የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽ​ሐፈ ሳሙ​ኤል ቀዳ​ማዊ 18

18
ሳኦል በዳ​ዊት እን​ደ​ቀና
1እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ዳዊት ለሳ​ኦል መን​ገ​ሩን በፈ​ጸመ ጊዜ የዮ​ና​ታን ነፍስ በዳ​ዊት ነፍስ ታሰ​ረች፤ ዮና​ታ​ንም እንደ ነፍሱ ወደ​ደው። 2በዚ​ያም ቀን ሳኦል ወሰ​ደው፤ ወደ አባ​ቱም ቤት ይመ​ል​ሰው ዘንድ አል​ፈ​ቀ​ደ​ለ​ትም። 3ዮና​ታ​ንም እንደ ነፍሱ ስለ ወደ​ደው ዮና​ታ​ንና ዳዊት ቃል ኪዳን አደ​ረጉ። 4ዮና​ታ​ንም የለ​በ​ሰ​ውን ካባ አው​ልቆ እር​ሱ​ንና ልብ​ሱን፥ ሰይ​ፉ​ንም፥ ቀስ​ቱ​ንም፥ ዝና​ሩ​ንም ለዳ​ዊት ሸለ​መው። 5ዳዊ​ትም ሳኦል ወደ ላከው ሁሉ ይሄድ ነበር፤ አስ​ተ​ው​ሎም ያደ​ርግ ነበር፤ ሳኦ​ልም በጦ​ረ​ኞች ላይ ሾመው፤ ይህም በሕ​ዝብ ሁሉ ዐይ​ንና በሳ​ኦል ባሪ​ያ​ዎች ዐይን መል​ካም ነበረ።
6እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ዳዊት ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊ​ውን ገድሎ በተ​መ​ለሰ ጊዜ፥ እየ​ዘ​መ​ሩና እየ​ዘ​ፈኑ፥ እል​ልም እያሉ ከበ​ሮና አታሞ ይዘው ዳዊ​ትን#ዕብ. “ንጉ​ሡን ሳኦ​ልን ሊቀ​በሉ” ይላል። ሊቀ​በሉ ሴቶች ከእ​ስ​ራ​ኤል ከተ​ሞች ሁሉ ወጡ። 7ሴቶ​ችም፥ “ሳኦል ሺህ ገደለ፤ ዳዊ​ትም ዐሥር ሺህ ገደለ” እያሉ እየ​ተ​ቀ​ባ​በሉ ይዘ​ፍኑ ነበር። 8ሳኦ​ልም እጅግ ተቈጣ፤ ይህም ነገር ሳኦ​ልን አስ​ከ​ፋው፤ እር​ሱም፥ “ለዳ​ዊት ዐሥር ሺህ ሰጡት፤ ለእኔ ግን ሺህ ብቻ ሰጡኝ፤ ከመ​ን​ግ​ሥት በቀር ምን ቀረ​በት?”#“ከመ​ን​ግ​ሥት በስ​ተ​ቀር ምን ቀረ​በት” የሚ​ለው በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም። አለ። 9ከዚ​ያም ቀን ጀምሮ ሳኦል ዳዊ​ትን ሁል​ጊዜ ይጠ​ባ​በ​ቀው ነበር።
10 # ምዕ. 18 ቍ. 10-11 በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም። እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በነ​ጋው ሳኦ​ልን ክፉ መን​ፈስ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ያዘው፤ በቤ​ቱም ውስጥ ትን​ቢት ተና​ገረ። ዳዊ​ትም በየ​ቀኑ ያደ​ርግ እንደ ነበረ በእጁ በገና ይመታ ነበር። ሳኦ​ልም ጦሩን በእጁ ይዞ ነበር። 11ሳኦ​ልም፥ “ዳዊ​ትን ከግ​ንቡ ጋር አጣ​ብቄ እመ​ታ​ዋ​ለሁ” ብሎ ጦሩን ወረ​ወረ። ዳዊ​ትም ሁለት ጊዜ ከፊቱ ዘወር አለ። 12እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከእ​ርሱ ጋር ስለ ነበረ፥ ከሳ​ኦ​ልም ስለ ተለየ ሳኦል ከዳ​ዊት ፊት የተ​ነሣ ፈራ። 13ስለ​ዚ​ህም ሳኦል ከእ​ርሱ አራ​ቀው፤ የሺህ አለ​ቃም አድ​ርጎ ሾመው፤ በሕ​ዝ​ቡም ፊት ይወ​ጣና ይገባ ነበር። 14ዳዊ​ትም በአ​ካ​ሄዱ ሁሉ ብል​ህና ዐዋቂ ነበር፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከእ​ርሱ ጋር ነበረ። 15ሳኦ​ልም እጅግ ብልህ እንደ ሆነ አይቶ እጅግ ፈራው። 16ነገር ግን በፊ​ታ​ቸው ይወ​ጣና ይገባ ስለ​ነ​በረ እስ​ራ​ኤ​ልና ይሁዳ ሁሉ ዳዊ​ትን ወደዱ።
ዳዊት የሳ​ኦ​ልን ልጅ እንደ አገባ
17ሳኦ​ልም ዳዊ​ትን፥ “ታላ​ቂቱ ልጄ ሜሮብ እነ​ኋት፤ እር​ስ​ዋን እድ​ር​ል​ሃ​ለሁ፤ ብቻ ጀግና ልጅ ሁን​ልኝ፤ ስለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ጦር​ነት ተጋ​ደል” አለው። ሳኦ​ልም፥ “የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን እጅ በእ​ርሱ ላይ ትሁን እንጂ የእኔ እጅ በእ​ርሱ ላይ አት​ሁን” ይል ነበር። 18ዳዊ​ትም ሳኦ​ልን፥ “ለን​ጉሥ አማች እሆን ዘንድ እኔ ማን ነኝ? ሰው​ነ​ቴስ ምን​ድን ናት? የአ​ባ​ቴስ ወገን በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ ምን​ድን ነው?” አለው። 19ነገር ግን የሳ​ኦል ልጅ ሜሮብ ዳዊ​ትን የም​ታ​ገ​ባ​በት ጊዜ ሲደ​ርስ ለሚ​ሆ​ላ​ዊው ለአ​ድ​ር​ኤል ተዳ​ረች። 20የሳ​ኦ​ልም ልጅ ሜል​ኮል ዳዊ​ትን ወደ​ደች፤ ይህም ወሬ ለሳ​ኦል ደረ​ሰ​ለት፤ ነገ​ሩም ደስ አሰ​ኘው። 21ሳኦ​ልም፥ “እር​ስ​ዋን እሰ​ጠ​ዋ​ለሁ፤ እር​ስ​ዋም እን​ቅ​ፋት ትሆ​ን​በ​ታ​ለች” አለ። እነ​ሆም፥ የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን እጅ በሳ​ኦል ላይ ነበ​ረች።#ዕብ. “በእ​ርሱ ላይ ትሆን ዘንድ እር​ስ​ዋን እድ​ር​ለ​ታ​ለሁ አለ ሳኦ​ልም ዳዊ​ትን ዛሬ ሁለ​ተኛ አማች ትሆ​ነ​ኛ​ለህ አለው” የሚል ይጨ​ም​ራል።
22ሳኦ​ልም ብላ​ቴ​ኖ​ቹን፥ “እነሆ፥ ንጉሥ እጅግ ወድ​ዶ​ሃል፤ ቤተ ሰቡም ሁሉ ወድ​ደ​ው​ሃል፤ አሁ​ንም ለን​ጉሥ አማች ሁን ብላ​ችሁ በስ​ውር ለዳ​ዊት ንገ​ሩት” ብሎ አዘ​ዛ​ቸው። 23የሳ​ኦ​ልም ብላ​ቴ​ኖች ይህን ቃል በዳ​ዊት ጆሮ ተና​ገሩ፤ ዳዊ​ትም፥ “እኔ የተ​ዋ​ረ​ድ​ሁና ክብር የሌ​ለኝ ሰው ስሆን ለን​ጉሥ አማች እሆን ዘንድ ለእ​ና​ንተ ትንሽ ነገር ይመ​ስ​ላ​ች​ኋ​ልን?” አለ። 24የሳ​ኦ​ልም ብላ​ቴ​ኖች፦ ዳዊት እን​ዲህ ብሎ ተና​ገረ ብለው ነገ​ሩት። 25ሳኦ​ልም አላ​ቸው፥ “የን​ጉ​ሥን ጠላ​ቶች ይበ​ቀል ዘንድ ከመቶ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ሸለ​ፈት በቀር ንጉሥ ማጫ አይ​ሻም ብላ​ችሁ ለዳ​ዊት ንገ​ሩት” አላ​ቸው። ሳኦል ግን ይህን ማለቱ በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን እጅ ይጥ​ለው ዘንድ አስቦ ነው። 26የሳ​ኦ​ልም ብላ​ቴ​ኖች ይህን ቃል ለዳ​ዊት ነገ​ሩት፤ ለን​ጉ​ሥም አማች ይሆን ዘንድ ዳዊ​ትን ደስ አሰ​ኘው። 27ዳዊ​ትና ሰዎ​ቹም ተነ​ሥ​ተው ሄዱ፤ ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ሁለት መቶ#ግሪክ ሰባ. ሊ. “አንድ መቶ” ይላል። ሰዎ​ችን ገደሉ፤ ዳዊ​ትም ለን​ጉሥ አማች ይሆን ዘንድ ሰለ​ባ​ቸ​ውን አም​ጥቶ በቍ​ጥ​ራ​ቸው ልክ ለን​ጉሡ ሰጠ። ሳኦ​ልም ልጁን ሜል​ኮ​ልን ዳረ​ለት። 28ሳኦ​ልም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከዳ​ዊት ጋር እንደ ሆነ አየ፤ እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ ወደ​ዱት። 29ሳኦ​ልም ዳዊ​ትን አጥ​ብቆ ፈራው፤ ሳኦ​ልም ዕድ​ሜ​ውን ሁሉ ለዳ​ዊት ጠላት ሆነ። 30የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም አለ​ቆች ይወጡ ነበር፤ በወ​ጡም ጊዜ ሁሉ ከሳ​ኦል አገ​ል​ጋ​ዮች ሁሉ ይልቅ ዳዊት አስ​ተ​ውሎ ያደ​ርግ ነበ​ርና ስሙ እጅግ ተጠ​ርቶ ነበር።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ