መዝሙረ ዳዊት 142
142
1ጸሎት፥ በዋሻ በነበረ ጊዜ፥ የዳዊት ትምህርት።
2በሙሉ ድምጼ ወደ ጌታ ጮኽሁ፥
በሙሉ ድምጼ ወደ ጌታ ለመንሁ።
3ሮሮዬን በፊቱ አፈስሳለሁ፥
መከራዬንም በፊቱ እናገራለሁ።
4 #
መዝ. 139፥24፤ 141፥9፤ 143፥4። መንፈሴ በዛለ ጊዜ መንገዴን አወቅሁ፥
በምሄድባት በዚያች መንገድ ወጥመድን ሰወሩብኝ።
5 #
መዝ. 16፥8፤ 73፥23፤ 121፥5። ወደ ቀኝ ተመለከትሁ አየሁም፥
የሚያውቀኝም አጣሁ፥
መሸሸጊያም የለኝም፥ ስለ ነፍሴም የሚያስብ የለም።
6 #
መዝ. 91፥2፤9፤ መዝ. 16፥5፤ 27፥13፤ 116፥9፤ ኢሳ. 38፥11። አቤቱ፥ ወደ አንተ ጮኽሁ፦
አንተ መጠጊያዬ ነህ፥
በሕያዋንም ምድር አንተ እድል ፈንታዬ ነህ አልሁ።
7 #
መዝ. 79፥8። እጅግ ተቸግሬአለሁና ጩኸቴን አድምጥ፥
በርትተውብኛልና ከሚያሳድዱኝ አድነኝ።
8አቤቱ፥ ስምህን አመሰግን ዘንድ
ነፍሴን ከወህኒ አውጣት፥
ስለ ምታጠግበኝ
ጻድቃን እኔን ይከባሉ።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 142: መቅካእኤ
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ
![None](/_next/image?url=https%3A%2F%2Fimageproxy.youversionapistaging.com%2F58%2Fhttps%3A%2F%2Fweb-assets.youversion.com%2Fapp-icons%2Fam.png&w=128&q=75)
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ