መዝሙረ ዳዊት 140
140
1ለመዘምራን አለቃ፥ የዳዊት መዝሙር።
2 #
መዝ. 71፥4። አቤቱ፥ ከክፉ ሰው አድነኝ፥
ከዓመፀኞች ሰዎች ጠብቀኝ
3በልባቸውም ክፉ ካሰቡ፥
ቀኑን ሁሉ ለሰልፍ ከሚከማቹ።
4 #
መዝ. 64፥4፤ ሮሜ 3፥13። ምላሳቸውን እንደ እባብ ሳሉ፥
ከከንፈራቸው በታች የእፉኝት መርዝ አለ።
5 #
ኤር. 18፥22፤ መዝ. 56፥7፤ 57፥7። አቤቱ፥ ከክፉዎች እጅ ጠብቀኝ፥
እርምጃዬንም ሊያሰናክሉ ከመከሩ
ከዓመፀኞች አድነኝ።
6ትዕቢተኞች ወጥመድን ሰወሩብኝ፥
ለእግሮቼም የወጥመድ ገመድን ዘረጉ፥
በመንገድ ዕንቅፋትን አኖሩ።
7 #
መዝ. 31፥15። ጌታንም፦ አንተ አምላኬ ነህ፥
የልመናዬን ቃል፥ አቤቱ፥ አድምጥ አልሁት።
8አቤቱ፥ ጌታዬ፥ የመድኃኒቴ ጉልበት፥
በሰልፍ ቀን ራሴን ሸፈንህ።
9አቤቱ፥ ከምኞቴ የተነሣ ለክፉዎች አትስጠኝ፥
ተንኮላቸው እንዲሳካ አትፍቀድ።
10የሚከብቡኝ ራሳቸውን አነሡ#140፥10 ኮሩብኝ።፥
የከንፈራቸው ክፋት ይክደናቸው።
11 #
መዝ. 11፥6፤ 120፥4፤ ዘፍ. 19፥24። የእሳት ፍም በላያቸው ይውደቅ፥
እንዳይነሡም ወደ እሳትና ወደ አዘቅት ይጣሉ።
12ተናጋሪ ሰው በምድር ውስጥ አይጸናም፥
ዓመፀኛን ሰው ክፋት ለጥፋት ይፈልገዋል።
13ጌታ ለድሀ ዳኝነትን
ለችግረኛም ፍርድን እንደሚያደርግ አወቅሁ።
14 #
መዝ. 11፥7፤ 16፥11፤ 17፥15። ጻድቃንም በእውነት ስምህን ያመሰግናሉ፥
ቅኖችም በፊትህ ይኖራሉ።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 140: መቅካእኤ
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ
![None](/_next/image?url=https%3A%2F%2Fimageproxy.youversionapistaging.com%2F58%2Fhttps%3A%2F%2Fweb-assets.youversion.com%2Fapp-icons%2Fam.png&w=128&q=75)
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ