ትንቢተ ሕዝቅኤል 4:4-5

ትንቢተ ሕዝቅኤል 4:4-5 አማ05

“እንግዲህ በግራ ጐንህ ተኝተህ የእስራኤላውያንን ኃጢአት ተሸከም፤ በጐንህ በምትተኛባቸው ቀኖች ቊጥር የእነርሱን ኃጢአት ትሸከማለህ። እስራኤላውያን ኃጢአት በሠሩባቸው ዓመቶች ብዛት ቀኖችን መድቤልሃለሁ፤ ይህም አንድ ቀን ለአንድ ዓመት ማለት ነው፤ ስለዚህ ለሦስት መቶ ዘጠና ቀኖች የእስራኤላውያንን ኃጢአት ትሸከማለህ።