መዝሙረ ዳዊት 51
51
1ለመዘምራን አለቃ፥ የዳዊት መዝሙር። 2#2ሳሙ. 12።ወደ ቤርሳቤህ ከገባ በኋላ ነቢዩ ናታን ወደ እርሱ በመጣ ጊዜ፥
3አቤቱ፥ እንደ ቸርነትህ መጠን ማረኝ፥
እንደ ምሕረትህም ብዛት መተላለፌን ደምስስ።
4ከበደሌ ፈጽሞ እጠበኝ፥
ከኃጢአቴም አንጻኝ፥
5 #
መዝ. 32፥5፤ 38፥19፤ ኢሳ. 59፥12። እኔ መተላለፌን አውቃለሁና፥
ኃጢአቴም ሁልጊዜ በፊቴ ነውና።
6 #
ሮሜ 3፥4። አንተን ብቻ በደልሁ፥
በፊትህም ክፋትን አደረግሁ፥
በነገርህ ትጸድቅ ዘንድ በፍርድህም ንጹሕ ትሆን ዘንድ።
7 #
ኢዮብ 14፥4። እነሆ፥ በዓመፃ ተወለድሁ፥
እናቴም በኃጢአት ፀነሰችኝ።
8እነሆ፥ እውነትን ወደድህ፥
የማይታይ ስውር ጥበብን አስታወቅኸኝ።
9 #
ኢዮብ 9፥30፤ ኢሳ. 1፥18፤ ሕዝ. 36፥25። በሂሶጵ እርጨኝ፥ እነጻማለሁ፥
እጠበኝ፥ ከበረዶም ይልቅ ነጭ እሆናለሁ።
10ሐሤትንና ደስታን አሰማኝ፥
የሰበርሃቸውም አጥንቶቼ ደስ ይላቸዋል።
11ከኃጢአቴ ፊትህን መልስ፥
በደሌንም ሁሉ ደምስስልኝ።
12 #
ሕዝ. 11፥19። አቤቱ፥ ንጹሕ ልብን ፍጠርልኝ፥
የቀናውንም መንፈስ በውስጤ አድስ።
13 #
ጥበ. 1፥5፤ 9፥17፤ ኢሳ. 63፥11፤ ሐጌ 2፥5፤ ሮሜ 8፥9። ከፊትህ አትጣለኝ፥
ቅዱስ መንፈስህንም ከእኔ ላይ አትውሰድብኝ።
14የማዳንህን ደስታ መልስልኝ፥
በእሽታ መንፈስም ደግፈኝ።
15ለሕግ ተላላፎች መንገድህን አስተምራለሁ፥
ኃጢአተኞችም ወደ አንተ ይመለሳሉ።
16 #
መዝ. 30፥10። የመድኃኒቴ አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፥ ከደም አድነኝ፥
አንደበቴም በአንተ ጽድቅ ትደሰታለች።
17አቤቱ፥ ከንፈሮቼን ክፈት፥
አፌም ምስጋናህን ይናገራል።
18 #
መዝ. 40፥7፤ 50፥8፤ አሞጽ 5፥21-22፤ ሆሴዕ 6፥6፤ ኢሳ. 1፥11-15፤ ዕብ. 10፥5-7። መሥዋዕትን ብትወድድስ በሰጠሁህ ነበር፥
የሚቃጠለውም መሥዋዕት ደስ አያሰኝህም።
19የእግዚአብሔር መሥዋዕት የተሰበረ መንፈስ ነው፥
የተሰበርውንና የተዋረደውን ልብ እግዚአብሔር አይንቅም።
20 #
ኤር. 31፥4፤ ሕዝ. 36፥33። አቤቱ፥ በውዴታህ ጽዮንን አሰማምራት፥
የኢየሩሳሌምንም ቅጽሮች ሥራ።
21የጽድቁን መሥዋዕት
መባውንም የሚቃጠለውንም መሥዋዕት በወደድህ ጊዜ፥
ያንጊዜ በመሠዊያህ ላይ ፍሪዳዎችን ይሠዋሉ።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 51: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ