መዝሙረ ዳዊት 23
23
1የዳዊት መዝሙር።
#
መዝ. 80፥2፤ 95፥7፤ 100፥3፤ ዘዳ. 2፥7። ጌታ እረኛዬ ነው፥ የሚያሳጣኝም የለም።
2 #
ራእ. 7፥17። በለመለመ መስክ ያሳድረኛል፥
በዕረፍት ውኃ ዘንድ ይመራኛል
3 #
ምሳ. 4፥11። ነፍሴን መለሳት፥
ስለ ስሙም በጽድቅ መንገድ መራኝ።
4 #
ኢዮብ 10፥21-22፤ ኢሳ. 50፥10። በሞት ጥላ ሸለቆ ውስጥ እንኳ ብሄድ
አንተ ከእኔ ጋር ነህና ክፉን አልፈራም፥
በትርህና ምርኩዝህ እነርሱ ያጸናኑኛል።
5 #
መዝ. 16፥5፤ መዝ. 92፥11። በፊቴ ገበታን አዘጋጀህልኝ
በጠላቶቼ ፊት ለፊት
ራሴን በዘይት ቀባህ፥
ጽዋዬንም እስከ አፉ ሞላህ።
6 #
መዝ. 27፥4። ቸርነትና ምሕረት በሕይወቴ ዘመን ሁሉ ይከተሉኛል፥
በእግዚአሔርም ቤት ለዘለዓለም እኖራለሁ።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 23: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ