደ የትኛውም አቅጣጫ ሳይዞሩ በቀጥታ ይሄዳሉ፤ የፊቱ መንኰራኲር ወደ የትኛውም አቅጣጫ ቢሄድ ሌሎቹ ሳይዞሩ በቀጥታ ይከተላሉ። 12መላ አካላቸውም ሆነ ጀርባቸው፥ እጆቻቸውም ሆኑ ክንፎቻቸው መንኰራኲሮቹ እንኳ ሳይቀሩ ሁሉም ብዙ ዐይኖች ነበሩአቸው፤ #ራዕ. 4፥8። 13መንኰራኵሮቹም እኔ እየሰማሁ የሚሽከረከሩ መንኰራኩሮች ተብለው ተጠሩ።
14እያንዳንዱ ኪሩብ አራት ፊቶች ነበሩት፤ የመጀመሪያው የበሬ ፊት፥ ሁለተኛው የሰው፥ ሦስተኛው የአንበሳ፥ አራተኛው ደግሞ የንስር ፊት ይመስል ነበር። #ሕዝ. 1፥10፤ ራዕ. 4፥7። 15ኪሩቤል ወደ ላይ ተነሡ እነርሱም በኬባር ወንዝ አጠገብ ያየኋቸው ሕያዋን ፍጥረቶች ናቸው። 16ኪሩቤሉ ሲንቀሳቀሱ ከጐናቸው ያሉት መንኰራኲሮችም አብረው ይንቀሳቀሳሉ፤ ኪሩቤሉ ለመነሣት ክንፋቸውን ሲዘረጉ ከጐናቸው ያሉት መንኰራኲሮችም ወደ ሌላ አይዞሩም። 17የሕያዋን ፍጥረቶች መንፈስ በመንኰራኲሮቹ ውስጥ ስላለ ፍጥረቶቹ ሲቆሙ መንኰራኲሮቹም አብረው ይቆማሉ፤ ኪሩቤሉ ሲነሡ መንኰራኲሮቹም ወደ ሌላ አይዞሩም።
18ከዚህ በኋላ የእግዚአብሔር ክብር ከቤተ መቅደሱ መድረክ ተነሥቶ ከኪሩቤል በላይ ወዳለው ስፍራ ወጥቶ ቆመ። 19እኔም ይህን በመመልከት ላይ ሳለሁ፥ ኪሩቤል ክንፎቻቸውን ዘርግተው ከመሬት ወደ ላይ በሚወጡበት ጊዜ ከጐናቸው የነበሩትም መንኰራኲሮቹ አብረዋቸው ሲወጡ አየሁ፤ በቤተ መቅደሱ በስተ ምሥራቅ ባለው የቅጽር በር ሲደርሱ ቆሙ፤ የእስራኤል አምላክም ክብር በእነርሱ ላይ ነበር። 20እነዚህም በኬባር ወንዝ አጠገብ ከእስራኤል አምላክ ሥር ያየኋቸው ሕያዋን ፍጥረቶች ናቸው፤ እኔም ኪሩቤል መሆናቸውን ዐወቅሁ።
21እያንዳንዳቸውም አራት ፊቶችና አራት ክንፎች ነበሩአቸው፤ በእያንዳንዱም ክንፍ ሥር የሰው እጅ የመሰለ ነገር ነበረ። 22ፊቶቻቸውም እነዚያኑ በኬባር ወንዝ አጠገብ ያየኋቸውን ፊቶች ይመስሉ ነበር፤ እያንዳንዱም ኪሩብ በቀጥታ ወደ ፊት ይሄድ ነበር።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ