የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ትን​ቢተ ሕዝ​ቅ​ኤል 30

30
ጌታ ግብ​ፅን እን​ደ​ሚ​ቀጣ
1የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ወደ እኔ እን​ዲህ ሲል መጣ፦ 2“የሰው ልጅ ሆይ! ትን​ቢት ተና​ገር፤ እን​ዲ​ህም በል፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ዋይ! በሉ፥#“ዋይ በሉ” የሚ​ለው በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም። ለቀኑ ወዮ! 3ቀኑ ቅርብ ነው፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቀን ቅርብ ነው፤ የደ​መና ቀን፥ የአ​ሕ​ዛብ ማለ​ቂያ ጊዜ ይሆ​ናል። 4ሰይፍ በግ​ብፅ ላይ ይመ​ጣል፤ ሁከ​ትም በኢ​ት​ዮ​ጵያ ይሆ​ናል፤ የተ​ገ​ደ​ሉ​ትም በግ​ብፅ ውስጥ ይወ​ድ​ቃሉ፤ ብዛ​ቷ​ንም ይወ​ስ​ዳሉ፤ መሠ​ረ​ቷም ይፈ​ር​ሳል። 5ኢት​ዮ​ጵ​ያና#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ፋርስ” ይላል። ፉጥ፥ ሉድም፥ ዓረ​ብም ሁሉ፥ ኩብም፤ ሊብ​ያም፤ ቀር​ጤ​ስም የተ​ደ​ባ​ለቀ ሕዝ​ብም ሁሉ፥ ቃል ኪዳ​ን​ንም የገ​ባ​ችው ምድር ልጆች ከእ​ነ​ርሱ ጋር በሰ​ይፍ ይወ​ድ​ቃሉ።
6“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዲህ ይላል፦ ግብ​ፅን የሚ​ደ​ግፉ ይወ​ድ​ቃሉ፤ የኀ​ይ​ል​ዋም ትዕ​ቢት ይወ​ር​ዳል፤ ከሚ​ግ​ዶል ጀምሮ እስከ ሰዌኔ#“ሰዌኔ” አስ​ዋን ነው። ድረስ በእ​ር​ስዋ ውስጥ በሰ​ይፍ ይወ​ድ​ቃሉ፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር። 7ባድ​ማም በሆኑ ሀገ​ሮች መካ​ከል ባድማ ይሆ​ናሉ፤ ከተ​ሞ​ች​ዋም በፈ​ረሱ ከተ​ሞች መካ​ከል ይሆ​ናሉ። 8እሳ​ት​ንም በግ​ብፅ ላይ በአ​ነ​ደ​ድሁ ጊዜ፥ ረዳ​ቶ​ች​ዋም ሁሉ በተ​ሰ​በሩ ጊዜ፥ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ። 9በዚያ ቀን መል​እ​ክ​ተ​ኞች ተዘ​ል​ለው#“ተዘ​ል​ለው” የሚ​ለው በዕብ. ብቻ። የሚ​ኖ​ሩ​ትን ኢት​ዮ​ጵ​ያ​ው​ያ​ንን ለማ​ጥ​ፋት ከፊቴ በመ​ር​ከብ#“በመ​ር​ከብ” የሚ​ለው በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም። ይወ​ጣሉ፤ በግ​ብ​ፅም ቀን ሁከት ይሆ​ን​ባ​ቸ​ዋል፤ እነሆ፥ ይመ​ጣ​ልና።
10“ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ የግ​ብ​ፅን ብዛት በባ​ቢ​ሎን ንጉሥ በና​ቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር እጅ አጠ​ፋ​ለሁ። 11እር​ሱና ሕዝቡ የአ​ሕ​ዛ​ብም ኀያ​ላን ምድ​ሪ​ቱን ለማ​ጥ​ፋት ይላ​ካሉ፤ ግብ​ፃ​ው​ያ​ን​ንም በሰ​ይፍ ይወ​ጉ​አ​ቸ​ዋል፤ ምድ​ሪ​ቱም በሙ​ታን ትሞ​ላ​ለች። 12ወን​ዞ​ች​ንም ምድረ በዳ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ ምድ​ሪ​ቱ​ንም በክፉ ሰዎች እጅ እሰ​ጣ​ለሁ፥#“በክፉ ሰዎች እጅ እሰ​ጣ​ለሁ” የሚ​ለው በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም። ምድ​ሪ​ቱ​ንና ሞላ​ዋ​ንም በባ​ዕ​ዳን እጅ ባድማ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተና​ግ​ሬ​አ​ለሁ።
13“ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ጣዖ​ቶ​ቹን አጠ​ፋ​ለሁ፤ ምስ​ሎ​ቹ​ንም#ግሪክ ሰባ. ሊ. “መኳ​ን​ን​ቶ​ች​ንም” ይላል። ከሜ​ም​ፎስ እሽ​ራ​ለሁ፤ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲ​ያም በግ​ብፅ ምድር አለቃ አይ​ሆ​ንም፤ በግ​ብፅ ምድር ላይም ፍር​ሀ​ትን አደ​ር​ጋ​ለሁ። 14ጳት​ሮ​ስ​ንም አፈ​ር​ሳ​ለሁ፤ በጣ​ኔ​ዎ​ስም ላይ እሳ​ትን አነ​ድ​ዳ​ለሁ፤ በዲ​ዮ​ስ​ጶ​ሊን ላይም ፍር​ድን አደ​ር​ጋ​ለሁ። 15በግ​ብ​ፅም ኀይል በሲን ላይ መዓ​ቴን አፈ​ስ​ሳ​ለሁ፤ የሜ​ም​ፎ​ስ​ንም ብዛት አጠ​ፋ​ለሁ። 16በግ​ብ​ፅም ላይ እሳ​ትን አነ​ድ​ዳ​ለሁ፤ ሲንም ትታ​ወ​ካ​ለች፤ ኖእም ትሰ​በ​ራ​ለች፤ ሜም​ፎ​ስም ምድረ በዳ ትሆ​ና​ለች። 17የሄ​ል​ዮቱ ከተ​ማና የቡ​ባ​ስ​ቱም ጐል​ማ​ሶች በሰ​ይፍ ይወ​ድ​ቃሉ፤ ሴቶ​ችም ይማ​ረ​ካሉ። 18የግ​ብ​ፅን ቀን​በር በዚያ በሰ​በ​ርሁ ጊዜ በጣ​ፍ​ናስ ቀኑ ይጨ​ል​ማል፤ የኀ​ይ​ል​ዋም ትዕ​ቢት ይጠ​ፋ​ባ​ታል፤ ደመ​ናም ይጋ​ር​ዳ​ታል፤ ሴቶች ልጆ​ች​ዋም ይማ​ረ​ካሉ። 19እን​ዲሁ በግ​ብፅ ላይ ፍር​ድን አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ።”
20እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በዐ​ሥራ አን​ደ​ኛው ዓመት በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ወር ከወ​ሩም በሰ​ባ​ተ​ኛው ቀን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ወደ እኔ እን​ዲህ ሲል መጣ፦ 21“የሰው ልጅ ሆይ! የግ​ብ​ፅን ንጉሥ የፈ​ር​ዖ​ንን ክንድ ሰብ​ሬ​አ​ለሁ፥ እነ​ሆም ይድን ዘንድ መድ​ኃ​ኒት ቀብ​ተው አያ​ደ​ር​ቁ​ትም፤ ሰይ​ፉ​ንም ለመ​ያዝ ኀይ​ልን ያገኝ ዘንድ አል​ታ​ሰ​ረም። 22ስለ​ዚህ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ እኔ በግ​ብፅ ንጉሥ በፈ​ር​ዖን ላይ ነኝ የጸ​ና​ች​ው​ንና የተ​ሰ​በ​ረ​ች​ው​ንም#ግሪክ ሰባ. ሊ. “የተ​ዘ​ረ​ጋ​ች​ው​ንም” ይላል። ክን​ዱን እሰ​ብ​ራ​ለሁ፤ ሰይ​ፉ​ንም ከእጁ አስ​ጥ​ለ​ዋ​ለሁ። 23ግብ​ፃ​ው​ያ​ን​ንም በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል እበ​ት​ና​ለሁ፤ በሀ​ገ​ሮ​ችም መካ​ከል እዘ​ራ​ቸ​ዋ​ለሁ። 24የባ​ቢ​ሎ​ን​ንም ንጉሥ ክንድ አበ​ረ​ታ​ለሁ፤ ሰይ​ፌ​ንም በእጁ እሰ​ጣ​ለሁ፤ ግብ​ፅ​ንም ይወ​ጋ​በ​ታል፥#ዕብ. “የፈ​ር​ዖ​ንን ክንድ ግን እሰ​ብ​ራ​ለሁ” ይላል። ምር​ኮ​ዋ​ንም ይማ​ር​ካል፤ ሰለ​ባ​ዋ​ንም ይሰ​ል​ባል።#ዕብ. “ተወ​ግ​ቶም በሚ​ሞ​ተው እን​ጕ​ር​ጕሮ በፊቱ ያን​ጐ​ራ​ጕ​ራል” ይላል። 25የባ​ቢ​ሎ​ን​ንም ንጉሥ ክንድ አጸ​ና​ለሁ፤ የፈ​ር​ዖ​ንም ክንድ ይወ​ድ​ቃል፤ ሰይ​ፌ​ንም በባ​ቢ​ሎን ንጉሥ እጅ በሰ​ጠሁ ጊዜ፥ እር​ሱም በግ​ብፅ ምድር ላይ በዘ​ረ​ጋው ጊዜ፥ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ። 26ግብ​ፃ​ው​ያ​ን​ንም በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል እበ​ት​ና​ለሁ፤ በሀ​ገ​ሮ​ችም መካ​ከል እዘ​ራ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ሁሉም እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ።”

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ