የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘዳ​ግም 27

27
በድ​ን​ጋ​ዮች ላይ የተ​ጻፈ ሕግ
1ሙሴም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ሽማ​ግ​ሌ​ዎች እን​ዲህ ብሎ አዘ​ዛ​ቸው፥ “ዛሬ ያዘ​ዝ​ኋ​ች​ሁን ትእ​ዛዝ ታደ​ርጉ ዘንድ ዕወቁ፤ 2አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ​ሚ​ሰ​ጣ​ችሁ ምድር ዮር​ዳ​ኖ​ስን በተ​ሻ​ገ​ራ​ችሁ ጊዜ ታላ​ላቅ ድን​ጋ​ዮ​ችን ለእ​ና​ንተ አቁሙ፤ በኖ​ራም ምረ​ጓ​ቸው። 3የአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ተና​ገ​ራ​ችሁ፥#ዕብ. “ተስፋ እንደ ሰጠህ” ይላል። ወተ​ትና ማር ወደ​ም​ታ​ፈ​ስስ ምድር፥ አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ​ሚ​ሰ​ጣ​ችሁ ምድር ትገቡ ዘንድ በተ​ሻ​ገ​ራ​ችሁ ጊዜ፥ የዚ​ህን ሕግ ቃሎች ሁሉ በድ​ን​ጋ​ዮች ላይ ጻፉ። 4ዮር​ዳ​ኖ​ስ​ንም በተ​ሻ​ገ​ራ​ችሁ ጊዜ፥ ዛሬ እን​ዳ​ዘ​ዝ​ኋ​ችሁ፥ እነ​ዚ​ህን ድን​ጋ​ዮች በጌ​ባል ተራራ አቁሙ፤ በኖ​ራም ምረ​ጓ​ቸው። 5በዚ​ያም ለአ​ም​ላ​ክህ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊያ ሥራ፤ መሠ​ዊ​ያ​ውም ብረት ካል​ነ​ካው ድን​ጋይ ይሁን። 6ካል​ተ​ጠ​ረ​በም ድን​ጋይ ለአ​ም​ላ​ክህ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊያ ሥራ፤ ለአ​ም​ላ​ክ​ህም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ት​ህን አቅ​ር​ብ​በት፤ 7ለአ​ም​ላ​ክህ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕት ሠዋ​በት፤ በዚ​ያም ብላ፤ ጥገ​ብም፤ በአ​ም​ላ​ክ​ህም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ደስ ይበ​ልህ። 8የዚ​ህ​ንም ሕግ ቃሎች ሁሉ የተ​ገ​ለጠ አድ​ር​ገህ በድ​ን​ጋ​ዮቹ ላይ ጻፍ።”
9ሙሴና ሌዋ​ው​ያን ካህ​ናት ለእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ እን​ዲህ ብለው ተና​ገሩ፥ “እስ​ራ​ኤል ሆይ፥ ዝም ብለህ አድ​ምጥ፤ ዛሬ የአ​ም​ላ​ክህ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕዝብ ሆነ​ሃል። 10የአ​ም​ላ​ክ​ህ​ንም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስማ፤ ዛሬም የማ​ዝ​ዝ​ህን ትእ​ዛ​ዙ​ንና ሥር​ዐ​ቱን አድ​ርግ።”
ዐሥራ ሁለት ርግ​ማ​ኖች
11ሙሴም በዚያ ቀን እን​ዲህ ብሎ ሕዝ​ቡን አዘዘ፦ 12“ዮር​ዳ​ኖ​ስን በተ​ሻ​ገ​ራ​ችሁ ጊዜ ሕዝ​ቡን ይባ​ርኩ ዘንድ በገ​ሪ​ዛን ተራራ ላይ የሚ​ቆሙ እነ​ዚህ ናቸው፤ ስም​ዖ​ንና ሌዊ፥ ይሁ​ዳና ይሳ​ኮር፥ ዮሴ​ፍና ብን​ያም። 13ይረ​ግ​ሙም ዘንድ በጌ​ባል ተራራ ላይ የሚ​ቆሙ እነ​ዚህ ናቸው፤ ሮቤ​ልና ጋድ፥ አሴ​ርና ዛብ​ሎን፥ ዳንና ንፍ​ታ​ሌም። 14ሌዋ​ው​ያ​ንም ከፍ ባለች ድምፅ ለእ​ስ​ራ​ኤል ሰዎች ሁሉ እን​ዲህ ብለው ይና​ገሩ።
15“በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ የተ​ጠላ የሠ​ራ​ተኛ እጅ ሥራን፥ የተ​ቀ​ረፀ ወይም ቀልጦ የተ​ሠራ ምስ​ልን የሚ​ያ​ደ​ርግ፥ በስ​ው​ርም የሚ​ያ​ቆ​መው ሰው ርጉም ይሁን፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ መል​ሰው አሜን ይላሉ።
16“አባ​ቱን ወይም እና​ቱን የሚ​ያ​ቃ​ልል ርጉም ይሁን፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ አሜን ይላሉ።
17“የባ​ል​ን​ጀ​ራ​ውን የድ​ን​በር ምል​ክት የሚ​ገፋ ርጉም ይሁን፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ አሜን ይላሉ።
18“ዕው​ሩን ከመ​ን​ገድ ፈቀቅ የሚ​ያ​ደ​ርግ ርጉም ይሁን፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ አሜን ይላሉ።
19“በመ​ጻ​ተኛ፥ በድሃ-አደ​ጉም፥ በመ​በ​ለ​ቲ​ቱም ላይ ፍር​ድን የሚ​ያ​ጣ​ምም ርጉም ይሁን፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ አሜን ይላሉ።
20“ከእ​ን​ጀራ እናቱ ጋር የሚ​ተኛ የአ​ባ​ቱን ኀፍ​ረት ገል​ጦ​አ​ልና ርጉም ይሁን፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ አሜን ይላሉ።
21“ከእ​ን​ስሳ ሁሉ የሚ​ደ​ርስ ርጉም ይሁን፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ አሜን ይላሉ።
22“ከአ​ባቱ ወይም ከእ​ናቱ ልጅ ከእ​ኅቱ ጋር የሚ​ተኛ ርጉም ይሁን፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ አሜን ይላሉ።
23“ከአ​ማቱ ጋር የሚ​ተኛ ርጉም ይሁን፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ አሜን ይላሉ። ከዋ​ር​ሳው ጋር የሚ​ተኛ#“ከዋ​ር​ሳው ጋር የሚ​ተኛ” የሚ​ለው በግ​እዝ የለም። ርጉም ይሁን፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ አሜን ይሁን ይላሉ።
24“ባል​ን​ጀ​ራ​ውን በተ​ን​ኰል የሚ​መታ ርጉም ይሁን፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ አሜን ይላሉ።
25“የን​ጹ​ሑን ሰው ነፍስ ለመ​ግ​ደል ጉቦ የሚ​ቀ​በል ርጉም ይሁን፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ አሜን ይላሉ።
26“የዚ​ህን ሕግ ቃሎች ያደ​ርግ ዘንድ የማ​ያ​ጸና ርጉም ይሁን፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ አሜን ይላሉ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ