የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝሙረ ዳዊት 68

68
1ለመዘምራን አለቃ፥ የዳዊት የምስጋና መዝሙር።
2 # ዘኍ. 10፥35። እግዚአብሔር ይነሣ፥ ጠላቶቹም ይበተኑ፥
የሚጠሉትም ከፊቱ ይሽሹ።
3 # መዝ. 97፥5፤ ዮዲ. 16፥15፤ ጥበ. 5፥14፤ ሚክ. 1፥4። ጢስ እንደሚበንን እንዲሁ ይብነኑ፥
ሰም በእሳት ፊት እንደሚቀልጥ፥
እንዲሁ ክፉዎች ከእግዚአብሔር ፊት ይጥፉ።
4ጻድቃንም ደስ ይበላቸው፥
በእግዚአብሔርም ፊት ሐሤት ያድርጉ፥
በደስታም እልል ይበሉ።
5 # መዝ. 18፥10፤ 104፥3፤ ዘዳ. 33፥26፤ ኢሳ. 19፥1። ለእግዚአብሔር ተቀኙ ለስሙም ዘምሩ፥
ወደ ምድረ በዳ ለወጣም መንገድ አድርጉ፥
ስሙ ጌታ ነው፥ በፊቱም ደስ ይበላችሁ።
6 # መዝ. 103፥6፤ 146፥7፤ 9፤ ዘፀ. 22፥20-22፤ ባሮክ 6፥37። እግዚአብሔር በቅዱስ መኖሪያው
ወላጅ ለሞቱባቸው አባት፥ ለባልቴቶችም ዳኛ#68፥6 ጠባቂ ነው ነው።
7እግዚአብሔር ብቸኞችን በቤት ያሳድራቸዋል፥
እስረኞችንም በኃይሉ ያወጣቸዋል፥
ዓመፀኞች ግን በምድረ በዳ ይኖራሉ።
8 # መዝ. 44፥10፤ 114፥4፤ 7፤ መሳ. 5፥4-5፤ ዕብ. 12፥26። አቤቱ፥ በሕዝብህ ፊት በወጣህ ጊዜ፥
በምድረ በዳም ባለፍህ ጊዜ፥
ምድር ተናወጠች፥
9 # ዘፀ. 19፥18። ከሲና አምላክ ፊት፥ ከእስራኤል አምላክ ፊት
ሰማያትም አንጠባጠቡ።
10አቤቱ፥ የተትረፈረፈ ዝናብ ለርስትህ አዘነብህ፥
በደከመም ጊዜ አንተ አጸናኸው።
11እንስሶችህ በውስጡ አደሩ፥
አቤቱ፥ በቸርነትህ ለድሆች አዘጋጀህ።
12ጌታ ትእዛዙን ሰጠ፥
የሚያበሥሩት ብዙ ሠራዊት ናቸው።
13 # መሳ. 5፥19፤22። የሠራዊት ነገሥታት ፈጥነው ይሸሻሉ፥
በቤትም የምትኖር ምርኮን ተካፈለች።
14 # መሳ. 5፥16። በርስቶች መካከል ብታድሩ፥
ከብር እንደ ተሠሩ እንደ ርግብ ክንፎች፥
በቅጠልያ ወርቅም እንደ ተለበጡ ላባዎችዋ ትሆናላችሁ።
15ሰማያዊ ንጉሥ በላይዋ ባዘዘ ጊዜ፥
በሰልሞን ላይ በረዶ ዘነበ።
16መለኮታዊ#68፥16 ኃያል ተራራ ተራራ፥ የባሳን ተራራ#68፥16 ግሪኩ የለመለመ ተራራ ይላል
የጸና ተራራና የባሳን ተራራ።
17 # መዝ. 132፥13-14፤ ሕዝ. 43፥7። ጽኑ ተራራዎች ሆይ ለምን በቅናት ታያላችሁ?
እግዚአብሔር ይህን ተራራ ያድርበት ዘንድ ወደደው፥
በእውነት ጌታ ለዘለዓለም ያድርበታል።
18የእግዚአብሔር ሠረገላዎች የብዙ ብዙ ሺህ ናቸው፥
ጌታ በመቅደሱ በሲና በመካከላቸው ነው።
19 # መዝ. 47፥8፤ ኤፌ. 4፥8-10። ወደ ላይ ዓረግህ፥ ምርኮን ማረክህ፥
ስጦታንም ከሰዎች ወሰድህ፥ ከዓመፀኞችም ጭምር፥
በዚያም ጌታ ያድር ዘንድ።
20 # መዝ. 34፥2፤ 145፥2፤ ኢሳ. 46፥3-4፤ 63፥9። በየዕለቱ የሚንከባከበን ጌታ የተመሰገነ ይሁን፥
እግዚአብሔር ያድነናል።
21አምላካችንስ የሚያድን አምላክ ነው፥
ከሞት ማምለጫውም ከጌታ ነው።
22 # ዘዳ. 32፥42። ነገር ግን እግዚአብሔር የጠላቶቹን ራስ፥
በበደል የሚሄድንም የጠጉሩን አናት ይቀጠቅጣል።
23ጌታ እንዲህ አለ፦ ከባሳን አመጣቸዋለሁ፥
ከባሕርም ጥልቅ እመልሳቸዋለሁ፥
24 # መዝ. 58፥11፤ 1ነገ. 21፥19፤ 22፥38፤ ኢሳ. 63፥1-6። እግሮችህ በደም ይረገጡ ዘንድ፥
የውሾችህ ምላስ በጠላቶች ላይ ይሆን ዘንድ።
25አምላክ ሆይ ጉዞህን አዩት፥
የአምላኬና የንጉሤ ንግደት ወደ ቤተ መቅደስ።
26 # መዝ. 81፥2-3፤ 87፥7፤ 149፥3፤ 150፥3-5፤ 2ሳሙ. 6፥5። አለቆች ቀደሙ፥ መዘምራንም ተከተሉ፥
ከበሮን በሚመቱ በቈነጃጅት መካከል።
27እግዚአብሔርን በጉባኤ፥
የእስራኤል ምንጭ ጌታችንንም አመስግኑት።
28 # ኢሳ. 8፥23። ወጣቱ ብንያም በጉልበቱ በዚያ አለ፥
ገዦቻቸው የይሁዳ አለቆች፥
የዛብሎን አለቆችና የንፍታሌምም አለቆች።
29አቤቱ፥ ኃይልህን እዘዝ፥
አቤቱ፥ ለእኛ የሠራኸውን አጽናው።
30በኢየሩሳሌም ስላለው መቅደስህ
ነገሥታት እጅ መንሻን ለአንተ ያመጣሉ።
31በሸምበቆ ውስጥ ያሉትን አራዊት፥
በአሕዛብ ውስጥ ያሉትን የበሬዎችንና የወይፈኖችን መንጋ ገሥጽ፥
እንደ ብር የተፈተኑት አሕዛብ እንዳይዘጉ፥
ሰልፍን የሚወድዱትን አሕዛብን በትናቸው።
32 # ኢሳ. 18፥7፤ 45፥14። መኳንንት ከግብጽ ይመጣሉ፥
ኢትዮጵያ እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች።
33 # መዝ. 138፥4። የምድር ነገሥታት፥ ለእግዚአብሔር ተቀኙ፥
ለጌታም ዘምሩ።
34በምሥራቅ በኩል በሰማየ ሰማያት ላይ ተቀምጦ ለሚጓዘው
የኃይል ቃል የሆነ ቃሉን፥ እነሆ፥ ይሰጣል።
35ለእግዚአብሔር ክብርን ስጡ፥
ግርማው በእስራኤል ላይ፥
ኃይሉም በደመናት ላይ ነው።
36 # መዝ. 28፥8፤ 29፥11። እግዚአብሔር በቅዱሳኑ ላይ ድንቅ ነው፥
የእስራኤል አምላክ እርሱ ኃይልን ብርታትንም ለሕዝቡ ይሰጣል፥
እግዚአብሔር ይመስገን።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ