የዮሐንስ ወንጌል 19:1-3

የዮሐንስ ወንጌል 19:1-3 መቅካእኤ

በዚያን ጊዜም ጲላጦስ ኢየሱስን ወስዶ ገረፈው። ወታደሮቹም ከእሾህ አክሊል ጐንጉነው በራሱ ላይ አኖሩ፤ ቀይ ልብስም አለበሱት፤ እየቀረቡም “የአይሁድ ንጉሥ ሆይ! ሰላም ለአንተ ይሁን” ይሉት ነበር፤ በጥፊም ይመቱት ነበር።