ዮሐንስ 19:1-3
ዮሐንስ 19:1-3 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ከዚህም በኋላ ጲላጦስ ጌታችን ኢየሱስን ይዞ ገረፈው። ጭፍሮችም የእሾህ አክሊል ጐንጕነው በራሱ ላይ ደፉበት፤ የቀይ ሐር መጐናጸፊያም አለበሱት። ወደ እርሱም እየመጡ፥ “የአይሁድ ንጉሥ ሆይ፥ ሰላም ለአንተ ይሁን” ይሉት ነበር፤ በጥፊም ይመቱት ነበር።
ያጋሩ
ዮሐንስ 19 ያንብቡዮሐንስ 19:1-3 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ጲላጦስም ኢየሱስን ወስዶ አስገረፈው። ወታደሮችም የእሾኽ አክሊል ጐንጕነው በራሱ ላይ አደረጉ፤ ሐምራዊ ልብስም አለበሱት፤ እየተመላለሱም፣ “የአይሁድ ንጉሥ ሆይ! ሰላም ለአንተ ይሁን” እያሉ በጥፊ ይመቱት ነበር።
ያጋሩ
ዮሐንስ 19 ያንብቡዮሐንስ 19:1-3 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
በዚያን ጊዜም ጲላጦስ ኢየሱስን ይዞ ገረፈው። ወታደሮችም ከእሾህ አክሊል ጐንጕነው በራሱ ላይ አኖሩ ቀይ ልብስም አለበሱት፤ እየቀረቡም፦ “የአይሁድ ንጉሥ ሆይ፥ ሰላም ለአንተ ይሁን” ይሉት ነበር፤
ያጋሩ
ዮሐንስ 19 ያንብቡ