የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ትን​ቢተ ሕዝ​ቅ​ኤል 40

40
ስለ አዲሱ ቤተ መቅ​ደስ የተ​ገ​ለጠ ራእይ
1በተ​ማ​ረ​ክን በሃያ አም​ስ​ተ​ኛው ዓመት በዓ​መቱ መጀ​መ​ሪያ ከወሩ በዐ​ሥ​ረ​ኛው ቀን፥ ከተ​ማ​ዪቱ ከተ​መ​ታች በኋላ በዐ​ሥራ አራ​ተ​ኛው ዓመት፥ በዚ​ያው ቀን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ በእኔ ላይ ነበረ፤ እር​ሱም ወደ​ዚያ ወሰ​ደኝ። 2በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ራእይ ወደ እስ​ራ​ኤል ምድር አመ​ጣኝ፤ እጅ​ግም በረ​ዘመ ተራራ ላይ አኖ​ረኝ፤ በዚ​ያም ላይ እንደ ከተማ ሆኖ የተ​ሠራ ነገር በፊቴ ነበረ። 3ወደ​ዚ​ያም አመ​ጣኝ፤ እነ​ሆም መልኩ እን​ደ​ሚ​ያ​ን​ፀ​ባ​ርቅ ናስ መልክ የመ​ሰለ አንድ ሰው በዚያ ነበረ፤ በእ​ጁም የተ​ልባ እግር ገመ​ድና የመ​ለ​ኪያ ዘንግ ነበረ፤ እር​ሱም በበሩ አጠ​ገብ ቆሞ ነበር። 4ያም ሰው፥ “የሰው ልጅ ሆይ! ይህን አሳ​ይህ ዘንድ አንተ ወደ​ዚህ መጥ​ተ​ሃ​ልና በዐ​ይ​ንህ እይ፤ በጆ​ሮ​ህም ስማ፤ የማ​ሳ​ይ​ህ​ንም ሁሉ በል​ብህ ጠብቅ፤ የም​ታ​የ​ው​ንም ሁሉ ለእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ንገር” አለኝ።
5እነ​ሆም በቤቱ ውጭ በዙ​ሪ​ያው ቅጥር ነበረ፤ በሰ​ው​የ​ውም እጅ የክ​ንዱ ልክ አንድ ክንድ ከጋት የሆነ ስድ​ስት ክንድ ያለ​በት የመ​ለ​ኪያ ዘንግ ነበረ፤ የቅ​ጥ​ሩ​ንም ስፋት አንድ ዘንግ ቁመ​ቱ​ንም አንድ ዘንግ አድ​ርጎ ለካ። 6ወደ ምሥ​ራቅ ወደ​ሚ​መ​ለ​ከ​ተ​ውም በር መጣ፤ በሰ​ባ​ቱም ደረ​ጃ​ዎች ላይ ወጣ፤ በበሩ በኩል ያለ​ው​ንም የመ​ድ​ረ​ኩን ወለል ወር​ዱን አንድ ዘንግ አድ​ርጎ ለካ፤ የሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ወለል ወርድ አንድ ዘንግ ነበረ። 7የዕቃ ቤቱ ሁሉ ርዝ​መት አንድ ዘንግ፤ ወር​ዱም አንድ ዘንግ ነበረ፤ በዕቃ ቤቶ​ቹም መካ​ከል አም​ስት ክንድ ነበረ፤ በበ​ሩም ደጀ ሰላም፤ በስ​ተ​ው​ስጥ በኩል የሚ​ገኝ የበሩ የመ​ድ​ረክ ወለል አንድ ዘንግ ነበረ። 8በስ​ተ​ው​ስ​ጥም#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ሦስ​ተ​ኛው ክፍል” ይላል። ያለ​ውን የበ​ሩን ደጀ​ሰ​ላም አንድ ዘንግ አድ​ርጎ ለካ። 9የበ​ሩ​ንም ደጀ ሰላም ስም​ንት ክንድ፤ የግ​ን​ቡ​ንም አዕ​ማድ ወርድ ሁለት ክንድ አድ​ርጎ ለካ፤ የበ​ሩም ደጀ ሰላም በስ​ተ​ው​ስጥ ነበረ። 10የም​ሥ​ራ​ቁም ዕቃ ቤቶች በዚህ በኩል ሦስት፥ በዚ​ያም በኩል ሦስት፥ ነበሩ፤ ለሦ​ስ​ቱም አንድ ልክ ነበረ፤ የግ​ን​ቡም አዕ​ማድ ወርድ በዚህ በኩ​ልና በዚያ በኩል አንድ ልክ ነበረ። 11የበ​ሩ​ንም መግ​ቢያ ወርድ ዐሥር ክንድ፥ የበ​ሩ​ንም ርዝ​መት ዐሥራ ሦስት ክንድ አድ​ርጎ ለካ። 12በዕቃ ቤቱም ፊት በዚህ በኩል አንድ ክንድ፥ በዚ​ያም በኩል አንድ ክንድ የሆነ ዳርቻ ነበረ፤ የዕቃ ቤቱም በዚህ በኩል ስድ​ስት ክንድ በዚ​ያም በኩል ስድ​ስት ክንድ ነበሩ። 13ከአ​ን​ዱም የዕቃ ቤት ደርብ ጀምሮ እስከ ሌላው ደርብ ድረስ የበ​ሩን ወርድ ሃያ አም​ስት ክንድ አድ​ርጎ ለካ፤ በሩና በሩም ትይዩ ነበረ። 14ደጀ ሰላ​ሙ​ንም ሃያ#ዕብ. “ስድሳ” ይላል። ክንድ አድ​ርጎ ለካ፤ በበ​ሩም ደጀ ሰላም ዙሪያ አደ​ባ​ባይ ነበረ። 15ከበ​ሩም መግ​ቢያ ፊት ጀምሮ እስከ ውስ​ጠ​ኛው የበሩ ደጀ ሰላም መጨ​ረሻ ድረስ አምሳ ክንድ ነበረ። 16በዕቃ ቤቶ​ቹም በበሩ ውስጥ በዙ​ሪ​ያው በነ​በ​ሩ​ትም በግ​ንቡ አዕ​ማድ የዐ​ይነ ርግብ መስ​ኮ​ቶች ነበ​ሩ​ባ​ቸው፤ ደግ​ሞም በደጀ ሰላሙ ውስጥ በዙ​ሪ​ያው መስ​ኮ​ቶች ነበሩ፤ በግ​ን​ቡም አዕ​ማድ ሁሉ ላይ የዘ​ን​ባባ ዛፍ ተቀ​ር​ጾ​ባ​ቸው ነበር።
17ወደ ውስ​ጠ​ኛው አደ​ባ​ባ​ይም አገ​ባኝ፤ እነ​ሆም በአ​ደ​ባ​ባዩ ዙሪያ የተ​ሠሩ ዕቃ ቤቶ​ችና ወለል ነበሩ፤ በወ​ለ​ሉም ላይ ሠላሳ ዕቃ ቤቶች ነበሩ። 18ወለ​ሉም በበ​ሮች አጠ​ገብ ነበረ፤ ይህም ታች​ኛው ወለል እንደ በሮቹ ርዝ​መት መጠን ነበረ። 19ከታ​ች​ኛ​ውም በር ፊት ጀምሮ እስከ ውስ​ጠ​ኛው አደ​ባ​ባይ ፊት ድረስ ወር​ዱን አንድ መቶ ክንድ አድ​ርጎ ወደ ምሥ​ራ​ቅና ወደ ሰሜን ለካ።
20ወደ ሰሜ​ንም መራኝ፤ እነ​ሆም በው​ጭው አደ​ባ​ባይ ያለ ወደ ሰሜን የሚ​መ​ለ​ከት በር ነበረ፤ ርዝ​መ​ቱ​ንና ወር​ዱ​ንም ለካ። 21የዕቃ ቤቶ​ቹም በዚህ በኩል ሦስት፥ በዚ​ያም በኩል ሦስት ነበሩ፤ የግ​ንቡ አዕ​ማ​ድና መዛ​ነ​ቢ​ያ​ዎ​ቹም፥ ወደ ምሥ​ራቅ የሚ​ያ​ሳዩ ዘን​ባ​ባ​ዎ​ቹም አምሳ ክንድ ነበሩ፤ ወር​ዱም ሃያ አም​ስት ክንድ ነበረ። 22መስ​ኮ​ቶ​ቹም፥ መዛ​ነ​ቢ​ያ​ዎ​ቹም፥ የዘ​ን​ባባ ዛፎ​ቹም ወደ ምሥ​ራቅ እን​ደ​ሚ​መ​ለ​ከ​ተው በር ልክ ነበሩ፤ ወደ እር​ሱም የሚ​ያ​ደ​ርሱ ሰባት ደረ​ጃ​ዎች ነበሩ፤ መዛ​ነ​ቢ​ያ​ዎ​ቹም በፊቱ ነበሩ። 23በው​ስ​ጠ​ኛ​ውም አደ​ባ​ባይ በሰ​ሜ​ኑና በም​ሥ​ራቁ በኩል በሌ​ላው በር አን​ጻር በር ነበረ፤ ከበ​ርም እስከ በር አንድ መቶ ክንድ አድ​ርጎ ለካ።
24ወደ ደቡ​ብም መራኝ፤ እነ​ሆም ወደ ደቡብ የሚ​መ​ለ​ከት በር ነበረ፤ የግ​ን​ቡን አዕ​ማ​ድና መዛ​ነ​ቢ​ያ​ዎ​ቹ​ንም እን​ደ​ዚ​ያው መጠን አድ​ርጎ ለካ። 25በእ​ር​ሱና በመ​ዛ​ነ​ቢ​ያ​ዎ​ቹም ዙሪያ እንደ እነ​ዚያ መስ​ኮ​ቶች የሚ​መ​ስሉ መስ​ኮ​ቶች ነበሩ፤ ርዝ​መቱ አምሳ ክንድ፥ ወር​ዱም ሃያ አም​ስት ክንድ ነበረ። 26ወደ እር​ሱም የሚ​ያ​ደ​ርሱ ሰባት ደረ​ጃ​ዎች ነበሩ፤ መዛ​ነ​ቢ​ያ​ዎ​ቹም በፊቱ ነበሩ፤ በግ​ን​ቡም አዕ​ማድ ላይ አንዱ በዚህ አን​ዱም በዚያ ወገን ሆኖ የዘ​ን​ባባ ዛፍ ተቀ​ር​ጾ​ባ​ቸው ነበር። 27በው​ስ​ጠ​ኛ​ውም አደ​ባ​ባይ በደ​ቡብ በኩል በር ነበረ፤ ከበር እስከ በር ድረስ በደ​ቡብ በኩል መቶ ክንድ አድ​ርጎ ለካ።
28በደ​ቡ​ብም በር በኩል ወደ ውስ​ጠ​ኛው አደ​ባ​ባይ አገ​ባኝ፤ እን​ደ​ዚ​ያ​ውም መጠን አድ​ርጎ የደ​ቡ​ብን በር ለካ፤ 29እን​ደ​ዚ​ያ​ውም መጠን አድ​ርጎ የዕቃ ቤቶ​ቹ​ንና የግ​ን​ቡን አዕ​ማድ፥ መዛ​ነ​ቢ​ያ​ዎ​ቻ​ቸ​ው​ንም ለካ፤ በእ​ር​ሱና በመ​ዛ​ነ​ቢ​ያ​ዎ​ቹም ዙሪያ መስ​ኮ​ቶች ነበሩ፤ ርዝ​መቱ አምሳ ክንድ፥ ወር​ዱም ሃያ አም​ስት ክንድ ነበረ። 30በዙ​ሪ​ያ​ውም ደጀ ሰላ​ሞች ነበሩ፤ ርዝ​መ​ታ​ቸ​ውም ሃያ አም​ስት ክንድ፥ ወር​ዳ​ቸ​ውም አም​ስት ክንድ ነበረ። 31መዛ​ነ​ቢ​ያ​ዎ​ቹም ወደ ውጭው አደ​ባ​ባይ ይመ​ለ​ከቱ ነበር፤ በግ​ን​ቡም አዕ​ማድ ላይ የዘ​ን​ባባ ዛፍ ተቀ​ርጾ ነበር፤ ወደ እር​ሱም የሚ​ያ​ደ​ርሱ ስም​ንት ደረ​ጃ​ዎች ነበሩ።
32በው​ስ​ጠ​ኛ​ውም አደ​ባ​ባይ በም​ሥ​ራቅ በኩል አገ​ባኝ፤ በሩ​ንም ለካ፤ መጠ​ኑም እንደ እነ​ዚያ ነበረ። 33እን​ደ​ዚ​ያም መጠን የዕቃ ቤቶ​ቹ​ንና የግ​ን​ቡን አዕ​ማድ፥ መዛ​ነ​ቢ​ያ​ዎ​ቹ​ንም ለካ፤ በእ​ር​ሱና በመ​ዛ​ነ​ቢ​ያ​ዎ​ቹም ዙሪያ መስ​ኮ​ቶች ነበሩ፤ ርዝ​መ​ቱም አምሳ ክንድ፥ ወር​ዱም ሃያ አም​ስት ክንድ ነበረ። 34መዛ​ነ​ቢ​ያ​ዎ​ቹም በስተ ውጭ ወደ አለው አደ​ባ​ባይ ይመ​ለ​ከቱ ነበር፤ በግ​ን​ቡም አዕ​ማድ ላይ በዚ​ህና በዚያ ወገን የዘ​ን​ባባ ዛፍ ተቀ​ርጾ ነበር፤ ወደ እር​ሱም የሚ​ያ​ደ​ርሱ ስም​ንት ደረ​ጃ​ዎች ነበ​ሩት።
35በሰ​ሜ​ንም ወደ አለው በር አመ​ጣኝ፤ እን​ደ​ዚ​ያ​ውም መጠን ለካው፤ 36የዕቃ ቤቶ​ቹ​ንና የግ​ን​ቡን አዕ​ማድ፥ መዛ​ነ​ቢ​ያ​ዎ​ቹ​ንም ለካ፤ በዙ​ሪ​ያ​ውም መስ​ኮ​ቶች ነበ​ሩ​በት፤ ርዝ​መ​ቱም አምሳ ክንድ፥ ወር​ዱም ሃያ አም​ስት ክንድ ነበረ። 37የግ​ን​ቡም አዕ​ማድ ወደ ውጭው አደ​ባ​ባይ ይመ​ለ​ከቱ ነበር፤ በግ​ን​ቡም አዕ​ማድ ላይ በዚ​ህና በዚያ ወገን የዘ​ን​ባባ ዛፍ ተቀ​ርጾ ነበር፤ ወደ እር​ሱም የሚ​ያ​ወጡ ስም​ንት ደረ​ጃ​ዎች ነበ​ሩት።
38በበ​ሮ​ቹም በግ​ንቡ አዕ​ማድ አጠ​ገብ ዕቃ ቤቱና መዝ​ጊ​ያው ነበሩ፤ በዚ​ያም የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት ያጥቡ ነበር። 39የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ው​ንም መሥ​ዋ​ዕት፥ የኀ​ጢ​አ​ቱ​ንና የበ​ደ​ሉ​ንም መሥ​ዋ​ዕት ያር​ዱ​ባ​ቸው ዘንድ፥ በበሩ ደጀ ሰላም በዚህ ወገን ሁለት ገበ​ታ​ዎች፥ በዚ​ያም ወገን ሁለት ገበ​ታ​ዎች ነበሩ። 40በሰ​ሜን በኩል በአ​ለው በር በስ​ተ​ው​ጭው፥ በመ​ወ​ጣ​ጫው ደረ​ጃ​ዎች አጠ​ገብ፥ በአ​ንዱ ወገን ሁለት ገበ​ታ​ዎች ነበሩ፤ በሌ​ላ​ውም ወገን በበሩ ደጀ ሰላም በኩል ሁለት ገበ​ታ​ዎች ነበሩ። 41በበሩ አጠ​ገብ በዚህ ወገን አራት ገበ​ታ​ዎች፥ በዚ​ያም ወገን አራት ገበ​ታ​ዎች ነበሩ፤ መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ያ​ር​ዱ​ባ​ቸው ገበ​ታ​ዎች ስም​ንት ነበሩ። 42ስለ​ሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውም መሥ​ዋ​ዕት ርዝ​መ​ታ​ቸው አንድ ክንድ ተኩል ወር​ዳ​ቸ​ውም አንድ ክንድ ተኩል ቁመ​ታ​ቸ​ውም አንድ ክንድ የሆኑ፥ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ትና ሌላ​ውን መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ያ​ር​ዱ​በ​ትን ዕቃ ያኖ​ሩ​ባ​ቸው ዘንድ፥ ከተ​ጠ​ረበ ድን​ጋይ የተ​ሠሩ አራት ገበ​ታ​ዎች ነበሩ። 43በዙ​ሪ​ያ​ውም በስ​ተ​ው​ስጥ የነ​በ​ረው የለ​ዘበ ከን​ፈ​ራ​ቸው አንድ ጋት ነበረ፤ በገ​በ​ታ​ውም ላይ#ዕብ. “በገ​በ​ታ​ዎ​ቹም ላይ የቍ​ር​ባኑ ሥጋ ነበ​ረ​ባ​ቸው” ይላል። መክ​ደኛ ነበረ፤ ከፀ​ሐ​ይና ከዝ​ና​ምም የተ​ሰ​ወረ ነበረ።
44ወደ ውስ​ጠ​ኛ​ውም አደ​ባ​ባይ አገ​ባኝ፤ እነ​ሆም ሁለት ቤቶች ነበሩ፤ አንዱ ወደ ሰሜን በሚ​መ​ለ​ከ​ተው በር አጠ​ገብ ነበረ፤ መግ​ቢ​ያ​ውም ወደ ደቡብ ይመ​ለ​ከት ነበረ፤ ሌላ​ውም ወደ ደቡብ በሚ​መ​ለ​ከ​ተው በር አጠ​ገብ ነበረ፤ መግ​ቢ​ያ​ውም ወደ ሰሜን ይመ​ለ​ከት ነበር። 45ሰው​ዬ​ውም፥ “ይህ ወደ ደቡብ የሚ​መ​ለ​ከት ቤት ለማ​ገ​ል​ገል ለሚ​ተጉ ካህ​ናት ነው። 46ወደ ሰሜ​ንም የሚ​መ​ለ​ከ​ተው ቤት መሠ​ዊ​ያ​ዉን ለማ​ገ​ል​ገል ለሚ​ተጉ ካህ​ናት ነው፤ እነ​ዚህ ከሌዊ ልጆች መካ​ከል ያገ​ለ​ግ​ሉት ዘንድ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ቀ​ርቡ የሳ​ዶቅ ልጆች ናቸው” አለኝ። 47አደ​ባ​ባ​ዩ​ንም በአ​ራት ማዕ​ዘኑ ርዝ​መ​ቱን መቶ ክንድ፥ ወር​ዱ​ንም መቶ ክንድ አድ​ርጎ ለካ፤ መሠ​ዊ​ያ​ውም በቤቱ ፊት ነበረ።
48ወደ ቤቱም ደጀ ሰላም አመ​ጣኝ፤ የደጀ ሰላ​ሙ​ንም የግ​ንብ አዕ​ማድ ወርድ በዚህ ወገን አም​ስት ክንድ፤ በዚ​ያም ወገን አም​ስት ክንድ አድ​ርጎ ለካ፤ የበ​ሩም ወርድ ዐሥራ አራት ክንድ ነበረ፤ በበ​ሩም በዚህ ወገ​ንና በዚያ ወገን የነ​በ​ሩት ግን​ቦች ሦስት ሦስት ክንድ ነበሩ። 49የደጀ ሰላ​ሙም ርዝ​መት ሃያ ክንድ፥ ወር​ዱም ዐሥራ ሁለት ክንድ ነበረ፥ ወደ እር​ሱም የሚ​ያ​ደ​ርሱ ዐሥር ደረ​ጃ​ዎች ነበሩ፤ አንድ በዚህ ወገን፥ አን​ድም በዚያ ወገን ሆነው በመ​ቃ​ኖቹ አጠ​ገብ የግ​ንብ አዕ​ማድ ነበሩ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ