የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘዳ​ግም 13

13
1“ከአ​ን​ተም ነቢይ ወይም ሕልም አላሚ ቢነሣ፥ ምል​ክ​ትም፥ ተአ​ም​ራ​ትም ቢሰ​ጥህ፥ 2እር​ሱም፦ ሄደን የማ​ታ​ው​ቃ​ቸ​ውን ሌሎች አማ​ል​ክት እን​ከ​ተል እና​ም​ል​ካ​ቸ​ውም ብሎ የተ​ና​ገ​ረህ ምል​ክቱ ወይም ተአ​ም​ራቱ ቢፈ​ጸም፥ 3አም​ላ​ካ​ች​ሁን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በፍ​ጹም ልባ​ችሁ፥ በፍ​ጹ​ምም ነፍ​ሳ​ችሁ ትወ​ድ​ዱት እን​ደ​ሆን ያውቅ ዘንድ አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሊፈ​ት​ና​ችሁ ነውና የዚ​ያን ነቢይ ቃል ወይም ያን ሕልም አላሚ አት​ስሙ። 4አም​ላ​ካ​ች​ሁን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ተከ​ተሉ፤ እር​ሱ​ንም ፍሩ፤ ትእ​ዛ​ዙ​ንም ጠብቁ፤ ቃሉ​ንም ስሙ፥#ዕብ. “እር​ሱ​ንም አም​ልኩ” የሚል ይጨ​ም​ራል። እር​ሱ​ንም ተማ​ጠ​ኑት። 5ከግ​ብፅ ምድር ካወ​ጣ​ችሁ፥ ከባ​ር​ነ​ትም ቤት ካዳ​ና​ችሁ ከአ​ም​ላ​ካ​ችሁ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሊያ​ስ​ታ​ችሁ፥ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ትሄ​ድ​ባት ዘንድ ካዘ​ዘህ መን​ገድ ሊያ​ወ​ጣህ ተና​ግ​ሮ​አ​ልና ያ ነቢይ ወይም ሕልም አላሚ ይገ​ደል፤ እን​ዲ​ሁም ክፉ​ውን ነገር ከአ​ንተ አርቅ።
6“የአ​ባ​ትህ#“የአ​ባ​ትህ” የሚ​ለው በዕብ. የለም። ወይም የእ​ና​ትህ ልጅ ወን​ድ​ምህ ወይም ወንድ ልጅህ ወይም ሴት ልጅህ ወይም አብ​ራህ የም​ት​ተኛ ሚስ​ትህ ወይም እንደ ነፍ​ስህ ያለ ወዳ​ጅህ በስ​ውር፦ ና፥ ሄደን አን​ተም አባ​ቶ​ች​ህም የማ​ታ​ው​ቋ​ቸ​ውን ሌሎች አማ​ል​ክት እና​ም​ልክ ብሎ ቢያ​ስ​ትህ፥ 7ከም​ድር ዳር ጀምሮ እስከ ምድር ዳር ድረስ ወደ አንተ የቀ​ረ​ቡት ከአ​ን​ተም የራ​ቁት አን​ተን ከብ​በ​ውህ ያሉ አሕ​ዛብ ከሚ​ያ​መ​ል​ኩ​አ​ቸው አማ​ል​ክት፥ 8ከእ​ርሱ ጋር አት​ተ​ባ​በር፤ አት​ስ​ማ​ውም፤ ዐይ​ን​ህም አይ​ራ​ራ​ለት፤ አት​ማ​ረ​ውም፤ አት​ሸ​ሽ​ገ​ውም፤ 9ነገር ግን ፈጽ​መህ ተና​ገር፤ እር​ሱን ለመ​ግ​ደል በፊት ያንተ እጅ፥ ከዚ​ያም በኋላ የሕ​ዝቡ ሁሉ እጅ በላዩ ትሁን። 10ከግ​ብፅ ምድር ከባ​ር​ነት ቤት ካወ​ጣህ ከአ​ም​ላ​ክህ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሊያ​ር​ቅህ ወድ​ዶ​አ​ልና በድ​ን​ጋይ ይው​ገ​ሩት፤ ይግ​ደ​ሉ​ትም። 11እስ​ራ​ኤል ሁሉ ሰም​ተው ይፍሩ፤ እን​ዲህ ያለ ክፉ ሥራም እን​ደ​ገና በእ​ና​ንተ መካ​ከል አይ​ደ​ገም።
12“አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልት​ኖ​ር​ባት ከሰ​ጠህ ከተ​ሞች በአ​ን​ዲቱ ከተ​ማህ፦ 13ክፋ​ተ​ኞች ሰዎች ከእ​ና​ንተ ዘንድ ወጥ​ተው፦ ሄደን የማ​ታ​ው​ቋ​ቸ​ውን ሌሎች አማ​ል​ክት እና​ም​ልክ ብለው የከ​ተ​ማ​ቸ​ውን ሰዎች አሳቱ ሲሉ ወሬ ብት​ሰማ፥ 14ትፈ​ል​ጋ​ለህ#“ትፈ​ል​ጋ​ለህ” የሚ​ለው በግ​እ​ዝና በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም። ትመ​ረ​ም​ራ​ለ​ህም፤ ትጠ​ይ​ቃ​ለ​ህም፤ እነ​ሆም፥ እው​ነት ቢሆን፥ ይህም ክፉ ነገር በመ​ካ​ከ​ልህ እንደ ተደ​ረገ ርግጥ ሆኖ ቢገኝ፥ 15የዚ​ያ​ችን ሀገር ሰዎች በሰ​ይፍ ስለት ፈጽሞ ትመ​ታ​ቸ​ዋ​ለህ፤ ሀገ​ሪ​ቱን፥ በው​ስ​ጥ​ዋም ያለ​ውን ሁሉ ትረ​ግ​ማ​ለህ። 16ዕቃ​ዋ​ንም ሁሉ ወደ አደ​ባ​ባ​ይዋ ትሰ​በ​ስ​ባ​ለህ፤ ከተ​ማ​ይ​ቱ​ንም፥ ዕቃ​ዋ​ንም ሁሉ በአ​ም​ላ​ክህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በእ​ሳት ፈጽ​መህ ታቃ​ጥ​ላ​ለህ፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም ወና ትሆ​ና​ለች፤ ደግ​ሞም አት​ሠ​ራም። 17የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የመ​ቅ​ሠ​ፍቱ ቍጣ ይመ​ለስ ዘንድ፥ ለአ​ባ​ቶ​ች​ህም እንደ ማለ​ላ​ቸው ይም​ርህ ዘንድ፥ ይራ​ራ​ል​ህም ዘንድ፥ ያበ​ዛ​ህም ዘንድ፥ ርጉም ከሆ​ነው አን​ዳች ነገር በእ​ጅህ አት​ንካ። 18ዛሬም እኔ የማ​ዝ​ዝ​ህን ትእ​ዛዝ ሁሉ ብት​ጠ​ብቅ፥ በአ​ም​ላ​ክህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት መል​ካ​ምና ጥሩ የሆ​ነ​ውን ብታ​ደ​ርግ፥ የአ​ም​ላ​ክ​ህን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ብት​ሰማ ለእ​ርሱ ልጅ ትሆ​ና​ለህ።#“ለእ​ርሱ ልጅ ትሆ​ና​ለህ” የሚ​ለው በዕብ. እና በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የም​ዕ​ራፍ 14 ማንሻ ነው።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ