የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

የሐ​ዋ​ር​ያት ሥራ 11

11
ጴጥ​ሮ​ስን ስለ ተቃ​ወ​ሙት ባል​ን​ጀ​ሮች
1ሐዋ​ር​ያ​ትና በይ​ሁዳ የነ​በሩ ወን​ድ​ሞ​ችም አሕ​ዛብ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል እንደ ተቀ​በሉ ሰሙ። 2ጴጥ​ሮ​ስም ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም በወጣ ጊዜ ከአ​ይ​ሁድ ወገን የሆ​ኑት ወን​ድ​ሞች ተቃ​ወ​ሙት። 3“ወደ አል​ተ​ገ​ረ​ዙት ሰዎች ቤት ገብ​ተህ አብ​ረ​ሃ​ቸው በል​ተ​ሃል” አሉት። 4ጴጥ​ሮ​ስም ከመ​ጀ​መ​ሪያ ጀምሮ ይነ​ግ​ራ​ቸው ጀመረ፤ እን​ዲ​ህም አላ​ቸው። 5“በኢ​ዮጴ ከተማ ሳለሁ ስጸ​ልይ ተመ​ስጦ መጣ​ብ​ኝና ራእይ አየሁ፤ ታላቅ መጋ​ረጃ የመ​ሰለ ዕቃ በአ​ራቱ ማዕ​ዘን ተይዞ ከሰ​ማይ ወረደ፤ ወደ እኔም መጣ። 6በው​ስ​ጡም አራት እግር ያላ​ቸው እን​ስ​ሳ​ንና አራ​ዊ​ትን፥ ተን​ቀ​ሳ​ቃ​ሾ​ች​ንም፥ የሰ​ማይ ወፎ​ች​ንም አየሁ። 7‘ጴጥ​ሮስ ሆይ፥ ተነ​ሥና አር​ደህ ብላ’ የሚ​ለ​ኝ​ንም ቃል ሰማሁ። 8‘አቤቱ፥ ከቶ አይ​ሆ​ንም፤ ንጹሕ ያል​ሆነ ርኩስ ነገር ወደ አፌ ገብቶ አያ​ው​ቅም’ አልሁ። 9ደግ​ሞም፦ ‘እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ንጹሕ ያደ​ረ​ገ​ውን አንተ አታ​ር​ክ​ሰው’ የሚል ቃል ከሰ​ማይ መለ​ሰ​ልኝ። 10እን​ዲ​ህም መላ​ልሶ ሦስት ጊዜ ነገ​ረኝ፤ ዳግ​መ​ኛም ሁሉ ተጠ​ቅ​ልሎ ወደ ሰማይ ተመ​ለሰ። 11በዚ​ያ​ችም ሰዓት ከቂ​ሳ​ርያ ወደ እኔ የተ​ላኩ ሦስት ሰዎች መጡ፤ እኔ ባለ​ሁ​በት ግቢ በርም ቆሙ። 12መን​ፈስ ቅዱ​ስም፦ ‘ሳት​ጠ​ራ​ጠር አብ​ረ​ሃ​ቸው ሂድ’ አለኝ፤ እነ​ዚህ ስድ​ስቱ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ንም ተከ​ት​ለ​ውኝ መጡና ወደ​ዚያ ሰው ቤት ገባን። 13እር​ሱም በቤቱ ቆሞ ሳለ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መል​አክ እን​ዳየ ‘ወደ ኢዮጴ ከተማ ልከህ ጴጥ​ሮስ የተ​ባ​ለ​ውን ስም​ዖ​ንን ይጥ​ሩ​ልህ። 14አን​ተና ቤተ ሰቦ​ችህ ሁሉ የም​ት​ድ​ኑ​በ​ትን ነገር እርሱ ይነ​ግ​ር​ሃል’ እንደ አለው ነገ​ረን። 15ላስ​ተ​ም​ራ​ቸው በጀ​መ​ርሁ ጊዜም ቀድሞ በእኛ ላይ እንደ ወረደ ሁሉ መን​ፈስ ቅዱስ በእ​ነ​ር​ሱም ላይ ወረደ። 16#የሐዋ. 1፥5። ‘ዮሐ​ንስ በውኃ አጠ​መቀ፤ እና​ንተ ግን፤ በመ​ን​ፈስ ቅዱስ ትጠ​መ​ቃ​ላ​ችሁ’ ያለ​ውን የጌ​ታ​ች​ንን ቃል ዐሰ​ብሁ። 17እን​ግ​ዲህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ለአ​መ​ን​ነው ለእኛ እንደ ሰጠን፥ ያን ጸጋ​ውን እንደ እኛ አስ​ተ​ካ​ክሎ ከሰ​ጣ​ቸው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ልከ​ለ​ክል የም​ችል እኔ ማነኝ?” 18ይህ​ንም በሰሙ ጊዜ ዝም አሉ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለአ​ሕ​ዛብ ደግሞ ለሕ​ይ​ወት የሚ​ሆን ንስ​ሓን ሰጣ​ቸው እንጃ” እያሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ሰ​ገኑ።
በእ​ስ​ጢ​ፋ​ኖስ ሞት ስለ ተበ​ተ​ኑት ምእ​መ​ናን
19 # የሐዋ. 8፥1-4። በእ​ስ​ጢ​ፋ​ኖስ ሞት ምክ​ን​ያት የተ​በ​ተ​ኑት ግን፤ ወደ ፊንቄ ወደ ቆጵ​ሮ​ስና ወደ አን​ጾ​ኪያ ደረሱ፤ ቃሉ​ንም ለአ​ይ​ሁድ ብቻ እንጂ ለአ​ን​ድስ እንኳ አይ​ና​ገ​ሩም ነበር። 20ከመ​ካ​ከ​ላ​ቸ​ውም ወደ አን​ጾ​ኪያ ሄደው ለአ​ረ​ማ​ው​ያን የጌ​ታ​ችን የኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን ነገር ያስ​ተ​ማሩ የቆ​ጵ​ሮ​ስና የቄ​ሬና ሰዎች ነበሩ። 21የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እጅ ከእ​ነ​ርሱ ጋር ነበረ፤ ወደ ጌታም ተመ​ል​ሰው ያመኑ ሰዎች ቍጥ​ራ​ቸው በዛ።
22ስለ እነ​ርሱ የተ​ነ​ገ​ረ​ውም ይህ ነገር በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ባለ​ችው ቤተ ክር​ስ​ቲ​ያን ዘንድ ተሰማ፤ በር​ና​ባ​ስ​ንም ወደ አን​ጾ​ኪያ ላኩት። 23በደ​ረሰ ጊዜም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጸጋ አየና ደስ አለው፤ በፍ​ጹም ልባ​ቸ​ውም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸን​ተው ይኖሩ ዘንድ መከ​ራ​ቸው። 24ደግ ሰው፥ መን​ፈስ ቅዱስ ያደ​ረ​በት፥ ሃይ​ማ​ኖ​ተ​ኛም ነበ​ርና፤ በጌ​ታ​ች​ንም አም​ነው ብዙ​ዎች አሕ​ዛብ ተጨ​መሩ።
ደቀ መዛ​ሙ​ርት ክር​ስ​ቲ​ያን ስለ መባ​ላ​ቸው
25ከዚ​ህም በኋላ በር​ና​ባስ ሳው​ልን ሊፈ​ልግ ወደ ጠር​ሴስ ሄደ፤ በአ​ገ​ኘ​ውም ጊዜ ወደ አን​ጾ​ኪያ ወሰ​ደው። 26በቤተ ክር​ስ​ቲ​ያ​ንም አንድ ዓመት አብ​ረው ተቀ​መጡ፤ ብዙ ሕዝ​ብ​ንም አስ​ተ​ማሩ፤ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ትም መጀ​መ​ሪያ በአ​ን​ጾ​ኪያ ክር​ስ​ቲ​ያን ተብ​ለው ተጠሩ።
27ያን​ጊ​ዜም ነቢ​ያት ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ወደ አን​ጾ​ኪያ ወረዱ። 28#የሐዋ. 21፥10። ከመ​ካ​ከ​ላ​ቸ​ውም አጋ​ቦስ የተ​ባለ አንድ ሰው ተነ​ሥቶ በዓ​ለም ሁሉ ጽኑ ረኃብ እን​ደ​ሚ​መጣ በመ​ን​ፈስ ቅዱስ ተገ​ል​ጦ​ለት ተና​ገረ፤ ይህም በቄ​ሣር ቀላ​ው​ዴ​ዎስ ዘመን ሆነ። 29ከዚ​ህም በኋላ ደቀ መዛ​ሙ​ርት እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸው የሚ​ች​ሉ​ትን ያህል አወ​ጣ​ጥ​ተው በይ​ሁዳ ሀገር ለሚ​ኖ​ሩት ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው ርዳ​ታን ይልኩ ዘንድ ወሰኑ። 30እን​ደ​ዚ​ህም አድ​ር​ገው በበ​ር​ና​ባ​ስና በሳ​ውል እጅ ወደ ቀሳ​ው​ስት ላኩት።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ