የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘዳ​ግም 7

7
ከአ​ሕ​ዛብ ስለ መለ​የት
(ዘፀ. 34፥11-16)
1“አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልት​ወ​ር​ሳት ወደ​ም​ት​ገ​ባ​ባት ምድር ባመ​ጣህ ጊዜ፥ ከፊ​ት​ህም ብዙና ታላ​ላቅ አሕ​ዛ​ብን፥ ከአ​ንተ የበ​ለ​ጡ​ትን፥ የበ​ረ​ቱ​ት​ንም ሰባ​ቱን አሕ​ዛብ፥ ኬጤ​ዎ​ና​ዊ​ውን፥ ጌር​ጌ​ሴ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም፥ አሞ​ሬ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም፥ ከነ​ዓ​ና​ዊ​ው​ንም፥ ፌር​ዜ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም፥ ኤዌ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም፥ ኢያ​ቡ​ሴ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም ባወጣ ጊዜ፥ 2አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ጅህ አሳ​ልፎ በሰ​ጣ​ቸ​ውና በመ​ታ​ሃ​ቸው ጊዜ፥ ፈጽ​መህ አጥ​ፋ​ቸው፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ቃል ኪዳን አታ​ድ​ርግ፤ አት​ማ​ራ​ቸ​ውም፤ 3ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር አት​ጋባ፤ ሴት ልጅ​ህን ለወ​ንድ ልጁ አት​ስጥ፥ ሴት ልጁ​ንም ለወ​ንድ ልጅህ አት​ው​ሰድ። 4ልጅ​ህን ከእኔ ያር​ቀ​ዋ​ልና፤ ሌሎ​ችን አማ​ል​ክ​ትም ያመ​ል​ካ​ልና። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቍጣ ይነ​ድ​ድ​ባ​ች​ኋል፤ ፈጥ​ኖም ያጠ​ፋ​ች​ኋል። 5ነገር ግን እን​ዲህ አድ​ር​ጉ​ባ​ቸው፤ መሠ​ዊ​ያ​ቸ​ውን አፍ​ርሱ፤ ሐው​ል​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም ሰባ​ብሩ፥ የማ​ም​ለ​ኪያ ዐፀ​ዶ​ቻ​ቸ​ው​ንም ቍረጡ፥ የአ​ማ​ል​ክ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም ምስል በእ​ሳት አቃ​ጥሉ።
6“ለአ​ም​ላ​ክህ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አንተ ቅዱስ ሕዝብ ነህና፤ በም​ድር ፊት ከሚ​ኖሩ አሕ​ዛብ ሁሉ ይልቅ ለእ​ርሱ ለራሱ ሕዝብ#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ርስት” ይላል። ትሆ​ን​ለት ዘንድ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መር​ጦ​ሃ​ልና። 7እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የወ​ደ​ዳ​ች​ሁና የመ​ረ​ጣ​ችሁ፥ ከአ​ሕ​ዛብ ሁሉ ስለ በዛ​ችሁ አይ​ደ​ለም፤ እና​ንት ከአ​ሕ​ዛብ ሁሉ ጥቂ​ቶች ነበ​ራ​ች​ሁና፤ 8ነገር ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ ወደ​ዳ​ችሁ፥ ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ች​ሁም የማ​ለ​ላ​ቸ​ውን መሐላ ስለ ጠበቀ፥ ስለ​ዚህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጽኑ እጅ፥ በተ​ዘ​ረ​ጋ​ችም ክንድ አወ​ጣ​ችሁ፤ ከባ​ር​ነ​ትም ቤት ከግ​ብፅ ንጉሥ ከፈ​ር​ዖን እጅ አዳ​ና​ችሁ። 9አን​ተም አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እርሱ አም​ላክ እንደ ሆነ፥ ለሚ​ወ​ድ​ዱ​ትም፥ ትእ​ዛ​ዙ​ንም ለሚ​ጠ​ብቁ ቃል ኪዳ​ኑ​ንና ምሕ​ረ​ቱን እስከ ሺህ ትው​ልድ ድረስ የሚ​ጠ​ብቅ የታ​መነ አም​ላክ እንደ ሆነ ዕወቅ፤ 10የሚ​ጠ​ሉ​ትን ለማ​ጥ​ፋት በፊ​ታ​ቸው ብድ​ራት ይመ​ል​ስ​ባ​ቸ​ዋል፤ ለሚ​ጠ​ላው አይ​ዘ​ገ​ይም፤ ነገር ግን በፊቱ ብድ​ራ​ትን ይመ​ል​ስ​በ​ታል። 11እን​ግ​ዲህ ታደ​ር​ጓት ዘንድ እኔ ዛሬ ለእ​ና​ንተ የማ​ዝ​ዛ​ትን ትእ​ዛ​ዝና ሥር​ዐት፥ ፍር​ድ​ንም ጠብቁ።
ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መታ​ዘዝ የሚ​ያ​ስ​ገ​ኘው በረ​ከት
(ዘዳ. 28፥11-14)
12“እን​ዲ​ህም ይሆ​ናል፤ ይህ​ችን ፍርድ ሰም​ታ​ችሁ ብት​ጠ​ብ​ቋት፥ ብታ​ደ​ር​ጓ​ትም፥ አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ የማ​ለ​ውን ቃል ኪዳ​ንና ምሕ​ረት ለእ​ና​ንተ ይጠ​ብ​ቅ​ላ​ች​ኋል፤ 13ይወ​ድ​ድ​ህ​ማል፤ ይባ​ር​ክ​ህ​ማል፤ ያባ​ዛ​ህ​ማል፤ ይሰ​ጥ​ህም ዘንድ ለአ​ባ​ቶ​ችህ በማ​ለ​ላ​ቸው ምድር የሆ​ድ​ህን ፍሬ፥ የመ​ሬ​ት​ህ​ንም ፍሬ፥ እህ​ል​ህን፥ ወይ​ን​ህ​ንም፥ ዘይ​ት​ህ​ንም፥ የከ​ብ​ት​ህ​ንም ብዛት፥ የበ​ግ​ህ​ንም መንጋ ይባ​ር​ክ​ል​ሃል። 14ከአ​ሕ​ዛ​ብም ሁሉ ይልቅ የተ​ባ​ረ​ክህ ትሆ​ና​ለህ፤ ከሴ​ቶ​ችህ መካን አት​ኖ​ርም፤ ልጆች የሌ​ሏት አገ​ል​ጋ​ይም አት​ኖ​ርም፤ ከከ​ብ​ት​ህም መካን አይ​ኖ​ርም።#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “በሰ​ው​ህና በከ​ብ​ትህ ዘንድ የወ​ንድ ወይም የሴት መካን አይ​ኖ​ርም” ይላል። 15በግ​ብ​ፃ​ው​ያን ላይ ሲመጣ ያየ​ኸ​ውን ክፉ ሕማ​ምና ደዌ ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከአ​ንተ ያር​ቅ​ል​ሃል፤ ያየ​ኸ​ው​ንም መከራ ሁሉ ወደ አንተ አያ​መ​ጣ​ውም፤ ከአ​ን​ተም በሚ​ጠ​ሉህ ሁሉ ላይ ይመ​ል​ሰ​ዋል። 16አም​ላ​ክ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ሰ​ጥ​ህን የአ​ሕ​ዛብ ምርኮ ትበ​ላ​ለህ፤ ዐይ​ን​ህም አታ​ዝ​ን​ላ​ቸ​ውም፤ ያም ለአ​ንተ ክፉ ይሆ​ን​ብ​ሃ​ልና አማ​ል​ክ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን አታ​ም​ል​ካ​ቸው።
17“በል​ብ​ህም፦ እነ​ዚህ አሕ​ዛብ ከእኔ ይልቅ ይበ​ዛ​ሉና አወ​ጣ​ቸው ዘንድ እን​ዴት እች​ላ​ለሁ? ብለህ፥ አት​ፍ​ራ​ቸው፤ 18ነገር ግን አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በፈ​ር​ዖ​ንና በግ​ብ​ፃ​ው​ያን ሁሉ ያደ​ረ​ገ​ውን ፈጽ​መህ አስብ፤ 19አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዓይ​ንህ እያ​የች፥ ታላቅ መቅ​ሠ​ፍ​ትን፥ ምል​ክ​ት​ንም፥ ተአ​ም​ራ​ት​ንም፥ የጸ​ና​ች​ው​ንም እጅ፥ የተ​ዘ​ረ​ጋ​ው​ንም ክንድ አድ​ርጎ እን​ዳ​ወ​ጣህ፤ እን​ዲሁ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አንተ በም​ት​ፈ​ራ​ቸው በአ​ሕ​ዛብ ሁሉ ላይ ያደ​ር​ጋል። 20ደግ​ሞም አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የቀ​ሩት፥ ከፊ​ት​ህም የተ​ሸ​ሸ​ጉት እስ​ኪ​ጠፉ ድረስ መቅ​ሠ​ፍ​ትን ይል​ክ​ባ​ቸ​ዋል። 21ከፊ​ታ​ቸው አት​ደ​ን​ግጥ፤ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ ከአ​ንተ ጋር ነውና፥ እር​ሱም አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታላ​ቅና ጽኑዕ ነውና። 22አም​ላ​ክ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እነ​ዚ​ህን አሕ​ዛብ በጥ​ቂት በጥ​ቂቱ ከፊ​ትህ ያጠ​ፋ​ቸ​ዋል፤ ምድ​ርም ምድረ በዳ እን​ዳ​ት​ሆን#“ምድር ምድረ በዳ እን​ዳ​ት​ሆን” የሚ​ለው በዕብ. የለም። የም​ድረ በዳ አራ​ዊ​ትም እን​ዳ​ይ​በ​ዙ​ብህ ፈጥኜ አጠ​ፋ​ቸ​ዋ​ለሁ አት​በል። 23አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን እነ​ር​ሱን በእ​ጅህ አሳ​ልፎ ይሰ​ጣ​ቸ​ዋል፥ እስ​ኪ​ጠ​ፉም ድረስ በታ​ላቅ ውር​ደት ይደ​መ​ስ​ሳ​ቸ​ዋል። 24ነገ​ሥ​ታ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም በእ​ጅህ አሳ​ልፎ ይሰ​ጣ​ቸ​ዋል፤ ስማ​ቸ​ው​ንም ከዚያ ቦታ ያጠ​ፋል፤ እስ​ክ​ታ​ጠ​ፋ​ቸው ድረስ ማንም ከፊ​ትህ ይቆም ዘንድ አይ​ች​ልም። 25የአ​ም​ላ​ኮ​ቻ​ቸ​ውን ምስል በእ​ሳት ታቃ​ጥ​ላ​ለህ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም የተ​ሠ​ራ​ባ​ቸ​ውን ብር​ንና ወር​ቅን፥ አት​መኝ፤ በአ​ም​ላ​ክ​ህም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ርኩስ ነውና እን​ዳ​ት​በ​ድ​ል​በት ከእ​ርሱ ምንም አት​ው​ሰድ። 26ርኩ​ስን ነገር ወደ ቤትህ አታ​ግባ፤ እንደ እር​ሱም ርጉም ትሆ​ና​ለህ፤ ርጉም ነውና መጸ​የ​ፍን ተጸ​የ​ፈው፤ መጥ​ላ​ት​ንም ጥላው።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ