ሕዝቅኤል 4:4-5
ሕዝቅኤል 4:4-5 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
“አንተም በግራ ጎንህ ተኛ፤ በምትተኛበትም ቀን ቍጥር የእስራኤልን ቤት ኀጢአት አኑርባት፤ ኀጢአታቸውንም ትሸከማለህ። እኔም የኀጢአታቸውን ዓመታት ለአንተ የቀን ቍጥር እንዲሆንልህ ሦስት መቶ ዘጠና ቀን ሰጥቼሃለሁ፤ የእስራኤልንም ቤት ኃጢአት ትሸከማለህ፤
ያጋሩ
ሕዝቅኤል 4 ያንብቡሕዝቅኤል 4:4-5 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
“አንተ በግራ ጐንህ ተኛ፤ የእስራኤልም ቤት ኀጢአት በአንተ ላይ ይሁን፤ በዚህ ጐንህ በተኛህበት ቀን ቍጥር ኀጢአታቸውን ትሸከማለህ። እነርሱ ኀጢአት ባደረጉባቸው ዓመታት መጠን የቀን ቍጥር መድቤብሃለሁ። ስለዚህ ሦስት መቶ ዘጠና ቀን የእስራኤልን ቤት ኀጢአት ትሸከማለህ።
ያጋሩ
ሕዝቅኤል 4 ያንብቡሕዝቅኤል 4:4-5 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
አንተም በግራ ጐድንህ ተኛ የእስራኤልንም ቤት ኃጢአት አኑርባት በምትተኛበትም ቀን ቍጥር ኃጢአታቸውን ትሸከማለህ። እኔም የኃጢአታቸውን ዓመታት ለአንተ የቀን ቍጥር እንዲሆንልህ ሦስት መቶ ዘጠና ቀን ሰጥቼሃለሁ፥ የእስራኤልንም ቤት ኃጢአት ትሸከማለህ።
ያጋሩ
ሕዝቅኤል 4 ያንብቡ