የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ትን​ቢተ ሕዝ​ቅ​ኤል 31

31
ግብፅ በዝ​ግባ ዛፍ እን​ደ​ም​ት​መ​ሰል
1እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በዐ​ሥራ አን​ደ​ኛው ዓመት በሦ​ስ​ተ​ኛው ወር ከወ​ሩም በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ቀን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ወደ እኔ እን​ዲህ ሲል መጣ፦ 2“የሰው ልጅ ሆይ! የግ​ብ​ፅን ንጉሥ ፈር​ዖ​ን​ንና ሕዝ​ቡን እን​ዲህ በላ​ቸው፦ በታ​ላ​ቅ​ነ​ትህ ማንን ትመ​ስ​ላ​ለህ? 3እነሆ አሦር ጫፉ እንደ ተዋበ፥ ችፍ​ግ​ነቱ ጥላ እንደ ሰጠ፥ ቁመ​ቱም እንደ ረዘመ፥ ራሱም ወደ ደመ​ና​ዎች እንደ ደረሰ እንደ ሊባ​ኖስ ዝግባ ነበረ። 4ውኃም አበ​ቀ​ለው፥ ቀላ​ይም አሳ​ደ​ገው፥ ወን​ዞ​ችም በተ​ተ​ከ​ለ​በት ዙሪያ ይጎ​ርፉ ነበር፤ ፈሳ​ሾ​ቹ​ንም ወደ ምድረ በዳ ዛፍ ሁሉ ላከ። 5ስለ​ዚህ ቁመቱ ከም​ድረ በዳ ዛፍ ሁሉ በላይ ከፍ ከፍ አለ፤ ቅር​ን​ጫ​ፎ​ቹም በዙ፤ ጫፎ​ቹም ከብዙ ውኆች የተ​ነሣ ረዘሙ። 6የሰ​ማ​ይም ወፎች ሁሉ በቅ​ር​ን​ጫ​ፎቹ ላይ ተዋ​ለዱ፤#ዕብ. “ጎጆ​ቻ​ቸ​ውን ሠሩ” ይላል። የም​ድ​ርም አራ​ዊት ሁሉ ከጫ​ፎቹ በታች ተዋ​ለዱ፤ ከጥ​ላ​ውም በታች ታላ​ላ​ቆች አሕ​ዛብ ሁሉ ይቀ​መጡ ነበር። 7ሥሩም በብዙ ውኃ አጠ​ገብ ነበ​ረና በታ​ላ​ቅ​ነ​ቱና በጫ​ፎቹ ርዝ​መት የተ​ዋበ ነበረ። 8በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ገነት የነ​በሩ ዝግ​ባ​ዎች አይ​ተ​ካ​ከ​ሉ​ትም፥#ዕብ. “አላ​ጨ​ለ​ሙ​ትም” ይላል። ጥዶ​ችም ቅር​ን​ጫ​ፎ​ቹን፥ አስታ የሚ​ባ​ለ​ውም ዛፍ ጫፎ​ቹን አይ​መ​ሳ​ሰ​ሉ​ትም ነበር፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ገነት ዛፍ ሁሉ በው​በቱ አይ​መ​ስ​ለ​ውም ነበር። 9በጫ​ፎቹ ብዛት ውብ አደ​ረ​ግ​ሁት፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ገነት በዔ​ድን የነ​በሩ ዛፎች ሁሉ ቀኑ​በት።
10“ስለ​ዚህ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ቁመ​ትህ ከፍ ከፍ ብሎ​አ​ልና፥ ራስ​ህም በደ​መ​ናት መካ​ከል ደር​ሶ​አ​ልና፤ ትዕ​ቢ​ቱ​ንም አየሁ፤ 11በአ​ሕ​ዛ​ብም አለ​ቆች እጅ አሳ​ልፌ እሰ​ጠ​ዋ​ለሁ፤ እር​ሱም እንደ ክፋቱ መጠን ያደ​ር​ግ​በ​ታል፤ እኔም አሳ​ድ​ደ​ዋ​ለሁ።#“እኔም አሳ​ድ​ደ​ዋ​ለሁ” የሚ​ለው በዕብ. ብቻ። 12የሌላ ሀገር ሰዎች፥ የአ​ሕ​ዛብ ጨካ​ኞች የሆኑ፥ ቈር​ጠው ጣሉት፤ በተ​ራ​ሮ​ችና በሸ​ለ​ቆ​ዎች ሁሉ ውስጥ ጫፎቹ ወደቁ፤ ቅር​ን​ጫ​ፎ​ቹም በም​ድር ፈሳ​ሾች ሁሉ ላይ ተሰ​ባ​በሩ፤ የም​ድ​ርም አሕ​ዛብ ሁሉ ከጥ​ላው ተመ​ል​ሰው ተዉት። 13በወ​ደ​ቀው ግንድ ላይ የሰ​ማይ ወፎች ሁሉ ይቀ​መ​ጣሉ፤ የም​ድ​ርም አራ​ዊት ሁሉ በቅ​ር​ን​ጫ​ፎቹ ላይ ይሆ​ናሉ። 14በው​ኃው አጠ​ገብ ያሉ የዕ​ን​ጨ​ቶች ሁሉ ቁመት እን​ዳ​ይ​ረ​ዝም ራሱም ወደ ደመና እን​ዳ​ይ​ደ​ርስ ያንም ውኃ የሚ​ጠ​ጡት እን​ጨ​ቶች ሁሉ በር​ዝ​መ​ታ​ቸው ከእ​ርሱ ጋራ እን​ዳ​ይ​ተ​ካ​ከሉ ሁሉም ወደ መቃ​ብር በሚ​ወ​ርዱ ሰዎች መካ​ከል በጥ​ልቅ ምድር ሞቱ።
15“ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ወደ ሲኦል በወ​ረ​ደ​በት ቀን ልቅ​ሶን አስ​ለ​ቀ​ስሁ፤ ቀላ​ዩ​ንም ስለ እርሱ ሸፈ​ን​ሁት፤ ፈሳ​ሾ​ች​ንም ከለ​ከ​ልሁ፤ ታላ​ላ​ቆ​ችም ውኆች ተከ​ለ​ከሉ፤ ሊባ​ኖ​ስ​ንም ስለ እርሱ አሳ​ዘ​ን​ሁት። የዱ​ርም ዛፎች ሁሉ ስለ እርሱ ዛሉ። 16ወደ ጕድ​ጓድ ከሚ​ወ​ርዱ ጋር ወደ ሲኦል በጣ​ል​ሁት ጊዜ ከመ​ው​ደቁ ድምፅ የተ​ነሣ አሕ​ዛ​ብን አን​ቀ​ጠ​ቀ​ጥሁ፤ ውኃም የሚ​ጠጡ ሁሉ፥ ምር​ጦ​ችና መል​ካ​ሞች የሊ​ባ​ኖስ ዛፎች፥ የዔ​ድን ዛፎች ሁሉ በታ​ች​ኛው ምድር ውስጥ ተጽ​ና​ን​ተ​ዋል። 17እነ​ር​ሱም በሰ​ይፍ ወደ ተገ​ደ​ሉት ወደ ሲኦል ከእ​ርሱ ጋር ወረዱ፤ በጥ​ላው ሥር ይኖሩ የነ​በሩ ዘሮ​ቹም በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል ጠፉ።
18“በክ​ብ​ርና በታ​ላ​ቅ​ነት በዔ​ድን ዛፎች መካ​ከል ማንን ትመ​ስ​ላ​ለህ? ነገር ግን ከዔ​ድን ዛፎች ጋር ወደ ታች​ኛው ምድር ያወ​ር​ዱ​ሃል፤ በሰ​ይ​ፍም በተ​ገ​ደ​ሉት ባል​ተ​ገ​ረ​ዙት መካ​ከል ትተ​ኛ​ለህ። ይህም ፈር​ዖ​ንና የሕ​ዝቡ ብዛት ሁሉ ነው፥” ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ